አማኝ ለበራለት በትክክል ለተረዳውና ላመነው ጌታ ራሱን መሰዋዕት እሰከማድረግ ድረስ ፀንቶ ለመቆም የጨከነ ነው:: ይህም ደግሞ የፀጋውን ችሎት የሚያሳይ ነው:: የዳንኤል ህይወት ለዚህ ድነቅ ምስክር ረው::
ነገሮች በዙሪያችን ክፋታቸው በዝቶ ጫፍ ሲወጣ ሊያጠፉን የደረሱ እስኪመስል ድረስ ሊያስጨንቁን ይችላሉ:: ነገር ግን ይህ ሁኔታ አግዚአብሔር ፅድቁን የሚገልጥበት እኛም ክብሩንና ታላቅነቱን የምናይበት ይሆናል::
እግዚአብሔር ይናገራል አሁንም ይናገራል:: ሰውም ሰምቶ እስኪመለስ አብዝቶ ይታገሳል:: ደግሞም በፅድቅ የሚፈርድ ሰለሆነም በፍርድ ይገለጣል::