Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ይህ ፕሮጄክት ኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የትውልድ አገራቸውን ስለምን ለቅቀው እንደወጡ፣ በተለያዩ አገራት የስደት ሕይወት ውስጥ እንደምን እንዳለፉና በታደገቻቸው ሁለተኛ አገራቸው አውስትራሊያ የዳግም ሠፈራ ሕይወት የገጠሟቸውን ተግዳሮችና የተቸሯቸውን መልካም ዕድሎች ለማንፀባረቅ ያለመ ነው። ትረካዎቹ የኢትዮጵያው... more
FAQs about የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ:How many episodes does የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ have?The podcast currently has 38 episodes available.
February 06, 2024ዶ/ር ብሩክ ይርሳው፤ ከድሬዳዋ እስከ አውስትራሊያዶ/ር ብሩክ ይርሳው፤ እንደምን ከአገረ ኢትዮጵያ በጃፓን ዞረው ለአውስትራሊያ ምድር እንደበቁ፤ የትምህርት፣ የሥራ፣ የቤተሰብ፣ ማኅበረሰባዊና መንፈሳዊ ሕይወት ትስስሮሻቸውን አንስተው ያወጋሉ።...more14minPlay
October 22, 2023"ሕይወት የጣለችብኝን ውጣ ውረድ ተወጥቻለሁ፤ ተስፋ ብቆርጥ ኖሮ አልኖርም ነበር፤ አሁን በሁለት እግሬ ቆሜያለሁ" ኢንጂነር ብዕሊ አድሃኖምኢንጂነር ብዕሊ አድሃኖም፤ በአዲስ አበባ አራዳ የዕድገት፣ በሱዳን የስደትና በአውስትራሊያ የሠፈራ ከፊል ሕይወቷን አጣቅሳ በቀዳሚ ሁለት ከፍለ ዝግጅቶች አውግታለች። የመደምደሚያ ግለ ታሪኳ የሚቋጨው በምስጋና ጀምሮ በወደፊት ትልሞቿ ነው።...more15minPlay
October 22, 2023ብዕሊ አድሃኖም፤ ከላጤ እናትነት እስከ ምሕንድስናኢንጂነር ብዕሊ አድሃኖም፤ በቀዳሚው ክፍለ ዝግጅት በለጋ የወጣትነት ዘመን ከአዲስ አበባ - አራዳ ተንስታ፤ የሱዳንን አዋኪ የስደት ሕይወት ገፍታና ለአቅመ ሔዋን ሳትደርስ የመጀመሪያ ልጇን አገረ አውስትራሊያ ውስጥ ለመገላገል እንደምን እንደበቃች አውግታለች። በቀጣዩ ትረካዋ የአውስትራሊያ የሠፈራ ኑሮን ተቋቁማ እንደምን ለምሕንድስና ባለሙያነት እንደበቃች አንኳር የሕይወት ጉዞ ተግዳሮቶችና ስኬቶቿን በመንቀስ ታነሳለች።...more15minPlay
October 19, 2023ብዕሊ አድሃኖም፤ ከአራዳ እስከ አውስትራሊያ"ልቤን ተከትዬ ጥፋት ሠራሁ" የምትለዋ ብዕሊ አድሃኖም ግለ ታሪክ መነሻ ከአዲስ አበባ ዕምብርት አራዳ ነው። አውስትራሊያን ሁለተኛ አገሯ ለማድረግ የበቃችው በለጋ ዕድሜዋ ፈታኙን የስደት ሕይወትን በአገረ ሱዳን ተቋቁማ ነው።...more14minPlay
October 17, 2023ስጦታው በፍቃዱ፤ ከቤተ እምነት እስከ ማረሚያ ቤት በጎ አድራጎትደራሲ ስጦታው በፍቃዱ በአፍላ ዕድሜያቸው ወደ አውስትራሊያ የዘለቁት ነፃ የሃይማኖት ትምህርት ዕድል አግኝተው ነው። አዘላለቃቸው ግና ያለ ቪዛ ነበር።...more19minPlay
October 17, 2023ስጦታው በፍቃዱ፤ ከማይጨው እስከ አውስትራሊያ"ከማይጨው እስከ ሲድኒ" ግለ ታሪክነቱ የደራሲ ስጦታው በፍቃዱ ቢሆንም፤ የተነሳሽነት ግፊትና ዕሳቤዎቹ የፈለቁት ግና ከአንድ የእምነት ተጋሪ ወዳጃቸውና ከሴት ልጃቸው ሊዲያ ነው።...more17minPlay
September 28, 2023"የትም አገር ልኑር ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ ኢትዮጵያዊነት ከደም የሚወጣ አይደለም" ድምፃዊ ኤልያስ "ኪዊ" የማነድምፃዊ ኤሊያስ "ኪዊ የማነ፤ የሙዚቃ ሕይወት ጉዞ ከቀበሌ ተንስቶ የምሽት ክለብ መድረኮች ላይ አላከተመም። ከቶውንም በጦር ትምህርት ቤት ሁርሶ፣ በስደት ሞቃዲሾ፣ በዳግም ሠፈራ ኒውዝላንድና አውስትራሊያ የጥበብ ሙያው እስትንፋስ ሆኖ ዛሬም ድረስ አለ።...more21minPlay
September 25, 2023"ፍቅር ፍርንባዬ ድረስ ነበር የያዘኝ፤ ማሰብና መናገር እስኪያቅተኝ ድረስ" ድምፃዊ ኤልያስ "ኪዊ""የማትፈታህ ሚስት ሙዚቃ ነች" የሚለውና በቀዳሚ ክፍለ ግለ ሕይወት ትረካው ከውልደት እስከ ምሽት ክለብ ጅማሮው ያወጋው ድምፃዊ ኤሊያስ "ኪዊ"፤ ትረካውን የምሽት ክለቡ ከቸረው የጥበብና የፍቅር ሕይወት እስከ ለጥቆ አገር ሲፈር እማኝ አስከ ሆነባትና ዝናን እስካተረፈባት የሶማሊያ ስደት አሻግሮ ያጋራል።...more20minPlay
September 24, 2023ለድቁና ታስቦ ለሙዚቃ መድረክ የበቃው ድምፃዊ ኤልያስ "ኪዊ"ድምፃዊ ኤልያስ የማነብርሃን ዳምጤ በቅፅል መጠሪያ ስሙ "ኪዊ" ተብሎ ይጠራል። ኒውዚላንድ በአንድ ወቅት ጥላ ከለላው ነበረችና የአገረ ኒውዚላንድ መለያ ቅፅል ስምን ይጋራል። ኤልያስ ለመድረክ የበቃው ድምፁን በሙሉቀን መለሰ ዘፈኖች አሟሽቶ፤ በጥላሁን ገሠሠ ቅላፄ ቃኝቶ ነው።...more16minPlay
August 25, 2022"ከሕክምና ወደ ምክር ቤት አባልነት ለመሸጋገር አስቤያለሁ" ሰላም ፈለቀ ተገኝሰላም ፈለቀ ተገኝ፤ ቀደም ባለው የግለ - ሕይወት ትረካዋ እንደምን ከዕድገት ቀዬዋ በቅሎ ቤት ተነስታ ከወላጆቿና ታናሽ ወንድሟ ጋር ለስደት እንደተዳረገችና ወደ አውስትራሊያ ከእነ ቤተሰቧ እንደዘለቀች አውግታለች። ቀጣይ ትረካዋ የአውስትራሊያ ምክር ቤት አባል የመሆን ትልሟ ዙሪያ ነው።...more13minPlay
FAQs about የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ:How many episodes does የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ have?The podcast currently has 38 episodes available.