የሚያዝያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ዋና ዋና ዜናዎች፤
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ዑርጌሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በኦሮሚያ ክልል በህቡዕ ተጠርቷል በተባለው አድማ በአንዳንድ አካባቢዎች የመጓጓዣ እንቅስቃሴ ገደብ መኖሩ እየተነገረ ነው።
ሱዳን ውስጥ በየቀኑ 20 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው እንደሚፈናቀሉ የተመድ አመለከተ።
የኢራን እስራኤል ውዝግብ እንዳይባባስ ሃገራት እያሳሰቡ ነው። ኢራን በበኩሏ ውጥረቱ እንዲባባስ እንደማትፈልግ ስትገልጽ፤ የእስራኤል የጦር ካቢኔ ስብሰባ ማድረጉ ተዘግቧል።
ኦማን ውስጥ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ቢያንስ 14 ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተገለጸ።