የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • DW Amharic የግንቦት 12 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትሯ አይሻ መሐመድን የመከላከያ ሚኒስትር አድርገው ሾሙ።
    • በእነ ቀሲስ በላይ መኮንን ላይ የቀረበውን ክስ ዛሬ ያስቻለው ችሎት ተከሳሾች አሁንም በፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ ወሰነ።
    • በኪንሻሳ ትናንት በተካሄደው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ የውጭ ዜጎች እና ኮንጎዎች ተሳትፈዋል ሲል የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጦር ዛሬ አስታወቀ።
    • የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና ሶስት የሃማስ ከፍተኛ አመራሮች ላይ የእስር ማዘዣ እንዲጣል የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ICC ዋና አቃቢ ህግ ጠየቁ።
    10 min
  • የግንቦት 10 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ማንኛውም የውጭ ሀገር የሕክምና ቀጠሮ” ከመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል “ውጪ እንደማይፈቀድ” ተናገሩ። የኬንያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በቅርቡ ከተከሰተው ከባድ ጎርፍ ተጎጂዎችን መጠበቅ አልቻሉም፤ ቸልተኛም ነበሩ ባላቸው ሦስት ባለሥልጣናት ላይ ክስ መሠረተ። ደቡብ ሱዳን ከአንድ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ኩባንያ 13 ቢሊዮን ዶላር ለመበደር መቃረቧን የተባበሩት መንግሥታት ባለሙያዎች ገለጹ። በደቡባዊ ጋዛ የምትገኘው ራፋሕ ዛሬ ቅዳሜ ከባድ ውጊያ እና የአየር ድብደባ አስተናገደች። በአፍጋኒስታን ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ቢያንስ 68 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
    10 min
  • የግንቦት 9፣2016 የዓለም ዜና
    -በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሥለ ኢትዮጵያ ፖለቲካዊና የሰብአዊ መብት ይዞታ የሰጡትን አስተያየት ኢትዮጵያ አጥብቃ ተቃወመችዉ።የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ባወጣዉ መግለጫ የአምባሳደሩን አስተያየት «ሐሰት« ና «ተቀባይነት» የሌለዉ በማለት አጣጥሎታል።-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዎላይታ ዞን ደሞዝ ያልተከፈላቸዉ የመንግስት ሠራተኞች ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ያደረጉት ሰልፍ በፖሊስ ኃይል ተበተነ።-የሩሲያዉ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን መንግስታቸዉ ከዩክሬን ጋር የገጠመዉን ጦርነት በድርድር ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን በድጋሚ አስታወቁ።
    11 min
  • የዓለም ዜና፤ ግንቦት 8 ቀን፣ 2016 ዓ.ም
    -ፑቲን፤ ቻይና በዩክሬን ውስጥ ላለው ጦርነት መፍትሄ ለማፈላለግ ስለመሞከርዋ አመሰገኑ። ፑቲን ይህ የተናገሩት ለሁለት ቀናት ጉብኝት መዲና ቤጂንግ ዛሬ ማለዳ ከገቡ በኋላ ነዉ። የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) የታሰሩበትን ሊቀመንበ ጨምሮ የኅሊና እስረኞች ያላቸው ሌሎች ታሳሪዎች ሁሉ ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ ይፈቱ ሲል ጠየቀ።
    በኢትዮጵያ ሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ጥላ ሥር የሚገኙ፤ 367 ሲቪል ድርጅቶች፤ ሕገ መንግሥት እና ሕገ መንግስታዊነት ብሎም የሀብት እና የሥልጣን ክፍፍል፤ ዋነኛ የሀገራዊ ምክክር ጉዳዮች እንዲሆኑ ጠየቁ።
    10 min
  • የግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. ዋና ዋና ዜናዎች
    በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሶዶ ዙሪያ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኞች ደሞዝ እንዲከፈላቸው በአደባባይ ሠልፍ ጠየቁ። ሠራተኞቹ ለሁለት እና ለሦስት ወራት ያህል ደሞዝ ባለማግኘታቸው ከነቤተሰባቸው ለችግር መጋለጣቸውን ተናግረዋል።
    ደቡብ ሱዳን ዉስጥ ከሰባት ሚሊዮን የሚበልጥ ሕዝብ ለአስከፊ ረሐብ መጋለጡን የተመድ አስታወቀ።
    ማዕከላዊ ኬንያ ውስጥ የወረደውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በደረሰው የመሬት መንሸራተት እስካሁን አምስት ሰዎች የገቡበት አልታወቀም።
    የስሎቬኪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት ፊኮ በዛሬው ዕለት በጥይት ተመትተው ሆስፒታል ገቡ። የተኮሰባቸው ተጠርጣሪ በፖሊስ ተይዟል።
    10 min
  • የማክሰኞ፤ ግንቦት 6 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
    አርእስተ-ዜና፦ ሰሜን ሸዋ፥ ቀዎት እና ሞላሌ ወረዳዎች የድሮን ጥቃት፤ ጋምቤላ፥ ኢታንግ የ10 ሰዎች ሕይወት በግጭት ማለፉ ተገለጠ፤ አ.አ፥ ብርቱ የእሳት አደጋ ንብረት አወደመ፤ ራፋ፥ እሥራኤል 76ኛ የነጻነት ቀኗን ባቀረበችበት ቀን ውጊያ በጋዛ፤ ኪዬቭ፥ የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዩክሬንን ድንገት ጎበኙ፤ ሙምባይ፥ ግዙፍ የማስታወቂያ ሠሌዳ ተደርምሶ ቢያንስ 14 ሰዎች ገደለ
    10 min
  • የዓለም ዜና፤ የግንቦት 5 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ሰኞ
    DW Amharic አርሰተ ዜናዎች
    -በኬንያ በተከሰተዉ ዝናብና ጎርፍ ሳብያ ለሁለት ሳምንት ተዘግተዉ የነበሩት ት/ ቤቶች ዛሬ ተከፈቱ። በጎርፍ አደጋዉ በትንሹ 277 ሰዎች ሞተዋል።
    -እስራኤል በጋዛ ከሃማስ ጋር በምታካሂደዉ ጦርነት የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽማለች ስትል ደቡብ አፍሪቃ በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት በእስራኤል ላይ ያቀረበችውን ክስ ግብፅ በይፋ ለመደገፍ ፍላጎት እንዳላት ገለፀች።
    -በአውሮጳና በአሜሪካ የሚኖሩ ከቻይናና ከሆንግ ኮንግ የመጡ ተማሪዎች በቤጂንጉ መንግስት ጫና እየደረሰባቸው መሆኑን አምነስቲ አጋለጠ።
    -በጀርመን በዉጭ ተዋናዮች የሚደርሰዉ የሳይበር ጥቃት መጨመሩን የጀርመን ባለስልጣናት ዛሬ ገለፁ።
    12 min
  • DW Amharic የግንቦት 04 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    ዐቢይ አሕመድ “በማይገባ ነገር መገዳደል ይብቃን” የሚል ጥሪ አቀረቡ።
    ቡሩንዲ አማፂያንን በማሰልጠን እና በማስታጠቅ ጎረቤት ሀገሯ ሩዋንዳን ወነጀለች።
    ደቡብ አፍሪቃ በእስራኤል ላይ የከፈተችውን ክስ ግብፅም እንደምትቀላቀል አስታወቀች።
    የሩስያ ወታደሮች ከዩክሬን ኻርካይቭ ግዛት ተጨማሪ መንደሮች በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ገለጸች።
    9 min
  • DW Amharic የግንቦት 03 ቀን 2016 የዓለም ዜና
    በኢትዮጵያ የ12ኛ ክፍል ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ 12 ቀን 2016 ሊሰጥ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀሪ ምርጫ በሚደረግባቸው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና አፋር ክልሎች፤ ድጋሚ ምርጫ በሚደረግባቸው በጅግጅጋ 2 እና መስቃን እና ማረቆ ምርጫ ክልሎች የዕጩዎችን ምዝገባ እስከ ሐምሌ 6 ቀን 2016 አራዘመ። በአፍጋኒስታን ሦስት ግዛቶች በደረሰ የጎርፍ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 153 መድረሱን የሀገሪቱ መንግሥት አስታወቀ። የጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት በጋዛ ሁለት ሆስፒታሎች በተገኙ የጅምላ መቃብሮች ላይ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ አቀረበ። እስራኤል ራፋሕን ጨምሮ በጋዛ የተለያዩ አካባቢዎች ዛሬ ቅዳሜ ኃይለኛ ድብደባ ፈጽማለች።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…