Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት... more
FAQs about የዓለም ዜና:How many episodes does የዓለም ዜና have?The podcast currently has 2,859 episodes available.
February 10, 2024የየካቲት 2 ቀን 2016 የዓለም ዜናበመራዊ የተፈጸመው የሰላማዊ ሰዎች ግድያ ላይ “ገለልተኛ ምርመራ ተደርጎ ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ” አሜሪካ ጥሪ አቀረበች። በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ እና በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ ልዑክ ማይክ ሐመር ወደ ኢትዮጵያ ሊጓዙ ነው። የሱዳን ጦርነት 700,000 ሕጻናትን ለብርቱ የተመጣጠነ ምግብ እጦት ሊያጋልጥ እንደሚችል የተመ አስጠነቀቀ። ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ የእስራኤል ወታደሮች በደቡባዊ ጋዛ ከምትገኘው ራፋ ሰላማዊ ሰዎች ለማሸሽ እንዲዘጋጁ ትዕዛዝ ሰጡ። አሜሪካ እና ብሪታኒያ በየመን በፈጸሙት ድብደባ የተገደሉ 17 የሑቲ ታጣቂዎች አባላት ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ...more10minPlay
February 08, 2024የጥር 30 ቀን 2016 የዓለም ዜናየኢትዮጵያ ብሔራዊ መረጃ እና ደሕንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው በመሥራት ላይ የነበሩት አቶ ተመስገን ጥሩነሕ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ታዬ አጽቀሥላሴ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ ዶክተር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ከአምስት ዓመታት ገደማ በፊት በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ የተፈረመውን ሥምምነት አፍርሷል ሲል ከሰሰ። ከቱኒያዝ የባሕር ዳርቻ ጀልባ ሰጥማ ሕይወታቸውን ያጡ 13 ሱዳናውያን አስከሬን ተገኘ። ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ የእስራኤል ወታደሮች በጋዛ ወደምትገኘው ራፋ ለመግባት እንዲዘጋጁ ትዕዛዝ ሰጡ።...more11minPlay
FAQs about የዓለም ዜና:How many episodes does የዓለም ዜና have?The podcast currently has 2,859 episodes available.