የእግዚአብሔር አለሁነት ፍጥረት ሊረሳው በማይችል ሁኔታ ይገለጣል:: እርሱ ፃድቅ ፈራጅ ነውና ፍርድን በማደላደል ይገለጣል:: ደግሞም በማዳን በፈውስና በማፅናናት ይገለጣል::
እውነተኛው ምስክርነት እርሱ ብሏል ማለት ብቻ ሳይሆን እኛም ደግሞ እውነት ነው እርሱ ያለው ለእኔ ሆኗል ሰንል ነው:: ደግሞም በአስፈሪውና በአስጨናቂው ፊት እርሱ ብሏልና እኔም እላለሁ ብለን ፀንተን ስንቆም ነው::
*** አንድን አማኝ እግዚአብሔር ጠንካራ ማድረግ የሚፈልገው ሲያለቅስ በመስጠት ሳይሆን ነገር ግን በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ እኔ አለሁ በሚል ነው::