የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የዓለም ዜና፤ ሚያዝያ 11 ቀን 2016 ዓ.ም
    በቤጂንግ የግማሽ ማራቶን ውድድር ቻይናዊ ሯጭን ሆን ብለው አሸናፊ አድርገውታል የተባሉት ኢትዮጵያዊ እና ኬንያዊ አትሌቶች እንዲሁም ቻይናዊዉ አትሌት የወሰዱትን ሜዳሊያና ሽልማት ተነጠቁ። ኬንያ የመከላከያ ኢታማዦር ሹሙን ጨምሮ ሌሎች ዘጠኝ ከፍተኛ መኮንኖች በሄሊኮፕተር አደጋ ከሞቱ። ዛሬ በሃገሪቱ የሦስት ቀናት ሃዘን ታወጇል። በ1 ሚሊየን የምርጫ ጣቢያዎች ድምጻቸውን የሚሰጡ ህንዳውያን ለስድስት ሳምንታት የሚዘልቀዉን ምርጫ ዛሬ ጀመሩ። አሜሪካ በተመድ የፀጥታ ም/ቤት ውስጥ ሙሉ አባል ለመሆን ፍልስጤም ያቀረበችዉን ማመልከቻ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብቷን ተጠቅማ ዉድቅ አደረገች።
    10 min
  • የሚያዝያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የልጃገረዶች ጠለፋ መባባሱ ተገለጠ። በክልሉ ኮሬ ዞን ውስጥ «እየተባባሰ መጥቷል» ባሉት ጠለፋ የተነሳ ሴት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ መቸገራቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
    ቡርኪና ፋሶ ሦስት የፈረንሳይ ዲፕሎማቶችን ከሀገር አባረረች። ፈረንሳይ ውሳኔውን አሳዛኝ ብላዋለች።
    የደቡብ ሱዳን ፖለቲከኞች በሀገሪቱ ምርጫ ለማካሄድ አስቸኳይ እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው የተመድ አሳሰበ።
    ኢራን እስራኤል የኒኩሊየር ተቋሟ ላይ ጥቃት የምትሰነዝር ከሆነ በአጸፋው የእስራኤልን የኒኩሊየር መሰረተ ልማት ኢላማ እንደምታደርግ አስጠነቀቀች።
    11 min
  • የሚያዝያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የሚያዝያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ዋና ዋና ዜናዎች፤
    የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ዑርጌሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በኦሮሚያ ክልል በህቡዕ ተጠርቷል በተባለው አድማ በአንዳንድ አካባቢዎች የመጓጓዣ እንቅስቃሴ ገደብ መኖሩ እየተነገረ ነው።
    ሱዳን ውስጥ በየቀኑ 20 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው እንደሚፈናቀሉ የተመድ አመለከተ።
    የኢራን እስራኤል ውዝግብ እንዳይባባስ ሃገራት እያሳሰቡ ነው። ኢራን በበኩሏ ውጥረቱ እንዲባባስ እንደማትፈልግ ስትገልጽ፤ የእስራኤል የጦር ካቢኔ ስብሰባ ማድረጉ ተዘግቧል።
    ኦማን ውስጥ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ቢያንስ 14 ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተገለጸ።
    11 min
  • DW Amharic የሚያዝያ 05 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    ኢትዮጵያ በሶማሌላንድ የባሕር ኃይል እንድታቋቁም እንደማትፈቅድ ሶማሊያ አስታወቀች። በውይይት ኢትዮጵያ ለንግድ አገልግሎት ወደብ የምታገኝበትን ዕድል ሶማሊያ ልታጤን እንደምትችል የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናግረዋል። የአፍሪካ ኅብረት ማሊ ወደ ሲቪል አስተዳደር የምትመለስበትን ፍኖተ-ካርታ እንድታቀርብ ጠየቀ። ናይጄሪያ አዲስ የማጅራት ገትር መከላከያ ክትባት ለዜጎቿ መስጠት ጀመረች። ጀርመን የሩሲያን ጥቃት ለመመከት ለዩክሬን ተጨማሪ ፓትሪዮት የአየር መከላከያ ሥርዓት ልትሰጥ ነው። የኢራን አብዮታዊ ዘብ አባላት ከእስራኤል ግንኙነት አለው የተባለ መርከብ ተቆጣጠሩ። በአውስትራሊያ በስለት በተፈጸመ ጥቃት ስድስት ሰዎች ተገደሉ።
    8 min
  • የዓርብ ሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የአርብ ሚያዚያ ሦስት ቀን 2016 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    አዲስ አበባ ውስጥ በቦሌ ክፍለ ከተማ ዛሬ ጠዋት ፖሊስ የፋኖ አባላት ናቸው ካላቸው ግለሰቦች ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርጎ ሁለቱን መግደሉን አስታወቀ። ሁለት የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት መቁሰላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
    ፖሊስ ፣ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ የተጠረጠሩ 13 ሰዎችንማሰሩን የኦሮምያ ብሮድካስቲንግ ኔት ዎርክ ዘገበ ። ቡ
    በሳዑዲ ዓረቢያ እሥር ቤቶች ተይዘው ከነበሩት ኢትዮጵያውያን መካከል ከ800 የሚበልጡት ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ ።
    12 min
  • የሐሙስ ሚያዝያ 3 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አርዕስተ ዜና፦ መቐለ፥ ትግራይ ክልል «በእሥር ላይ ናቸው» የተባሉ የመከላከያ ሠራዊት አባላት፥ መቂ፤ የፖለቲከኛ ቤቴ ኡርጌሳ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ፤ ጄኔቫ፥የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲያከትም ተመድ ጥሪ አስተላለፈ፤ ጋዛ፥ የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሐማስ መሪ ሦስት ልጆች ተገደሉ፤ ኪዬቭ፥ ሩስያ የዩክሬን የኃይል ማመንጫዎችን በሚሳይሎች ደበደበች፤ ኢዝላማባድ፥ ፓኪስታን ለኢድ በዓል ሲጓዙ የነበሩ መንገደኞች አውቶቡስ ተገልብጦ 17 ሞቱ
    10 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…