የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የመጋቢት 22 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    ኬንያ ከአገር ጎብኚዎች የምታገኘው ገቢ እያደገ መምጣቱን የሃገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ።
    በቱርክ ዛሬ እየተካሄደ ባለው አካባቢያዊ ምርጫ በተነሳ ግጭት 1 ሰው ሲገደል 12 መቁሰላቸውን ተሰማ።
    የፈረንጆቹ የትንሳኤ በዓል በሚከበርበት በዛሬው ዕለት ሩስያ በዩክሬይን ሌቪቭ ዞን መጠነሰፊ የአየርና የሚሳይል ጥቃት ማካሄዷን አስታወቀች።
    ፈረንሳይ ለዩክሬን ተጨማሪ ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎችና የአየር መቃወሚያ ሚሳይሎችን እንደምትሰጥ አስታወቀች።
    11 min
  • DW Amharic የመጋቢት 21 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የመጀመሪያውን የሰነደ ሙዓለ-ንዋይ አማካሪነት ፈቃድ ለዲሎይት ሰጠ።የጋምቤላ ክልል ችግር “እየተባባሰ እንዲሔድ የማድረግ ዝንባሌ” እንዳለ የክልሉ መንግሥት አስጠነቀቀ።ባሲሩ ዲዮማይ ፋይ የሴኔጋል ፕሬዝደንት ሆነው ማክሰኞ ቃለ-መሐላ ሊፈጽሙ ነው። ደቡብ ሱዳን በጎረቤቷ ሱዳን በበረታው ጦርነት ሳቢያ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦዎች በመዘጋታቸው የኤኮኖሚ እና የፖለቲካ ቀውስ እንደሚያሰጋት ባለሙያዎች አስጠነቀቁ። በሰርቢያ ዋና ከተማ ቤልግሬድ በመካሔድ ላይ በሚገኘው የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና በወጣት ሴቶች የ6 ኪሎ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውን አትሌቶች አሸነፉ።
    8 min
  • የዓለም ዜና፦ መጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም.
    የመጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    ለስምንት ወራት በእሥር ላይ የቆዩት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል አቶ ዮሐንስ ቧያለው ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ።
    ደቡብ ሱዳን በጎረቤት ሱዳን በሚካሄደው ጦርነት ምክንያት ዋነኛው የነዳጅ ዘይት ማስተላለፊያ መስመር መዘጋት የኤኮኖሚና የፖለቲካ ቀውስ እንዳያስከትልባት አስግቷል።
    ሩስያ ትናንት ለሊቱን ዩክሬን በሚገኙ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ሰበብ በሦስት ግዛቶች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን ዩክሬን አስታወቀች ።
    11 min
  • የመጋቢት 19፣2016 የዓለም ዜና
    -የትግራይና የአማራ ክልላዊ መስተዳድሮች የቃላት እሰጥ አገባ አገርሽቷል።የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ባለፈዉ ሳምንት የአማራ ክልል «በኃይል የያዛቸዉን የትግራይ ሥፍራዎች የአማራ እንደሆኑ በማስተማሪያ መፅሐፍ አትሟል በማለት ወቅሶ ነበር።የአማራ ክልል ዛሬ ባወጣዉ መግለጫ የትግራይ ክልልን መግለጫ አሳሳች፣ካሐዲና ጠብ ጫርነትን የተሸከመ» በማለት ነቅፎታል።-የሶማሊያዉ አክራሪ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አል ሸባብ ማዕከላዊ ሶማሊያ ዉስጥ በሁለት አካባቢዎች በከፈተዉ ጥቃት 53 የመንግስት ወታደሮችን መግደሉን አስታወቀ።የሶማሊያ መንግስት ባለስጣናት ወታደሮች መገደላቸዉን ቢያምኑም ብዛቱን አልጠቀሱም።
    11 min
  • የመጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ዐርዕስተ ዜና
    የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብቸው ከተቀመጠ ገንዘብ ውጭ በሕገወጥ መንገድ ገንዘብ ወሰደው በከፊል ተመላሽ አደረጉ ያላቸው ግለሰቦች ቀሪውን ገንዘብ እስከ ቅዳሜ መጋቢት 21 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ካልመለሱ ማንነታቸውን በመገናኛ ብዙሀን ይፋ እንደሚያደርግ አስጠነቀቀ
    የባህር ዳር ከነማ የመሐል ሜዳ የእግር ኳስ ተጫዋች አለልኝ አዘነ የእግር ኳስ ቡድንኑ አስታወቋል።
    በዩናይትድ ስቴትሱ የሜሪላንድ ግዛት ዋና ከተማ ባልቲሞር የሚገኝ ድልድይ በመርከብ ተገጭቶ ከተደረመሰ በኋላ የደረሱበት አልታወቀም የተባለ ስድስት ሰዎች ፍለጋ ቆመ። የሕይወት አድን ሥራው ቆሞ ወደ አስከሬን ፍለጋ መገባቱን ባለስልጣናት ተናግረዋል።
    12 min
  • የመጋቢት 17፣2016 የዓለም ዜና
    -የአዲስ አበባ መስተዳድር በከተማይቱ የተለያዩ አካባዎች የሚገኙ መንደሮችንና ቤቶችን በጥድፊያ ማፍረሱን ነዋሪዎችና ነጋዴዎች ተቃዋሙ።ቅሬታ አቅራቢዎቹ እንደሚሉት መስተዳድሩ አንዳድ አካባቢዎች የሚገኙ ቤቶቹን የሚያፈርሰዉ አንድም ያለምንም፣ ሁለትም ባጭር ጊዜ ማስጠንቀቂያ ነዉ።-የኬንያ ባለስልጣናት በምፅዓት ቀን ኃይማኖታዊ ሰባኪ ልፈፋ ያለቁ ሰዎችን አስከሬን ለየቤተሰቦቻቸዉ ማደል ጀመሩ።እራሱን ፓስተር ብሎ የሚጠራ የቀድሞ ታክሲ ነጂን ሰበካ ሰምተዉ 430 ሰዎች በረሐብ፣ታፍነዉንና በእየር እጥረት ሞተዋል።-ሞስኮን ባሸበረዉ ጥቃት ሰበብ ሩሲያ ከዩክሬንና ከምዕራባዉያን መንግስታት ጋር አዲስ ዉዝግብ ገጥማለች።
    11 min
  • DW Amharic የመጋቢት 16 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት በጋዛ የተኩስ አቁም ላይ እንዲደረስ ጥሪ አቀረበ። የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በሚካሔደው ምርጫ ለመሳተፍ የመመዝገቢያ 50,000 ዶላር ክፈሉ መባላቸውን ተቃወሙ። በሴኔጋል ሥልጣን ላይ የሚገኘውን ጥምር ፓርቲ ወክለው ለፕሬዝደንትነት የተወዳደሩት አማዱ ባ የተቃዋሚ ፓርቲው ዕጩ ማሸነፋቸውን አምነው ተቀበሉ። የአሜሪካው አውሮፕላን አምራች ቦይንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ዴቪድ ካልሁን ከኃላፊነታቸው እንደሚለቁ አስታወቀ። የሩሲያ ፍርድ ቤት ከሞስኮ ወጣ ብሎ በሚገኘው ክሮከስ አዳራሽ ጥቃት ፈጽመው 137 ሰዎች በመግደል የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦች እስር ቤት እንዲቆዩ አዘዘ።
    10 min
  • DW Amharic የመጋቢት 15 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    የኢትዮጵያ መንግሥት “የውጭ ሀገር ሰዎች የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ” የሚፈቅድ ሕግ እያዘጋጀ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ። በሞቃዲሾ ሆቴል በተፈጸመ ጥቃት የተጠረጠሩ 16 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የሶማሊያ መንግሥት ገለጸ። በናይጄሪያ በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ ከ130 በላይ ተማሪዎች ተለቀቁ። ፕሬዝደንት ማኪ ሳልን ለመተካት ሴኔጋላውያን ድምጽ ሲሰጡ ዋሉ። በሞስኮ አቅራቢያ በሚገኘው ክሮከስ አዳራሽ በተፈጸመው ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 137 ደረሰ። ሩሲያ የዩክሬን ሁለት ከተሞችን በ57 ሚሳይሎች እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ደበደበች።
    10 min
  • የዐርብ፤ መጋቢት 13 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አቶ ዮሐንስ ቧያሌው፣ ዶክተር ካሳ ተሻገር እና አቶ ክርስትያን ታደለን ጨምሮ 14 በእሥር ላይ የሚገኙ ታዋቂ ፖለቲከኞች ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ «አካላዊ ፣ ሞራላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ጥቃት» እየተፈፀመባቸው መሆኑን ገለጡ፤
    የዩጋንዳ የረዥም ዘመን አምባገነን መሪ ፕሬዚደንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጄኔራል ልጃቸውን የሀገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር አድርገው ሾሙ ፤
    የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት በጋዛ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ስትል ዩናይትድ ስቴትስ ያቀረበችውን ረቂቅ ዛሬ ሳያፀድቅ ቀረ፤
    ሩስያ በስምንት ሚሳይሎች የዩክሬን ግዙፉን ዲኒፕሮ የኃይል ማመንጫ ተቋም ዛሬ ደበደበች ።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…