የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • DW Amharic የዓለም ዜና፤ የሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ሰኞ
    --የአውሮጳ ህብረት ለኢትዮጵያውያን ዜጎች የሚሰጠውን ቪዛ ለመገደብ መወሰኑን ዛሬ አስታወቀ። --በኬንያ ስምጥ ሸለቆ ከተማ አቅራቢያ የሚገኝ አንድ ግድብ ተንዶ በትንሹ 42 ሰዎች ሞቱ። -ቡርኪናፋሶ ወታደራዊ ጁንታ የዶቼ ቬሌን ራድዮ ጨምሮ የተለያዩ ዓለምአቀፍ የዜና ማሰራጫዎችንና ጋዜጦችን ማገዱ አስታወቀ። -የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የእስራኤል እና የሃማስ ጦርነት ሲያበቃ፤ ከአረብ ሀገራት መሪዎች ጋር በጋዛ ጉዳይ ላይ ለመምከር በሳዑዲ ዋና ከተማ ሪያድ መግባታቸዉ ተዘገበ።
    ዝርዝሩን ያድምጡ!
    10 min
  • DW Amharic የሚያዝያ 20 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    በኬንያ ከመጋቢት ጀምሮ እየጣለ የሚገኘው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 76 አሻቀበ። ሱዳን በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች “ትንኮሳ” ላይ የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት በአስቸኳይ እንዲወያይ ጥያቄ አቀረበች። የፖርቹጋል መንግሥት አፍሪካውያን በባርነት ሲሸጡም ሆነ በቅኝ ግዛት ወቅት ለተፈጸሙ ወንጀሎች ካሳ ለመክፈል ምንም አይነት ሒደት እንደማይጀምር አስታወቀ። ወግ አጥባቂው የእስራኤል የፋይናንስ ሚኒስትር ቤዛሌል ስሞትሪች በራፋ የታቀደው ወረራ ከተሰረዘ የጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁን መንግሥት እንደሚያፈርሱ ዛቱ። ሁለት ዩክሬናውያን በላይኛው ባቫሪያ በስለት ተወግተው መገደላቸውን የጀርመን ፖሊስ አስታወቀ።
    10 min
  • የሚያዚያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የኦፌኮ አመራሮች እስራት፤ የፓርቲው መግለጫ
    ሩዋንዳ፤ ለዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውንጀላ ምላሽ ሰጠች
    ቤኒን፤ ፖሊስ ሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጭስ ተኮሰ
    ሃማስ አዲሱን የእስራኤል የእርቅ ሃሳብ እንደሚያጤን አስታወቀ
    የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ጥሪ
    አትሌት መዲና ኢሳ በ 5ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን ሰበረች
    10 min
  • የዓለም ዜና፦ ሚያዚያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም.
    የሚያዚያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም. አርዕሰተ ዜና
    የአፍሪቃ ሕብረት «የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው» በሚል የተሰራጨው መረጃ «የተሳሳተ» ነው ሲል የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ አስታወቀ።
    የሶማሊያ መንግሥት ራሽን በመስረቅ የተጠረጠሩ በዩናይትድ ስቴትስ የሰለጠኑ የልዩ ኮማንዶ አባላት ማገዱንና ማሰሩን አስታወቀ።
    በጋዛ ሰርጥ አስቸኳይ ፣ቅድመ ሁኔታ የሌለውና ዘላቂ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ቻይና ጥሪ አቀረበች። የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ በጋዛ የተኩስ አቁም ላይ እንዲደረስ በጸጥታው ምክር ቤት የሚደረገውን ጥረት ማደናቀፍ እንዲቆምም ጠይቃለች።
    11 min
  • የሚያዝያ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የሰላም ሚኒስትር ደኤታ የነበሩት አቶ ታዬ ደንደአ በዛሬ ዕለት የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍና ጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው።
    ታንዛኒያ ውስጥ በደረሰ የጎርፍ አደጋ የ155 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አስታወቁ። እስያ ውስጥ ደግሞ በሙቀት ማዕበል ሰዎች እየሞቱ ነው። ቱርክና ግሪክ ከሰሃራ በመጣ አቧራ አየራቸው ታፍኗል።
    በማዕከላዊ ናይጀሪያ ከባድ ዝናብ በእስር ቤት ላይ ጉዳት ማድረሱን ተከትሎ 120 የሚሆኑ እስረኞች ማምለጣቸው ተሰማ።
    ባለፉት ጥቂት ዓመታት በኢትዮጵያም ሆነ በመላው ዓለም የወባ በሽታ ስርጭት በእጅጉ መስፋፋቱ እና የሚያደርሰው ጉዳትም እየከፋ መምጣቱ ተገለጸ።
    12 min
  • የሚያዚያ 16፣2016 የዓለም ዜና
    ባለፈው ሳምንት በሰነድ ማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ቀሲስ በላይ መኮንን ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡---አዲስ አበባ ዉስጥ የሁለት ቤተሰብ አባላት በሚኖሩበት ቤት ላይ ዛሬ ማለዳ የተናደ ድንጋይና አፈር 7 ሰዎች ገደለ።---ጎርፍ ሰሞኑን ኬንያ ዉስጥ 32፣ ታንዛኒ 58 ሰዎች ሲገድል ቡሩንዲ ዉስጥ ከ100 ሺሕ በላይ ሕዝብ አፈናቅሏል።-----ዓለም ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ፍፃሜ ወዲሕ የምትመራበት ሕግና ሥርዓት ከጥፋት አፋፍ ላይ መድረሱን አምንስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።
    12 min
  • የዓለም ዜና፦ ሚያዚያ 15 ቀን 2016 ዓ.ም.
    የሚያዚያ 15 ቀን 2016 ዓም አርዕስተ ዜና
    የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው በትግራይ እና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በሚገኙ ከተሞች በተነሳው ግጭት የተፈናቀሉት ሰዎች ቁጥር ከ50 ሺህ መብለጡን የተመድ አስታወቀ።
    ስደተኞችን የጫነች ጀልባ ጅቡቲ የባህር ዳርቻ ላይ ሰጥማ 16 ሰዎች መሞታቸውን 28 ሰዎች ደግሞ የደረሱበት እንዳልታወቀ IOM ዛሬ አስታወቀ።
    የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪቺ ሱናክ ብሪታንያ የሚገኙ ተገን ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ከመላክ የሚያግዳቸው እንደሌለ አስታወቁ። ስደተኞች በትናንሽ ጀልባዎች ወደ ብሪታንያ እንዳይመጡ የሚከለክል ሕግ የብሪታንያ ፓርላማ ካጸደቀ በኋላ ነው ሱናክ ይህን ያሉት።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…