Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ይህ ፕሮጄክት ኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የትውልድ አገራቸውን ስለምን ለቅቀው እንደወጡ፣ በተለያዩ አገራት የስደት ሕይወት ውስጥ እንደምን እንዳለፉና በታደገቻቸው ሁለተኛ አገራቸው አውስትራሊያ የዳግም ሠፈራ ሕይወት የገጠሟቸውን ተግዳሮችና የተቸሯቸውን መልካም ዕድሎች ለማንፀባረቅ ያለመ ነው። ትረካዎቹ የኢትዮጵያው... more
FAQs about የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ:How many episodes does የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ have?The podcast currently has 38 episodes available.
August 22, 2024ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃና፤ ከወላይታ እስከ አውስትራሊያተዋናይ፣ ደራሲ፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና ከስመ ገነን የተውኔት ተጠባቢዎች አንዱና ተጠቃሽ ነው። በሀገረ አውስትራሊያ ከቤተሰቡ፤ በሀገረ ኢትዮጵያ ከትወና ጋር ተዋድዶና ተዛንቆ አለ።...more16minPlay
August 13, 2024"ለመላ ኢትዮጵያውያን ለአዲሱ ዓመት የምመኘው አንድነትን ነው፤ አንድ ካልሆኑ ዕድገት የለም፤ አንድነት ኃይል ነው" እማማ አኒ ማርሴሩ አታሜይንእማማ አኒ ማርሴሩ አታሜይን፤ ቦርቀው ያደጉባት፣ ፊደል የቆጠሩባት፣ ተኩለው የተዳሩባትንና ልጆች ያፈሩባትን ሀገረ ኢትዮጵያ ለቅቀው ከወጡ የአንድ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ዕድሜ አስቆጥረዋል። የኢትዮጵያ ፍቅረ ነበልባል ግና አሁንም ድረስ ልባቸው ውስጥ ይንቦገቦጋል፤ ትዝታዎቿም ዓመታት ሳያደበዝዟቸው ግዘፍ ነስተው ከአዕምሯቸው ተቀርፀው አሉ።...more18minPlay
July 28, 2024"ለስደት ፍቅሩ የለኝም፤ አውስትራሊያ የመጣሁት አጋጣሚዎች ስላስገደዱኝ ነው፤ ወደ ኢትዮጵያ ሳልመለስ በፊት ወድጄው የኖርኩበት ሀገር ነው" ወ/ሮ ነኢማ ሙዘይን መሐመድወ/ሮ ነኢማ ሙዘይን መሐመድ፤ ለአዕምሮ ሕመምተኞች አገልግሎት ሰጪ የሆነው ይመለከተኛል በጎ አድራጎት ድርጅት መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ናቸው። ከውልደትና ዕድገታቸው እስከ በጎ አድራጎት ድርጅት ምሥረታ ያለ የሕይወት ጉዟቸውን ነቅሰው ይናገራሉ።...more16minPlay
June 21, 2024የስደተኞች ሳምንት 2024፤ ድምፃዊ ኤልያስ የማነ "ኪዊ" - ከአፍሪካ ቀንድ እስከ እስያ ፓስፊክየዓለም የስደተኞች ቀን ከ2001 አንስቶ ወርሃ ጁን በገባ በ20ኛው ቀን ሲከበር፤ አውስትራሊያ ውስጥ ጁን 20ን አካትቶ ከአንድ ቀን መታሰቢያነት ዝለግ ብሎ ከጁን 16 እስከ 22 አንድ ሳምንት ደፍኖ ይከበራል። ይህንኑ አስባብ አድርገን ከሶማሊያ ተንስቶ፣ በኬንያና ኒውዝላንድ አቋርጦ አውስትራሊያ የሠፈረውን ድምፃዊ ኤልያስ የማነ "ኪዊ" ከቀደም የግለ ታሪክ ወጉ ቀንጭበን አቅርበናል።...more20minPlay
June 02, 2024"የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግፎ እዚህ አድርሶኛል፤ ከአውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ የምሻው 'አይዞህ' የሚል የሞራል ድጋፍ ነው" ለማ ክብረትበቀዳሚው ክፍለ ዝግጅት የቀድሞው ዝነኛ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በረኛ ለማ ክብረት፤ ከውልደት እስከ ዕድገት፣ ከቁስቋም የሶስተኛ ክፍል እግር ኳስ ተጫዋችነት እስከ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂነት እንደምን እንደ ደረሰ አውግቷል። በቀጣዩ ትረካው ከሞሪሽየስ ጥገኝነት ጥየቃ እስከ አውስትራሊያ ዳግም ሠፈራ ያለ የሕይወት ጉዞውን ነቅሶ ያወጋል።...more15minPlay
June 02, 2024ለማ ክብረት፤ ከቁስቋም እስከ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን በረኛነትለማ ክብረት፤ በቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እግር ኳስ ባልደረባው ኤርሚያስ ወንድሙ አንደበት "ምናልባትም ከዓለም ምርጥ በረኛ" የተሰኘ፤ ሞሪሽየስ ላይ ከአምስት የመለያ ፍፁም ቅጣት ምቶች አራቱን በማዳን የሀገሩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለድል ያበቃ ስመ ጥር ግብ ጠባቂ ነው።...more16minPlay
May 26, 2024"በእኔ በኩል ቀጣዩ ሕይወቴ አውስትራሊያ ይሁን ኢትዮጵያ አላውቅም" ዳይሬክተር ዐቢይ አየለበአንድ የጀርመን ባለስልጣን "ሰርከስ ኢትዮጵያ ጀርመን ውስጥ ኮካ ኮላ የሚታወቀውን ያህል በልጆች ዘንድ ይታወቃል" የተባለለት ድርጅት ዳይሬክተር የነበረው ዐቢይ አየለ፤ ስለ ጥገኝነት ጥየቃ ውጣ ውረዶችና የአውስትራሊያ ሕይወት ጉዞ ጅማሮው ይናገራል።...more18minPlay
May 26, 2024"ከ30 የሰርከስ ኢትዮጵያ አባላት ውስጥ 15ታችን አውስትራሊያ ጥገኝነት ጠይቀን ቀረን" ዳይሬክተር ዐቢይ አየለየቲአትርና ፊልም ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ፤ በቀዳሚ ክፍለ ዝግጅታችን ስለ ትውልድና ዕድገቱ፣ የቀለም ትምህርትና የጥበብ ዕውቀት ቀሰማውን ከሰርከስ ኢትዮጵያ መቀላቀሉ ጋር አሰናስሎ አንስቷል። በሀገረ አውስትራሊያ የጥገኝነት ጥየቃው ውሳኔውን አስከትሎ ያወጋል።...more15minPlay
May 21, 2024ዐቢይ አየለ፤ ከአዋሬ እስከ አውስትራሊያየቲአትርና ፊልም ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ፤ ከጥበብ ሙያ ጅማሮው ተነስቶ፤ የስደት ጉዞውን አጣቅሶ እስከ አውስትራሊያ የሠፈራ ሕይወቱ ያወጋል።...more14minPlay
May 14, 2024መለስ ሳህሌ፤ ከድሬዳዋ እስከ አውስትራሊያየቀድሞው የSBS አማርኛ አገልግሎት ዋና አዘጋጅ መለስ ሳህሌ፤ ስለ ድሬዳዋ ትውልድና ዕድገቱ፣ የጂቡቲ ስደት ፈተናዎቹና የአውስትራሊያ የሠፈራ ሕይወቱ ያወጋል።...more12minPlay
FAQs about የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ:How many episodes does የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ have?The podcast currently has 38 episodes available.