የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የመጋቢት 12፣2016 ዜና
    -ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማና አካባቢዉ ባካባቢዉ ሚሊሺያና ከሌላ አካባቢ የመጡ በተባሉ ታጣቂዎች መካከል በተደረገ ዉጊያ በትንሽ ግምት 10 ሰዎች ተገደሉ።ለሁለት ተከታታይ ቀናት የተደረገዉ ዉጊያ ዛሬ ጋብ ማለቱ ተነግሯል።-የሱዳን የርስ በርስ ጦርነት ለረሐብ ያጋለጠዉ ሕዝብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ፣ ረሐቡም ወደ ጠኔ እየከፋ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት የርዳታ ድርጅቶች ባለሥልጣናት አስታወቁ።ባለስልጣናቱ እንዳሉት አንዳድ አካባቢዎች ሕፃናት በረሐብና ረሐብ በሚያስከትለዉ በሽታ እየሞቱ ነዉ።-የአረብ እና የዩናይትድ ስቴትስ ሚንስትሮች የጋዛ ጦርነትን «ላጭር ጊዜ ለማስቆም» ያሉትን ስብሰባና ዉይይት እያደረጉ ነዉ።
    11 min
  • የዓለም ዜና፦መጋቢት 11 ቀን 2016 ዓ.ም.
    የመጋቢት 11 ቀን 2016 ዓም ዐርዕስተ ዜና
    የኢትዮጵያ የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በአዲስ አበባ ከተማ እና በዙሪያዋ "በትጥቅ የታገዘ ሁከት እና ብጥብጥ ለመፈፀም በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ" ያላቸው 50 ሰዎች መያዛቸውን አስታወቀ።
    የአማራ ክልል አሽከርካሪዎች በከፍተኛ የነዳጅ እጥረት ምክንያት ሥራችንን መስራት አልቻልንም ሲሉ ለዶቼቬለ ተናገሩ።የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ችግሩን ለመቀነስ ጥረት እየተደረገ ነው ብሏል።
    የእስራኤል ጦር በጋዛው የአልሺፋ ሆስፒታል የነበሩ 90 ታጣቂዎች መግደሉን ዛሬ አስታወቀ። ሀማስ በሆስፒታሉ ውስጥ የተገደሉት ተዋጊዎች ሳይሆኑ ሰለማዊ ሰዎች ናቸው ሲል አስተባብሏል።
    11 min
  • የመጋቢት 10፣2016 የዓለም ዜና
    -የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኮምፒዉቴር ቴክኒካዊ ችግር ምክንያት ደንበኞቹ አላግባብ ያዘዋወሩ ወይም ያወጡትን በቢሊዮን የሚቆጠር ብርለማስመለሥ እየጣረ መሆኑን አስታወቀ።ባንኩ ባለፈዉ አርብ ማታ ባጋጠመዉ የቴክኒክ ችግር ምክንያት ደንበኞቹ የራሳቸዉ ያልሆነ 2.4 ቢሊዮን ብር አዘዋዉረዋል ወይም አዉጥተዋል።-ባለፈዉ የካቲት ማብቂያ በታጣቂዎች ታግተዉ የነበሩ የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች ተገድለዉ አስከሬናቸዉ ተጥሎ መገኘቱን ቤተሰቦቻቸዉ አስታወቁ።የሟች ቤተሰቦች እንዳሉት ሠራተኞቹ ከታገቱ በኋላ አጋቾቹ ገንዘብ እንዲከፈላቸዉ ጠይቀዉ ከቤተሰቦች ጋር በመደራደር ላይ ነበሩ።
    11 min
  • የዓለም ዜና፤ መጋቢት 9 ቀን 216 ዓ.ም ሰኞ
    አርስተ ዜናዎች፤
    --የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሠ መስተዳድር በድንገት የተፈቱበትን ውሳኔ ኦነግ አጣጥሎ ነቀፈ። የታሰሩ አባሎቼ እስካሁን ክስ አልተመሰረተባቸዉም ሲል ከስዋል።
    --ከሁለት ዓመት በፊት ከፈረንሳይ ግዛት በእንግሊዝ የባህር ወሽመጥ ላይ ከሰመጡ 27 ሰዎች መካከል የአንድ ኢትዮጵያዊ ቤተሰብ በፈረንሳይ መንግሥት ላይ ክስ መሠረተ።
    --የእስራኤል ኃይሎች ጋዛ ኧል ሺፋ ሆስፒታል ላይ ጥቃት ጀመሩ። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ስጋታቸዉን ገልፀዋል።
    --የ71 ዓመቱ የሩስያ ፕሬዚደንት በዓለማችን ፈላጭ ቆራጭ ከተባሉ ሃገራት መንግሥታት የእንኳን ደስ ያሎት መልዕክት ተቀበሉ። ሙሉዉን ዜና ይከታተሉ!
    13 min
  • DW Amharic የመጋቢት 08 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግሎት ትላንት ቅዳሜ የተቋረጠው “ባንኩ በመደበኛነት በሥርዓቶቹ ላይ በሚያደርገው ማሻሻያ እና ፍተሻ ምክንያት” እንደሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ። የሶማልያ ፕሬዝደንት ሐሰን ሼይክ ማሕሙድ ዳግም ወደ ኤርትራ አቀኑ። የኒጀር መንግሥት ሀገሪቱ ከአሜሪካ ጋር የተፈራረመችውን ወታደራዊ ሥምምነት አቋረጠ። የአውሮፓ ኅብረት ለግብጽ የ8 ቢሊዮን ዶላር የብድር፣ ርዳታ እና መዋዕለ-ንዋይ ሥምምነት ይፋ አደረገ። የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ በጋዛ ጦርነት የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ። ኢትዮጵያውያኑ ጀማል ይመር እና ፍቅርተ ወረታ በሴዑል ማራቶን አሸነፉ።
    9 min
  • የዓለም ዜና፦ መጋቢት 6ቀን 2016 ዓ.ም.
    የመጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    የቀድሞ የሶማሌ ክልል ርዕሠ መስተዳድር አብዲ መሐመድ ዑመር እና የቀድሞ የሜቴክ የበላይ ሃላፊ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ከእስር ተለቀቁ ።
    አሸባብ መቅዲሾ ውስጥ በሚገኘው «ሳይ» በተባለው በዚሁ ሆቴል ላይ ትናንት ምሽት በደረሰው ጥቃት የአሸባብ ሚሊሽያዎችን ጨምሮ ቢያንስ ስምነት ሰዎች ተገደሉ። 18 ሰላማዊ ሰዎችና 9 ወታደሮች ቆስሉ።
    በሩስያ ለሦስት ቀናት የሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዛሬ ተጀምሯል። ምርጫው ሩስያ ከዩክሬን በገነጠለቻቸው ግዛቶችም ጭምር እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል። የ71 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለአምስተኛ የስልጣን ዘመን ነው የሚወዳደሩት።
    11 min
  • የሐሙስ መጋቢት 5 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
    *በኢትዮጵያ የአውሮጳ ኅብረትን ጨምሮ የቡድን 7 ሃገራት ልዑካን የፕሪቶሪያ የተኩስ ማቆም ስምምነት የአተገባበር ሥራዎችን ለመደገፍ ቁርጠኛነታቸውን ገለጡ ።
    *የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት የአቶ ክርስትያን ታደለ ያለመከሰስ መብት ተነሳ ። አቶ ክርስቲያን በምክር ቤት ያሰሙ በነበረው ፍርሐት አልባ ንግግራቸው ይታወቃሉ ።
    *300 ቶን ርዳታ የጫነች ሁለተኛ መርከብ ከቆጵሮስ ወደ ጋዛ ለመቅዘፍ መዘጋጀቷ ተገለጠ ።
    *በኔዘርላንድ ስደተኞች እና የእስልምና እምነት ተከታዮች ጠል ፓርቲ መሪ ሄርት ቪልደርስ ቀጣዩ ጠቅላይ ሚንስትር የመሆን ሕልማቸው መከነ ። እና ሌሎችም፦
    11 min
  • የዓለም ዜና፦ መጋቢት 4 ቀን 2016 ዓ.ም.
    የመጋቢት 4 ቀን 2016 ዓም የዓለም ዋና ዋና ዜና
    -የእርዳታ ድርጅቶች ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ጋዛ ለማስገባት እየጣሩ ነው
    -ፍልስጤማውያንን የሚረዳው የተመድ ቅርንጫፍ የሚሰጠው እርዳታ ላይ የተጣለው እገዳ ሊቀጥል ይችላል
    -ሾልዝ ታውሩስን ለዩክሬን የማይሰጡበትን ምክንያት ለጀርመን ፓርላማ ተናገሩ - የአውሮጳ ኅብረት ለሄይቲ እርዳታ ሊልክ ነው
    -በሀማስ ታግቶ የነበረው ጀርመናዊ እስራኤል መሞቱ ተነገረ
    11 min
  • የመጋቢት 3 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የመጋቢት 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ዋና ዋና ዜናዎች
    ዩናይትድ ስቴትስ አሸባብን በገንዘብ ይደግፋሉ ባለቻቸው 16 ግለሰቦች እና የንግድ ተቋማት ላይ ማዕቀብ ጣለች።
    የሱዳን ጦር የሀገሪቱን ብሔራዊ የራዲዮ እና ቴሌቪዝን ጣቢያ ዋና መሥሪያ ቤት በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ሥር ማድረጉን አስታወቀ።
    በቀውስ የምትታመሰው የሄይቲ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሥልጣን ለመውረድ መስማማታቸውን አስታወቁ።
    15 ሰዎችን ያሳፈረ የሩሲያ ወታደራዊ መጓጓዣ አውሮፕላን ከተነሳበት ብዙም ሳይርቅ ተከሰከሰ። ከተሳፋሪዎቹ የተረፈ ሰው ስለመኖሩ የተነገረ ነገር የለም።
    10 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…