Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about Voice of Truth and Life:How many episodes does Voice of Truth and Life have?The podcast currently has 1,418 episodes available.
January 14, 2021ፀሎትፀሎት ሸክም ነው :: ደገሞም ተዕዛዝ ነው:: ፀሎት በጉዳያችን ውስጥ ጌታን ማኖር ነው:: የሚፀልይ ሰው የሌለውን ነገር ወደፊት ያያል በፈረሰው ላይ ቆሞ የሚገነባውን የሚተደሰውን ያያል:: ዛሬ ላይ ሆኖ ነገን ያያል:: *** ሁላችን የምንፀልየው በሊቀካህኑ በኢየሱስ ስር ሆነን ነው:: ሰለዚህ ፀሎታችን ኢየሱስን በመምስል መሆን አለበት:/ የፍቅር ሰው: ይቅር ባይ: ትሁት ወዘተ.../::...more33minPlay
January 14, 2021እግዚአብሔር አዲስ ነገርን ያደርጋል ት.ኢሳ.43:18-21 ክፍል ሁለትእግዚአብሔር አዲስ ነገር አደረጋለሁ የቀደመውን አታስቡ ሲል: በዘመናት ድንቅን የሚያደርግ ክንዱን ሀይሉንና ብርታቱን ሳይሆን: አታስቡ የሚለው አደራረጉን ነው:: እግዚአብሔር እርሱ ሀሳቡን እንደወደደ በራሱ መንገድ ይሰራልና አሰራሩ ሁልጊዜ አንድ አይነት አይደለም:: *** የእግዚአብሔር ህልውና መገኘት ከእኛ ጋር ይሁን እንጂ ከፊታችን ባለው አስፈሪና አሰጨናቂ ሁኔታ ላይ የምንሻገርበትንና የምናልፍበትን ያልተጠባበቅነውን አዲስ ነገር ያደርጋል:: ምስጋናም ይበዛልናል::...more46minPlay
January 13, 2021መንፈሳዊ ምሪት ትምህርት አራትእውነተኛ የሆነ የክርስቶስ ህይወት ኑሮ ባለበት በዛ የመንፈስ ቅዱስ ምሪት አለ:: በመንፈስ ምሪት ውስጥ ያለውም የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው:: የእርሱም ፈቃድ በእኛ የሚሰራው ደግሞ የራሳችንን ፈቃድ በተውንበት በጣልንበት ነው::*** ሁሉን የሚችል አምላክ ፈቃዱን በእኛ ድካም ውስጥ ሊፈፅም በወደደ ጊዜ የእኛ ድርሻ ምሪቱን መቀበል መታዘዝ ደግሞም ፈቃዱን የሚፈፅመውን ጌታ ማሰቀደም እኛም ደግሞ መከተል ነው::...more1h 2minPlay
January 13, 2021ምስጋና ይብዛልን:: መሣ.5:1-3 ክፍል አንድ::እግዚአብሔር ሰላምና እረፍትን ወደ ህይወታችን ሲያመጣ አላማው ወደ እርሱ እንድንጠጋና በምስጋና እንድንሆን ነው:: በሰላም ጊዜ እግዚአብሔር እንዳለና እንደሚመራን እንዲሁ የጨለማ ጊዜ የመከራ ጊዜ በምንለውም ውስጥ እርሱ አለ ይመራናልም:: በዚህም ውስጥ ምስጋና ለእግዚአብሔር ነው::*** በነገር ሁሉ እግዚአብሔርን ስናመሰግን የምናደርገው እግዚአብሔርን ከፊት እኛን ከኃላ::...more35minPlay
January 12, 2021ተግዳሮትን በድል ማለፍ:: ኢያሱ 6:1-27እግዚአብሔር ህዝቡን በመንገዱ ይመራል:: ሲመራም በድልና በሸናፊነት ነው:: በመንገዳችን እርሱ ከእኛ ይሁን እንጂ ተግዳሮቶቻችንን እናልፋቸዋለን:: በእኛ ማንነት ሳይሆን በፀጋ ሐይልና ጉልበት:: *** እግዚአብሔር የሚያስኬደን መንገድ ሁልጊዜ በእምነትና በመታዘዝ አንድንከተል የሚጠይቅ ደግሞም ሰላምንም የሚሞላ ነው::...more39minPlay
January 12, 2021መንፈሳዊ ምሪት ትምህርት ሦስትእኛ ሰዎች ነንና የመንፈስ ቅዱስን ፈቃድ የምናውቀው ከፍለን ነው:: ምሪቱ የሚገባን ደግሞም ፈቅደን የምንቀበለው በራሳችን ነገርና ሁኔታ ባልተያዝንበት መጠን ነው:: የመንፈስ ምሪት ትክክለኛውን መንገድ እንድንሔድ እንድንኖርም ያደርጋል:: ይህ በፀጋው ችሎት እነጂ በእኛ አይደለም::*** የመንፈስ ቅዱስ ምሪት ለህይወታችን ደግሞም በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ለምንስራው ስራ ፍሬያማነት ዋነኛ ነው::...more1h 6minPlay
January 11, 2021መንፈሳዊ ምሪት ትምህርት ሁለትምሪት የሚያስፈልገን የምንኖረው ኑሮ የእግዚአብሔር ኑሮ ሲሆን ነው:: በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ስር ሰንሆን በእውቀት እያደግን ስንመጣ ወደ እገዚአብሔር ፈቃድ የምንደርስበትን ምሪት እንቀበላለን::ሰው ከእግዚአብሔር ሰአት ጋር የሚራመደው ራዕይ ስላለው ሳይሆን ምሪት ስላለው ነው:: ያለ ምሪት የሆኑ ሰዎች እነርሱ በራሳቸው ጊዜ ይወጣሉ በራሳቸው ጊዜ ይገባሉ::...more1h 1minPlay
January 11, 2021መንፈሳዊ ምሪት:: ትምህርት አንድ::የመንፈስ ቅዱስ ምሪት በመጀመሪያ በእርሱ ላይ የተጣለ ማንነትን ይሻል:: በእርሱ ላይ የተጣለ ደግሞ የእኔ የሚለው አማራጭ ሰለማይኖረው በምሪቱ ደስተኛ ነው:: እግዚአብሔረም በራሱ መንገድ ነገሮችን መገጣጠም ይጀምራል:: *** እግዚአብሔር እርሱ በማይቀድምበት አይመራንም:: ጌታ ሲመራን ከፊት ያለውን የሚያይልን ጌታ እርሱ ይቀድማል እኛም እነከተላለን::...more34minPlay
January 09, 2021መንፈሳዊ ከፍታመንፈሳዊ ከፍታ የእግዚአብሔረ አላማ በህይወታችን የሚከናወንበት በእርሱም በረከት የምንባረክበት ደግሞም በእርሱ አሸናፊነት አሸናፊውን ህይወት መኖር የምንጀምርበት ነው:: *** በእግዚአብሔረ ፀጋ ውስጥ ራሳችንን ያገኘንበት: ጨርሰን ከራሳችን ወጥተን ፀጋው ብቻ በእኛ የሚሰራበት እርሱ ነው ከፍታችን::...more20minPlay
FAQs about Voice of Truth and Life:How many episodes does Voice of Truth and Life have?The podcast currently has 1,418 episodes available.