ለአማኝ የተቀደሰው ሰፍራ የሰላም ወንጌል ነው:: በዚህ ሰፍራ መቆሙን ማስተዋልና ሊያደርግ የሚገባውን ሊያደርግ የተገባ ነው:: ይኸውም የመጀመሪያው የራስን ሸክም መጣልና የእግዚአብሔርን ሸክም መሸከም ነው:: የእግዚአብሔር ሸክም ደግሞ ሰላም የሞላበት ተስፋና መፅናናት ያለበት ነው::
የሰው ታሪክ በመለኮት ከሚተረጎምበት ቀን ጋር እስኪገናኝ ሰው በፀሎት ስፍራው ለም በዚህ አልፋለሁ ለምን ይሁ የሆንብኛል እያለ ያለቅሳል:: ለቅሶው የሚቆመው የሸክም ለውጥ የታሪክ ለውጥ ሲሆን ነው:: የእኛ ሸክም የእግዚአብሔር ሸከም ሲሆን የመለኮተ ትርጉ ሲመጣ::
*** ትክክለኛው የህይወታችን ታሪክ የሚተረጎመው ሁሉን በሚቆጣጠር በመለኮት ነው::