Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about Voice of Truth and Life:How many episodes does Voice of Truth and Life have?The podcast currently has 1,418 episodes available.
January 31, 2021እግዚአብሔር ፃድቅ ነውእግዚአብሔር በባህርዩ ፃድቅ አምላክ ነው:: ይህም የትክክለኛነቱና የቅንነቱ መግለጫ ነው:: ይህ የተሰወረበት አማኝ ለራሱ የመሰለውን ይናገራል :: በእግዚአብሔርም ላይ የድፍረት ቃል አስከ ማውጣት ይደርሳል::የእግዚአብሔር ፅድቅ የተገለጠለት እርሱ በመጀመሪያ ከራሱ ነገር ይወጣል ራሱንም በፊቱ ያዋርዳል:: መንፈሳዊ ጤንነታችን ያለው እግዚአብሔር ፃድቅ ነው ባልንበት ላይ ነው::...more23minPlay
January 30, 2021ጌታ ነገሮችን ለክብሩ ይለውጣል ዮሐ 9፥ 1-12እግዚአብሔር ለጥያቄዎቻችን መልስ የሚሰጠው በእኛ ጊዜ ደግሞም እኛ በምንጠብቀው መንገድ አይሆንም:: ሰለዚህ ብዙ ጊዜ ጌታ የዘገየ ደግሞም የተወን ይመስለናል:: ነገር ግን እግዚአብሐር ሁሉን ለክብሩ በሚሆን መንገድ ይመልሳል:: ባልተጠባበቅነውም ሁኔታ ራሱን ይገልጥበታል :: ሁሉን ቻይነቱን ማዳኑን ቸርነቱንና በጎነቱን::...more24minPlay
January 29, 2021በፅድቅ መንቃት::የፅድቅና የህይወት ጉዳይ ጌታ በመስቀል ላይ ራሱን የሰጠበት ጉዳይ ስለሆነ በዚህ መደራደር ወይንም ይህን ተክቶ በህይወታችን ስፍራን የሚይዝ ሊኖር ፈፅሞ አይገባም:: እግዚአብሔር በፀጋው የሚገልፀው ወይም የሚሰራው የእኛን ህይወት ሳይሆን የሚያሳየው የፀጋውን ነገር የእግዚአብሔርን ሉዐላዊነትና ምህረት ነው የሚያሳየው:: *** በዘመናችን ደግሞም በዙሪያችን ያለውን ክፋት አሰራሩንም እያሰተዋልን በፅድቅ ልንነቃ ከኃጢአትና በደልም ልንርቅ ጊዜው ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው::...more44minPlay
January 29, 2021በጌታ ማረፍአማኝ እግዚአብሔርን አንደ አምላክነቱ መጠን እያወቀው በሄደ ቁጥር እረፍት እየተሞላ ይሄዳል:: ታላቅነቱንና ሁሉን ቻይነቱን ታማኝነቱንና የማይለወጥ እንደ ቃሉ መሆኑን መረዳት: ከምናልፍበት አንዳንድ ሁኔታዎች ተፅእኖ ሥር እንዳንወድቅ ደግሞም በክፉው የማስፈራሪያ ወጥመድ ውስጥ እንዳንወድቅ ያደርጋል:: የእግዚአብሔር አይኖች በምድር ዙሪያ ሀሉ ያያሉ:: ስለዚህ የኛ ነገር ሁሉ በእርሱ ፊት ነው:: ይህን ማወቅ እግዚአብሔርን በአምላክነቱ ችሎት ማወቅና ማክበር ደግሞም በእርሱ መደገፍ ነው::...more51minPlay
January 28, 2021በዚህ ምድር የላቀ የመኖራችን ምክንያት ሐዋ.27:10-25 ክፍል ሁለትኢየሱስ ክርስቶስን በማመን የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑ ሁሉ በምድር ላይ ያለው ህይወታቸው አላማ ወንጌል ነው:: ያለተስፋ በጨለማ ላሉት ብንሃን በረከትና መፅናናት ለመሆን ነው::የምናልፍባቸው ፈተናዎችና አንዳንድ አስጨናቂ ሁኔታዎች የሚያጠፉን ሳይሆኑ በእኛ ሁኔታ እግዚአብሔር ሊስራ ያለውን የዘላለም ፈቃዱን ሊገልጥበት ደግሞም እኛንም ወደ ላቀው የመኖራችን ምክንያት ወደ ሆነው ወደ ወንጌል እውነት ምሰክር ሊያመጣን ነው::...more34minPlay
FAQs about Voice of Truth and Life:How many episodes does Voice of Truth and Life have?The podcast currently has 1,418 episodes available.