የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የዓለም ዜና፦ ረቡዕ ሚያዚያ 2 ቀን 2016 ዓ.ም.
    አርዕስተ ዜና
    1 ሺህ 445 ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ዛሬ በመላ ኢትዮጵያ ተከብሮ ውሏል። በዓሉ በብሔራዊ ደረጃ በተለይም በአዲስ አበባ ስታድዮም በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች በተገኙበት በጋራ ፀሎትና በኢድ ሶላት ተከብሯል።
    የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር በቴ ዑርጌሳ ምስራቅ ሸዋ ዞን መቂ ከተማ ትናንት ሌሊት ካደሩበት ሆቴል ተወስደው መገደላቸውንና አስከሬናቸው ወደ ባቱ (ዝዋይ) መውጫ መንገድ ዳር ተጥሎ ዛሬ ጠዋት መገኘቱንም ተናግረዋል።
    እውቁ ተወዳጅ ድምጻዊ በኋላም መንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ የገባው ሙሉቀን መለሰ ትናንት በአሜሪካን ዋሽንግተን ዲሲ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
    11 min
  • የማክሰኞ ሚያዝያ 1 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አርዕስተ ዜና፦ አ.አ፥ የምክር ቤት አባላት የችሎት ውሎ፤ ጋምቤላ፥ አራት አመራሮች ከኃላፊነታቸው ተነሱ፤ ጅቡቲ፥ባሕር የሰጠሙ 38 ኢትዮጵያውያn አስክሬኖች ተሰበሰበ፤ ጄኔቫ፥የጉበት ተሐዋሲ በእየቀኑ ከ3,500 በላይ ሰዎች ሞት ምክንያት ነው ተባለ፤ ደብሊን፥የ37 ዓመቱ ሲሞን ሐሪስ የአየርላንድ ጠቅላይ ሚንሥትር ሆኑ፤ ማድሪድ፥ የሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች
    11 min
  • DW Amharic የመጋቢት 28 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ደጋፊዎች አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ሠልፍ አደረጉ። በአማራ ክልል የደብረ ብርሀን እና ደሴ ከተሞችን የሚያገናኘው ዋና አውራ ጎዳና ከዛሬ ጀምሮ ለመንገደኞች ክፍት እንደሆነ የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር አስታወቀ። ሐማስ የግብጽ አደራዳሪዎች ባቀረቡት ግብዣ ነገ እሁድ ለሚካሔደው የተኩስ አቁም ንግግር ልዑካኑን ወደ ካይሮ መላኩን አስታወቀ። ሩሲያ በዩክሬን ኻርካይቭ ከተማ በሚሳይሎች በፈጸመችው ድብደባ ስድስት ሰዎች ተገደሉ። በሶርያ ዳራ ግዛት በተከሰተ ፍንዳታ ሰባት ሕጻናት ተገደሉ። በፕራግ የግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ጌጤ ዓለማየሁ አሸነፈች።
    8 min
  • የመጋቢት 27 ቀን 2016 ዓም የዓለም ዜና
    ትናንት ጠዋት በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ በዳሞት መሰናዶ ትምህርት ቤት ውስጥ በተጣለ ቦምብ 31 ተማሪዎች መቁሰላቸው ተሰማ።
    ከምሥራቅ ወለጋ ዞኖች ተፈናቅለው ደብረብርሀን በመጠለያ ስፍራ ቆይተው የተመለሱ ዜጎች ወደ ገጠር ቤታቸው ገብተው መሥራት እንዳልቻሉ አመለከቱ።
    የዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ ጋር የ1,7 ቢሊየን ዶላር ብድር መፈራረሙን የፋይናንስ ሚኒስቴር አስታወቀ። የፓሪስ ክለብ አበዳሪ ሃገራትም ለኢትዮጵያ የሰጡትን የጊዜ ገደብ እስከ ሰኔ መጨረሻ ማራዘማቸው ተነገረ።
    እራስ ገዞቹ ፑንትላንድ እና ሶማሊላንድ የሶማሊያ መንግሥት የቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች እንዲዘጉ ያስተላለፈውን ውሳኔ እንደማይቀበሉ አስታወቁ።
    12 min
  • የመጋቢት 26፣2016 የዓለም ዜና
    -የኢትዮጵያ መንግስት ጦር ኃይል በአማራ ክልል አድርሶታል ተብሎ የሚጠረጠረዉን የጦር ወንጀል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንዲያጣራ ሁዩማን ራይትስ ወች ጠየቀ።የመብት ተሟጋቹ ድርጅት እንደሚለዉ የመንግስት ወታደሮች አማራ ክልል መራዓዊ ከተማ ዉስጥ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ገድለዋል።ሐብት ንብረት አዉድመዋልም።
    -የኢትዮጵያና የሶማሊያ የዲፕሎማሲ ዉዝግብ እየተካረረ ነዉ።ሶማሊያ ዛሬ በሞቃዲሾ የኢትዮጵያን አምባሳደር አባርራለች።የራስዋን አምባሳደርም ከአዲስ አበባ ጠርታለች።ፑንትላንድና ሶማሊላንድ የሚገኙ የኢትዮጵያ ቆስላ ፅሕፈት ቤቶች እንዲዘጉ አዝዛለችም።የፑንትላንድ ከፍተኛ ባለስልጣናት አዲስ አበባን እየጎበኙ ነዉ።
    13 min
  • የመጋቢት 24፣2016 የዓለም ዜና
    -የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመኖሪያ ቤት አከራይና ተከራዮችን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ያገለግላል ያለዉን አዲስ ሕግ አፀደቀ።ምክር ቤቱ «የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ» ያለዉ ሕግ በአከራይ፣ በተከራይና በመንግስት መካከል ግልፅነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን ይረዳል ተብሏል።
    -የእስራኤል ጦር ለጋዛ ሕዝብ ርዳታ የሚሰጡ ሠራተኞችን መግደሉን የሐገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር አመኑ።ጥቃቱን የተለያዩ መንግስታትና ድርጅቶች አዉግዘዉታል።በሌላ በኩል ደማስቆ-ሶሪያ የሚገኘዉ የቆንስላ ፅሕፈት ቤቷ ትናንት የጋየባት ኢራን እስራኤል ለመበቀል ዛተች።የዜናዉ መልዕክት የእስካሁኑ ነበር።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…