በእግዚአብሔር ላይ የታመነውና መደገፊያውንም እርሱን ያደረገ ዳንኤል በፊቱ ቅንነት ተገኝቶብኛል አነዳለ አማኝ የእግዚአብሐርን ክብሩንና ሉአላዊነቱነ የሚያይበት መንገዱ ቅንነት ነው:: ይህ ደግሞ አንዱ የጌታ ባህርይ ነው::
ቅንነት ባለበት በዛ ንፁህ ህይወት ይገለጣል:: ትእግስት የበዛለት በእውነትና በፅድቅ የሚኖረው ፀጋም የሚበዛለት እርሱ በቅንነት የሚሄደው ነው::
*** አማኝ ከቅንነት ከጎደለ ህሊናው ንፁህ አይሆንም:: በቅንነት የሚራመድ እርሱ ግን ከእግዚአብሔር ጋር ይራመዳል:: የዛሬን ብቻ ሳይሆን የወደፊት ዘመንም አሻግሮ ያያል