የምንሰማውንና የምናየውን ነገር በእኛ ላይ እንደሚሆን እንደሚደርስብንም አድርገን ስንቆጥር እንፈራለን:: የእግዚአብሔር ቃል እመን እንጂ አትፍራ እንደሚል በፊታችን ያለው አሰፈሪ ነገር ደግሞም የማስፈራራቱ ድምፅ እያለ ነገር ግን አለመፍራት የምርጫ ወይም የችሎታ ጉዳይ አይደለም:: የፀጋ ጉዳይ ነው እንጂ::
እምነት በጨመርን ቁጥር የሚያስፈራውን ነገር ከላይ ወደ ታች መመልከት እንጀምራለን:: እምነት ፍርሀትን አይቀበልምና::
*** የእግዚአብሔር ድምፅ በየዘመናቱ ደግሞ ዛሬም ለሕዝቡ አትፍሩ የሚል ነው::