ፀሎት አንዱ እግዚአብሔርን የምንማርበት ህይወት ነው:: በቃሉ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን መህረትና ቸርነት ደገሞም የማዳኑን ሀይልና ታማኝነቱን በፀሎታችንውስጥ እንማራለን::
የእምነት ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር የሚያነካካን ነው:: በእምነት ወደ እግዚአብሔር ፊት የቀረበ ሰው ከፀሎቱ በኃላ በቀደመው ማንነትና ስሜት አይሆንም:: በመፅናናትና በተሰፋ በተሞላ በሌላ ማንነት በአሜን ይነሳል::
*** ነገሮችን ሁሉ በራሳችን ከማየት ወጥተን በእግዚአብሔር አይን ስናይ ፀሎታችንም በፊቱ እነደ እርሱ ፈቃድ ይመለስልናል:: እኛም ከድንጋጤና ፍርሃት ይልቅ በምሰጋናና በተሰፋ እንሆናለን::