የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የዓለም ዜና፦የካቲት 22 ቀን 2016 ዓ.ም.
    የየካቲት 22 ቀን 2016 ዓ.ም. አርዕሰተ ዜና
    -በባሕርዳር ዛሬ ጠዋት በከተማው ቀበሌ 14ና በተለምዶ ዓባይ ማዶ በተባሉት የከተማው አካባቢዎች የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ነዋሪዎቹ ለዶቼቬለ ተናገሩ፡፡
    -ባለፈው መስከረም በጀርመንዋ ሽቱትጋርት ከተማ በተካሄደ የኤርትራውያን ድግስ ላይ በተነሳው ብጥብጥ መንስኤ የሽቱትጋርት ፍርድ ቤት የ29 ዓመት ኤርትራዊ ወጣት ላይ የሦስት ዓመት ከ9 ወራት እሥራት መበየኑን የፍርድ ቤቱ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
    -ትናንት የእስራኤል ወታደሮች ርዳታ ለመውሰድ ይሞክሩ በነበሩ ሲቪል ፍልስጤማውያን ላይ በከፈቱት ተኩስ በርካታ ፍልስጤማውያን መገደላቸው ከዓለም ዙሪያ ውግዘት ገጥሞታል።
    13 min
  • የዓለም ዜና ፤ የካቲት 21 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ሃሙስ
    በአማራ ክልል በሀገር መከላከያ ሰራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በሚደረገው ውጊያ ሳቢያ በክልሉ የምግብ እና የሸቀጦች ዋጋ በማሻቀቡን የክልሉ ነዋሪዎች ገለፁ። በዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ዘመን በመቅደላ ጦርነት ተዘርፎ እንጊሊዝ የነበረዉ ጥንታዊ ቅርስ በኢትዮጵያን ባለስልጣናት ግፊት ለሽያጭ ጨረታ ሳይቀርብ መቅረቱ ተነገረ። የቅርስ ሽያጩ የተሰማዉ ከአዉሮጳ የዘረፉበት ቅርሶች እየመለሱ ባለበት በአሁኑ ወቅት ነዉ። የጋና ፓርላማ በተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የሚከሰሱ ሰዎችን፤ በእስር ለመቅጣት አዲስ ረቂቅ ሕግ አፀደቀ። ዩናይትድ ስቴትስ ረቂቅ ሕጉ፤ ሕገ መንግሥታዊ ነፃነቶችን አደጋ ላይ የሚጥል ስትል እንዳሳሰባት ገለፀች።
    13 min
  • የዓለም ዜና፦የካቲት 20 ቀን 2016
    የየካቲት 20 ቀን 2016 ዓም ዐርዕስተ ዜና
    በጋምቤላ ክልል ጋምቤላ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ ወረዳዎች ከግንቦት 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በተከሰቱ ግጭቶች ቢያንስ የ138 ሰዎች ሕይወት ማለፉንና 113 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን ማረጋገጥ መቻሉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ አስታወቀ።
    ፈረንሳዊው ጋዜጠኛ አንቷን ጋሊንዶ በቁጥጥር ስር የዋለው ከተሰጠው የዘገባ ፈቃድ ውጭ መረጃዎችን ለመሰብሰብ በመንቀሳቀሱ ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ።
    በቀይ ባህር በሚተላለፉ የንግድ መርከቦች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለመከላከል የተሰማራው የጀርመን ባህር ኃይል የሁቲዎችን ጥቃት መመከቱ ተነገረ።
    12 min
  • የየካቲት 19 ቀን 2016 ዓ.ም. ዋና ዋና ዜናዎች
    በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን አንዳንድ አካባቢዎች ውጊያዎች መካሄዳቸውን ነዋሪዎች አመለከቱ።
    ቤኒን 2,000 ወታደሮቿን ወደ ሀይቲ ለመላክ መዘጋጀቷን የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣን አስታወቁ።
    የሰሜን አትላንኒቲክ የጦር ቃል ኪዳን ኔቶ እግረኛ ወታደሮችን ወደ ዩክሬን የመላክ ዕቅድ እንደሌለው ዛሬ አስታወቀ። ጀርመን፣ ስፔን እና ፖላንድም ተመሳሳይ አቋማቸውን አሳውቀዋል።
    ዩናይትድ ስቴትስ በቀይ ባሕር ላይ ስጋት ናቸው ያለቻቸው የሁቲ ጀልባዎች፣ ሚሳኤሎችን እና ሰው አልባ አውሮፕላን የመን ውስጥ ማውደሟን አስታወቀች። ሁቲዎች በበኩላቸው ጥቃታቸውን የሚያቆሙት ለጋዛ መፍትሄ ሲገኝ ነው ብለዋል።
    12 min
  • የዓለም ዜና፤ ካቲት 18 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ሰኞ
    አርስተ፤ ዜና
    «የኢትዮጵያ መንግሥት በሃይማኖት ተቋማት እና አባቶች ላይ የሚደርሰውን "በደል እና የግፍ ግድያ" እንዲያስቆም ለተቋማቱም ጥበቃ እንዲያደርግላቸው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዛሬ ጠየቀ። ለአፍሪቃ ህብረት የመሪዎች ስብሰባን ለመዘገብ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ የነበረ አንድ ፈረንሳዊ ጋዜጠኛ መታሰሩን ተሰማ። ጋዜጠኛዉ የታሰረዉ አንድ የኦነግ ቃል አቀባይን ሲጠይቅ ነዉ ተብሏል። በትግራይ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተዉ ከፍተኛ በድርቅ በክልሉ የሚኖረዉን ህዝብ እየፈተነዉ። ሁለት ዓመት ባስቆጠረው የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት በአጠቃላይ 31 ሺህ ወታደሮች እንደተገደሉባት የዩክሬን ፕሬዚዳንት አስታወቁ።»
    12 min
  • የየካቲት 17 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የተፈጸመ ግድያ “በገለልተኛ አካል እንዲጣራ” ጥሪ አቀረበ።
    ኤኮዋስ በኒጀር ላይ ከተጣሉ ማዕቀቦች የተወሰኑትን አነሳ። የደቡብ አፍሪካው ገዢ ፓርቲ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ደጋፊዎች የጫነ ተሽከርካሪ ዛሬ ጠዋት በገጠመው አደጋ ዘጠኝ ሰዎች ሞቱ። የቀድሞው የናሚቢያ ፕሬዝደንት ሐጌ ጋይንጎብ ሥርዓተ-ቀብር ዛሬ እሁድ ተፈጸመ። በፓሪስ የተካሔደ ውይይት ሐማስ ታጋቾችን እንዲለቅ እና በጋዛ ተኩስ እንዲቆም ሊያደርግ ወደሚችል ሥምምነት ሊያመራ እንደሚችል “መግባባት” መኖሩን አሜሪካ አስታወቀች።
    9 min
  • የዐርብ የካቲት 15 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አራት መነኮሳት በታጣቂዎች ተገደሉ፤ ሕወሓት 2 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱን አባረረ፤ የአንጋፋው ድምፃዊ የጌታቸው ካሳ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ ተፈጸመ፤ ኬኒያዊው የማራቶን ጀግና ኬልቪን ኪፕቱም ተቀበረ፤ በእሳት አደጋ ቢያንስ አምስት ሰዎች ሞተዋል፤ ኦዲሴየስ መንኲራኲር ጨረቃ ላይ በስኬት አረፈች
    9 min
  • የዓለም ዜና፤ የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም ሃሙስ
    አርስተዜና፤ የአማራ ክልል ምክር ቤት የአቶ ዮሐንስ ቧያለውን ያለመከሰስ መብት አነሳ። በዓለም ዙሪያ የተፈናቀሉ ህፃናት ቁጥር ከሦስት ዓመታት ወዲህ በእጥፍ መጨመሩ ተመለከተ ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የፓርቲውን ህልውና እየተፈታተነ ይገኛል “ ሲል የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ «ሲፌፓ» አስታወቀ ። ቱርክ ለሶማሊያ የባህር አገልግሎት የፀጥታ ድጋፍን በመስጠት አገሪቱ የዉኃ ግዛትዋን እንድትጠብቅ ድጋፍ ታገኛለች ሲል የቱርክ መከላከያ ሚንስትር አስታወቀ።
    10 min
  • የየካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ሶማሊያ በዛሬው ዕለት ከቱርክ ጋር የመከላከያ ስምምነት መፈራረሟን አስታወቀች።
    ዩናይትድ ስቴትስ የተመድ እስራኤልን ከፍልስጤም ግዛት የደህንነት ዋስትና ሳይሰጣት በሕግ አስገድዶ ሊያስወጣ እንደማይገባ አሳሰበች።
    በሕንድ የገበሬዎች ተቃውሞ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
    ብራስልስ፤ የአውሮጳ ሕብረት በሩሲያ ላይ አዲስ ማዕቀብ አጸደቀ።
    አዲስ አበባ፤ አንጋፋው የሙዚቃ ሰው ጌታቸው ካሣ አረፈ።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…