ዳንኤል በእግዚአብሔር ፊት በፀሎት ሲተጋ በብዙ ዝቅታና ራስን በማዋረድ በብዙ ትህትና ሆኖ ነው:: ስለዚህም ከእግዚአብሔር ዘንድ ያገኘው መልስ የራሱን ዘመን አልፎ እስከ ዘመን ፍፃሜ ያለውን የሚያሳይ ሆኗል::
በፀሎታችን ውስጥ የሚረዳን የጌታ መንፈስ እንዳለ ሁሉ ከትክክለኛው የፀሎት መንፈስ ሊያወጣን የሚዋጋን እንዳለ ልናስተውል ይገባል::
አማኝ የክፉውን ውጊያ ሊያሸንፍና ፀሎቱም ከጌታ ዘንድ መልስ የመጣ ዘንድ በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ በጎ ህሊና ሊኖረው የተገባ ነው::