የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የዓለም ዜና፤ መጋቢት 2 ቀን 2016 ዓ.ም ሰኞ
    --የአፍሪቃ ሕብረት በኢትዮጵያ መንግሥትና በህወሓት መካከል ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ የተፈረመውን የፕሪቶሪያ ስምምነት አፈፃፀም ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ መገምገም ጀመረ።
    የተመድት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ዛሬ የጀመረዉን የረመዳን ጾምን በማስመልከት በእስራኤል-ሀማስ መካከል ጋዛ ሰርጥ ዉስጥ የሚካሄደዉ ጦርነት ብሎም የሱዳኑ ግጭት እንዲቆምና እርቅ እንዲወርድ ጥሪ አስተላለፉ።
    --በዓለማችን በጦር መሳርያ ንግድ ቀዳሚዋ የሆነችዉ ዩናይትድ ስቴትስ ዘንድሮም ቀዳሚዉን ስፍራ መቀጠልዋን ዓለም አቀፍ የሰላም ምርምር ተቋም አመለከተ። ሁለተኛዋ አገር ፈረንሳይ ነች ተብሏል። ሩስያ ወደ ሦስተኛ ደረጃ ዝቅ ማለትዋም ተመልክቷል።
    13 min
  • የየካቲት 29 ቀን 2016 ዓም የዓለም ዜና
    አርዕስተ ዜናዎች
    ከ250 ሚሊየን በላይ አዋቂ እና አዳጊ ሴቶች ግርዛት እንደተፈጸመባቸው ዛሬ ይፋ የተደረገ ጥናት አመለከተ።
    በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ በመቶዎች የሚቆጠሩ የመንግሥት ሠራተኞች፣ የቀበሌ አመራሮችና ሚሊሻዎች ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን መፈናቀላቸው ተሰማ። «የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት» ኦነሰ በወረዳው የሚገኙ አብዛኞቹን ቀበሌያት መቆጣጠሩን ተፈናቃዮቹ ገልጸዋል።
    በሀረሪ ክልል አሚር ኑር ወረዳ የክልሉ መስተዳድር ሕገወጥ ናቸው ያላቸውን ይዞታዎች ለማፍረስ በወሰደው እርምጃ ግጭት ተከስቶ የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ።
    10 min
  • የሐሙስ የካቲት 28 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የአፍሪቃ ኅብረት የፕሪቶሪያ ስምምነት አፈጻጸም ግምገማ መጀመሩ ተገለጠ፤ በጦርነቱ 16 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ንብረት መውደሙ ተገለጠ ፤ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ነፃነት ማሽቆልቆሉ «አሳሳቢ ነው» ተባለ፤ አአ፥ኢትዮጵያ ለስደተኞች አካታች የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት መዘርጋቷን ገለጠች፤ ሮም፥ ከተጨናነቀች የእንጨት ጀልባ ከተረፉ ስደተኞች የ17 ዓመት አዳጊ ሞተ፤ ማኒላ፥ በሁቲ ዓማጺያን በሚሳይል ከተመታችው መርከብ ሦስት ሠራተኞች ሞቱ፤ ቤርሊን፥ «የዶይቸ ባን» የባቡር እና የሉፍታንዛ አየር መንገድ ሠራተተኞች የሥራ ማቆም አድማ መቱ ።
    11 min
  • የዓለም ዜና፦ የካቲት 27 ቀን 2016 ዓ.ም.
    በባህር ዳርና አካባቢው እንዲሁም በኮረምና ዓላማጣ አካባቢዎች ትናንት ተቋርጦ የነበረው የኃይል አገልግሎትም ዛሬ መመለሱ ተገልጿል።
    የጀርመኑ የባድን ቩርተምበርግ ግዛት አስተዳደር በሽቱትጋርት ከተማ በኤርትራውያን ድግስ ላይ በተፈጸመ ኃይል የቀላቀቀ አመጽ አራት ዓመት የሚጠጋ እስር የተፈረደበትን ኤርትራዊ ከጀርመን ማባረር እንደሚፈልግ አስታወቀ።
    በበርካታ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች ትናንት የተካሄደውን የየፓርቲውን እጩ በሚያጸድቀው ምርጫ የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሸነፉ።
    በምርጫው የተሸነፉት የትራምፕ ተፎካካሪ ኒኪ ሄሊከምርጫ ዘመቻew ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታውቀዋል።
    11 min
  • የዓለም ዜና፤ የካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ማክሰኞ
    --ከባህር ዳር፤ በደብረታቦር፤ንፋስ መውጫ፤ጋሸና፤አላማጣ የተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር በመበጠሱ ኃይል ተቋርጧል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ። የአፋር ከተማ ሰመራና የተለያዩ ወረዳዎች እና የትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀሌን ጨምሮ በሌሎች ከተሞች የኤሌትሪክ ኃይል እንደተቋረጠ ተሰምቷል።
    --የኢትዮጵያ መንግሥት የኦነግ ቃል አቀባይ ባቴ ኡርጌሳንና ሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ ፖለቲከኞችን እያዋከበ ነው ሲል አምነስቲ አስታወቀ።
    --ከኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለዉ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የተጠለሉ ሰዎች ረሀብ መጋለጣቸዉ ተሰማ። የሞቱ ሰዎች እንዳሉም ተነግሯል።
    13 min
  • የየካቲት 25 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በመንግሥት ጦር ኃይል እና የፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ መቀጠሉ እየተነገረ ነው።
    የናይጀሪያ የድንገተኛ አደጋ ተቋም በዋና ከተማዋ አቡጃ የምግብ መደብሮች ከተዘረፉ በኋላ የመጋዘኖቹን ጥበቃ ማጠናከሩን አስታወቀ።
    በሄይቲ የአስቸኳይ ጊዜ እና የምሽት ሰዓት እላፊ ታወጀ።
    ሩሲያ ሾልኮ ወጣ በተባለ የድምጽ መረጃ ምክንያት የጀርመን አምባሳደርን በዛሬው ዕለት ጠርታ አነጋገረች።
    12 min
  • የየካቲት 23 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    ኢትዮጵያውያን ቅኝ ሊገዛቸው የሞከረውን የጣሊያን ጦር ተባበረው ቢያሸንፉም እርስ በርስ ባደረጉት ጦርነት ብርቱ ሰብአዊ ቀውስ መድረሱን ርዕሰ-ብሔር ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የዓድዋ ድል 128ኛ ዓመት ሲከበር ተናገሩ። በሱዳን የግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ለተቸገሩ ርዳታ እንዳያቀርቡ መተላለፊያ መከልከል በጦር ወንጀል ሊያስጠይቅ እንደሚችል ፎልከር ቱርክ አስጠነቀቁ። የቻድ ወታደራዊ መሪ ማሐማት ኢድሪስ ዴቢ ኢትኖ በሀገራቸው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ እንደሚወዳደሩ አስታወቁ። በጋዛ ርዳታ ከጫነ የከባድ ተሽከርካሪዎች ቅፍለት አቅራቢያ በተከፈተው ተኩስ በርካታ ሰዎች በጥይት ተመትተው መቁሰላቸውን የተመ ታዛቢዎች ቡድን አስታወቀ
    10 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…