Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ይህ ፕሮጄክት ኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የትውልድ አገራቸውን ስለምን ለቅቀው እንደወጡ፣ በተለያዩ አገራት የስደት ሕይወት ውስጥ እንደምን እንዳለፉና በታደገቻቸው ሁለተኛ አገራቸው አውስትራሊያ የዳግም ሠፈራ ሕይወት የገጠሟቸውን ተግዳሮችና የተቸሯቸውን መልካም ዕድሎች ለማንፀባረቅ ያለመ ነው። ትረካዎቹ የኢትዮጵያው... more
FAQs about የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ:How many episodes does የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ have?The podcast currently has 41 episodes available.
August 30, 2025ሀገራዊ ቃል ኪዳን "ባለቤቴን ለትዳር ስጠይቃት 'እኔ ሀገሬ ላይ ነው መኖር የምፈልገው፤የአንቺ ሃሳብ ምንድነው? ይህን ማወቅ አለብኝ አልኳት' ዳንኤል አለማርዳንኤል አለማር፤ በቀዳሚው ክፍለ ዝግጅታችን የግለ ታሪክ ወጉ እንደምን በለጋ የወጣትነት ዘመኑ ከእነ ቤተሰቡ ለሀገረ ኬንያ የስደት ሕይወት እንደበቃና እንደተወጣው አውግቷል። በመቋጫው፤ የአውስትራሊ አዲስ የሕይወት ምዕራፍ ጅማሮውን፣ ተግዳሮቶችና መልካም ዕድሎችን አንስቶ ይናገራል።...more23minPlay
August 30, 2025"ለዛሬ መድረሻዬ ሆነኝ የምለው፤ በስደት ካምፕ የነበረኝና የሰንቅኩት ሕይወት ነው" ዳንኤል አለማር"የኃይለ ሥላሴ ቤተሰብ ነው እንዳትነኩት" - ዳንኤል አለማር፤ በግለ ታሪክ ወጉ ገና ለአካለ መጠን ሳይደርስ በለጋ ዕድሜው ከእናትና ወንድሞቹ ጋር እንደምን የትውልድ ሀገሩን ኢትዮጵያን ለቅቆ ለኬንያ የስደት ካምፕ እንደተዳረገና የኢትዮጵያ ስም እንደምን ከእሥር እንዳስለቀቀው ነቅሶ ያወጋል።...more14minPlay
April 03, 2025"ኢትዮጵያውያን መጥተው ድጋፋቸውን ቢቸሩኝ ደስ ይለኛል" ሶሊያና እርሴአንፀባራቂ ኮከብ በመሆን ላይ ያለችው ሶሊያና እርሴ፤ ከትውልድ ከተማዋ ጎንደር፣ ከዕድገት ክፍለ ሀገሯ ትግራይ ተነስታ፤ እንደምን ትንፋሽን የሚያስውጥ፣ የልብ ትርታን ከፍና ዝቅ የሚያደርግ፣ ምትሃታዊ እንጂ ከቶውንም የመድረክ ዕውነታ የማይመስለው፤ ግና ሞገስን የተላበሰ አካላዊ መተጣጠፍ ኮንቶርሽን ተጠባቢ ለመሆን እንደበቃች ታወጋለች። ከኤፕሪል 3 እስከ ሜይ 11 በሜልበርን ከተማ Meat Market ከ Club Kabarett ጋር በመሆን ለሕዝብ ስለምታቀርበው ዝግጅቷ ታነሳለች። የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላትም በሥፍራው እንዲገኙ ትጋብዛለች።...more10minPlay
January 29, 2025"የትም ሀገር ብንሆን ኢትዮጵያን ከውስጣችን ማውጣት አይቻልም፤በአፍሪካ የመጀመሪያው በሆነው የሰርከስ ማዕከል ግንባታ ኢትዮጵያውያን ተሳታፊ ቢሆኑ ደስ ይለኛል"ሶስና ወጋየሁየቀድሞዋ ኢትዮ - ሰርከስ ኮከብ አባልና የኢትዮ - ሰርከስ ኢንተርቴይንመንት ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሶስና ወጋየሁ፤ ከግለ ሕይወት ታሪካቸው ጋር አሰናስለው እንደምን ከሀገረ አውስትራሊያ ወደ ሀገር ቤት በመመለስ፤ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሚሆነውን የሰርከስ ማዕከል በእንጦጦ ፓርክ በመገንባት ላይ እንዳሉ ይናገራሉ።...more22minPlay
January 21, 2025ሶስና ወጋየሁ፤ ከአውስትራሊያ ጥገኝነት ጥየቃ ለክብር ሽልማት መብቃትየቀድሞዋ ኢትዮ - ሰርከስ ኮከብ አባልና የኢትዮ - ሰርከስ ኢንተርቴይንመንት ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሶስና ወጋየሁ፤ እንደምን በሀገረ አውስትራሊያ ከጥገኝነት ጥየቃ ለከፍተኛ የክብር ሽልማት እንደበቁ ያወጋሉ።...more15minPlay
January 09, 2025ሶስና ወጋየሁ፤ ከሜክሲኮ አደባባይ እስከ ሀገረ አውስትራሊያሶስና ወጋየሁ፤ ስርከስ ኢትዮጵያ ካፈራቸው ምርጥ ኮከቦች አንዷ ናቸው። ከሜክሲኮ አደባባይ ውልደትና ዕድገታቸው እስከ አውስትራሊያ የጥገኝነት ጥየቃ ሕይወታቸው ያወጋሉ።...more19minPlay
September 29, 2024" 'ሞቷል' የሚባለው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር እንደተነሳ የምናሳየው የምንሠራቸውን ነገሮች በማሳየትና ተጠያቂም በመሆን ነው" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛውዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ የማኅበረሰብ የበጎ ፈቃደኛ አገልጋይነትን ፋይዳዎች በማመላከት ጥሪዎችን ያቀርባሉ።...more13minPlay
September 29, 2024"በኢትዮጵያዊነታችን እናምናለን የምንል ከሆነ፤ የግል የፖለቲካ አቋማችንና ሃይማኖታችንን ሳናንፀባርቅ ወደ አንድነት እንምጣ" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛውዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ ለማኅበረሰብ አገልጋይነት ገፊና ሳቢ የሆኗቸውን አስባቦች፤ በቀዳሚው ክፍለ ዝግጅታችን ያወጉት 'ከጎንደር እስከ አውስትራሊያ' ግለ ታሪካቸው ተከታይ አድርገው ይናገራሉ።...more15minPlay
September 24, 2024ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ ከጎንደር እስከ አውስትራሊያዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው የወቅቱ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት ናቸው። ከውልደት ሥፍራቸው ጎንደር ከተማ እንደምን ለሀገረ አውስትራሊያ እንደበቁ ግለ ታሪካቸውን አጣቅሰው ያወጋሉ።...more17minPlay
September 09, 2024"መጪው ዓመት ሁላችንም የምንመኘውን የምናገኝበት አዲስ ዓመት እንዲሆንልን ምኞቴ ነው" ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃናተዋናይ፣ ፀሐፌ ተውኔት፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና፤ የግለ ታሪክ ወጉን የሚቋጨው የባሕር ማዶኛ የጥበብ ባለሙያዎች የሚገጥማቸውን ተግዳሮቶች በማንሳትና ለአዲሱ ዓመት 2017 ያለውን መልካም ምኞት በመግለፅ ነው።...more17minPlay
FAQs about የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ:How many episodes does የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ have?The podcast currently has 41 episodes available.