የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • DW Amharic የግንቦት 2 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    እናት ፓርቲ እና መኢአድ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በሚቀጥለው ወር ከሚካሔደው ምርጫ ራሳቸውን አገለሉ። የፍልስጤምን የተባበሩት መንግሥታት አባልነት የጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት እንዲቀበል የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ጠየቀ። በደቡብ አፍሪካ በግንባታ ላይ የነበረ ሕንጻ ሲደረመስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 12 ደረሰ። በቻድ ምርጫ ጄኔራል ማሕማት ኢድሪስ ዴቢ ማሸነፋቸው ሲሰማ ደስታቸውን ለመግለጽ አደባባይ ከወጡ ሰዎች መካከል የተወሰኑት ለፌሽታ በተተኮሰ ጥይት ሲገገደሉ በርካቶች ቆሰሉ። እስራኤል በራፋሕ የምታደርገው ዘመቻ ከፍተኛ ሰብአዊ አደጋ እንደሚያስከትል አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አስጠነቀቁ።
    11 min
  • የረቡዕ፤ ሚያዝያ 30 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አ.አ፥ የፕሬስ ነጻነት በኢትዮጵያ ማሽቆልቆሉ ተገለጠ፤ ወለጋ፥ ጠ/ሚ አብይ አሕመድ ነቀምቴ ስታዲየም ንግግር አሰሙ፤ ናይሮቢ፥ በጎርፍ አደጋው ማግሥት የኮሌራ ወረርሺን ሥጋት አጭሯል፤ ጋዛ፥ የራፋሕ መሸጋገሪያ ሰብአዊ ቀውሱ ተባብሷል፤ ሞስኮ፥ ከዩክሬን ጉዳይ ፈረንሣይ እጇን እንድታነሳ ሩስያ አስጠነቀቀች፤ ማድሪድ፥ለሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ ሪያል ማድሪድ ከባዬርን ሙይንሽን
    11 min
  • የሚያዚያ 29፣2016 የዓለም ዜና
    -መንገደኞችን አሳፍሮ ከሐዋሳ ወደ አዲስ አበባ ይበር የነበረ አንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ላይ እያለ የተፈጠረበት ጢስና መንጋጫገጭ መንገደኞችን ማስጋትና ማስጨነቁ ተነገረ።አዉሮፕላኑ አደጋ ሳይደርስበት አዲስ አበባ አርፏል።-የእስራኤል እግረኛ ጦር በሕዝብ የተጨናነቀችዉን የጋዛ የጠረፍ ከተማ ራፋሕን ለመዉረር መዘጋጀቱ አለም አቀፍ ሥጋትና ዉጥረት አስከትሏል።የፍልስጤም ራስ ገዝ መስተዳድር፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የአዉሮጳ ሕብረት ራፋሕ እንዳትወረር አሜሪካ ጣልቃ ትገባ ዘንድ እየተማፀኑ ነዉ።-የሩሲያዉ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን መንግስታቸዉ ከምዕራባዉያን ባለንጦቹ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን አስታወቁ።
    11 min
  • DW Amharic የዓለም ዜና፤ የሚያዝያ 28 ቀን 2016 ዓ.ም ሰኞ
    -የእስራኤል ጦር በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ ወታደራዊ ዘመቻን ለመጀመር ወደ 100 ሺህ የሚሆኑ የራፋህ ነዋሪዎች አካባቢዉን ለቀዉ እንዲወጡ አዘዘ።
    -የአዉሮጳ ህብረት የዉጭ ጉዳይ ተጠሪ ጆሴፕ ቦሬል እስራኤል በራፋህ የሚገኙ ሲቪል ነዋሪዎች እንዲለቁ ትእዛዝ ማስተላለፏ ሁኔታዉን አስከፊ ያደርገዋል ሲሉ አሳሰቡ። የዮርዳኖስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸዉ በፍልስጤማዉያን ላይ ሌላ እልቂት እያንዣበበ ነዉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
    -በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና አገልጋዮቿ ላይ የሚደረገው "ማሳደድና እስር በአስቸኳይ ይቁም" ሲል እናት ፓርቲ ጠየቀ።
    -ቻድ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እያካሄደች ነው።
    12 min
  • የዓለም ዜና፦ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም.
    የሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የላስታ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው መልሴና የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን አፈወርቅ እንዲሁም የራያ አላማጣ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው ሰሞኑን በታጣቂዎች ተግደለዋል ሲሉ ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ገልጸዋል።
    የጋዛው ጦርነት ጦርነቱ ዛሬ ቢቆም እንኳን የወደሙትን ቤቶች መልሶ ለመገንባት ቢያንስ 16 ዓመታት ሊወስድ እንደሚችል የተመድ አስታወቀ።
    የአውሮጳ ኅብረት ለሊባኖስ አንድ ቢሊዮን ዩሮ ወይም 1.07 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የፋይናናስ እርዳታ ለመስጠት ቃል ገባ።
    11 min
  • DW Amharic የሚያዝያ 23 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    የአውሮፓ ኅብረት ለኢትዮጵያውያን የቪዛ አሰጣጥ ሒደት እንዲጠብቅ ያሳለፈውን ውሳኔ እንዲያጤን ኢትዮጵያ ጠየቀች። የአፍሪካ ኅብረት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንቶች 6 ሚሊዮን ዶላር ለማጭበርበር የተደረገ ሙከራ ማክሸፉን አስታወቀ። ከ7 ሚሊዮን በላይ ደቡብ ሱዳናውያን የምግብ ዋስትና እጦት ሊገጥማቸው እንደሚችል ተመድ አስጠነቀቀ። እስራኤል በጋዛ ወደምትገኘው ራፋ ያቀደችውን ወታደራዊ ዘመቻ አሜሪካ አሁንም እንደምትቃወም ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ገለጹ። ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት የማረከቻቸውን የምራባውያን የጦር መሣሪያዎች፣ ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች እና ወታደራዊ ሠነዶች በሞስኮ ለዕይታ አቀረበች።
    9 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…