በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን አንዳንድ አካባቢዎች ውጊያዎች መካሄዳቸውን ነዋሪዎች አመለከቱ።
ቤኒን 2,000 ወታደሮቿን ወደ ሀይቲ ለመላክ መዘጋጀቷን የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣን አስታወቁ።
የሰሜን አትላንኒቲክ የጦር ቃል ኪዳን ኔቶ እግረኛ ወታደሮችን ወደ ዩክሬን የመላክ ዕቅድ እንደሌለው ዛሬ አስታወቀ። ጀርመን፣ ስፔን እና ፖላንድም ተመሳሳይ አቋማቸውን አሳውቀዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ በቀይ ባሕር ላይ ስጋት ናቸው ያለቻቸው የሁቲ ጀልባዎች፣ ሚሳኤሎችን እና ሰው አልባ አውሮፕላን የመን ውስጥ ማውደሟን አስታወቀች። ሁቲዎች በበኩላቸው ጥቃታቸውን የሚያቆሙት ለጋዛ መፍትሄ ሲገኝ ነው ብለዋል።