Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት... more
FAQs about የዓለም ዜና:How many episodes does የዓለም ዜና have?The podcast currently has 2,860 episodes available.
January 15, 2024የጥር 6 ቀን 2016 የዓለም ዜናበአዲስ አበባ የሚገኘው የንፋስ ስልክ ቀለም ፋብሪካ ብርቱ የእሳት አደጋ ደረሰበት። የሱዳን ጦር በዋይት ናይል ግዛት በፈጸመው ድብደባ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን ተገደሉ። በሺሕዎች የሚቆጠሩ ትራክተሮች እና አስር ሺሕ ገደማ የጀርመን ገበሬዎች በበርሊን ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ። ከቀዝቃዛው ጦርነት ወዲህ ትልቁ በተባለ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) ወታደራዊ ልምምድ የብሪታኒያ 20 ሺሕ ወታደሮች እንደሚሳተፉ የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር ግራንት ሻፕስ ገለጹ። የጋዛ የጤና ሚኒስቴር በእስራኤል እና በሐማስ መካከል ውጊያ ከተቀሰቀሰ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ24 ሺሕ በላይ መድረሱን አስታወቀ።...more11minPlay
January 13, 2024የጥር 4 ቀን 2016 የዓለም ዜናየሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል አዛዥ መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ በመጪው ሐሙስ በዩጋንዳ በሚካሔደው የምሥራቅ አፍሪካ በይነ-መንግሥታት አስቸኳይ የመሪዎች ጉባኤ እንዲሳተፉ መጋበዛቸውን አስታወቁ። አሜሪካ በየመን የሑቲ አማጽያን ዒላማዎች ላይ ዛሬ ቅዳሜ ጠዋት የአየር ድብደባ ፈጸመች። ጋና ከኦፊሴያል አበዳሪዎቿ ጋር የ5.4 ቢሊዮን ዶላር የዕዳ አከፋፈል ሽግሽግ ሥምምነት ላይ ደረሰች። እስራኤል በጋዛ ለሊቱን በፈጸመችው የአየር ድብደባ ቢያንስ 60 ሰዎች መገደላቸውን በሐማስ የሚመራው የጤና ሚኒስቴር ባለሥልጣናት አስታወቁ። በአይቮሪ ኮስት አዘጋጅነት የሚካሔደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ ይጀመራል።...more8minPlay
January 08, 2024የታኅሳስ 29 ቀን 2016 የዓለም ዜናየሶማሊያ ፕሬዝደንት ሐሰን ሼይክ ሞሐመድ ከኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለመነጋገር አስመራ ገቡ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ዛሬ ሰኞ ከሶማሌላንድ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ኑር ኢስማኤል ታኒ ጋር በአዲስ አበባ ተገናኝተዋል። በላይቤሪያ የነዳጅ ማጓጓዣ ቦቴ ሲፈነዳ የገደላቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 74 ማሻቀቡን የሀገሪቱ መንግሥት አስታወቀ። በኢራን የሚደገፈው የሒዝቦላህ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ በደቡባዊ ሊባኖስ በእስራኤል ጥቃት ተገደሉ። የጀርመን መንግሥት በሒደት የግብርና ድጎማ ለማቋረጥ ያሳለፈውን ውሳኔ በመቃወም ሰልፍ የወጡ ገበሬዎች በትራክተሮቻቸው መንገድ ዘጉ።...more10minPlay
FAQs about የዓለም ዜና:How many episodes does የዓለም ዜና have?The podcast currently has 2,860 episodes available.