ናቡከደነፆር ያየው ህልምና ዳንኤል የተረጎመው የምሰሉ ምስጢር እኛ አስካለንበት ደግሞም እስከ ጌታ ዳግም መምጣት ድረስ የሚዘልቅ ነው:: የዳንኤል መፅሐፍ የአለምን ሁኔታ እስከ ዘመን ፍፃሜ የሚሆነውን የሚገለፅ መፅሐፍ ነው::
በምድር ላይ ሊሆን ያለው የመለኮት ፈቃድ መተርጎሙ ትልቅ ነገር ነው:: ወደ ፈቃዱና አመራሩ መምጣት ደግሞ ታላቅ በረከት ነው::
እግዚአብሔር ገዢ ነው:: ደግሞም መሪ ነው:: እርሱ ሲመራን መንፈሱ ወደ እውነተኛ ንስሀ ይመራናል:: በፊቱም ትሁት እንሆናለን::