ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የጥቅምት 4 ቀን 2018 የዜና መፅሔት
    በዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ፣-በሕዳሴ ግድብ ምክንያት ውዝግብ ውስጥ ያሉት ኢትዮጵያ እና ግብጽ ከግድቡ መጠናቀቅ በኋላም መካሰሳቸው መቀጠሉ
    የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ብሪታኒያ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን ጋር ያካሄደው ውይይት ፣ የደሴ ከተማን ህዝብ ያስቆጣው የወጣቷ ተማሪ ግድያ ፣ የቀጠለው የትግራይ ክልል ኃይሎች ተቃውሞ፣ ኃይል መቋረጥ የፈተናቸው የኮሬ ዞን ነዋሪዎች በተሰኙ ርዕሶች ስር የተቀናበሩ ዘገባዎች ይቀርባሉ
    23 min
  • የዐርብ መስከረም 30 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
    በሰሜን ሸዋ ዞን፤ ወራጃርሶ ወረዳ ታጣቂዎች ያደረሱት ጥቃት፤ በአማራ ክልል የልጅነት ልምሻ መከሰትን ተከትሎ የተጀመረዉ ክትባት፤ እንዲሁም ጋና ከዩናይትድ ስቴትስ የሚባረሩ ተገን ጠያቂዎችን ለመቀበል መስማማትዋ እና ያስነሳዉ ተቃዉሞ የዛሬዉ ዜና መጽሔት የሚዳስሳቸዉ ዘገቦቻችን ናቸው።
    13 min
  • የዜና መጽሔት፤ መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም ሐሙስ
    የዜና መጽሔት ከሚያተኩርባቸው ጉዳዮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፥
    የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተመድ ለየፃፈው ደብዳቤ ሕወሓት ምላሽ ሰጠ፤ ለአሽከርካሪዎች ፈተና እየሆነ መጥቷል የተባለው የጊቤ መንገድ የፀጥታ ይዞታ፤ የኢትዮጵያ ምንዛሪ በአፍሪካ ደካማ ከሆኑት 21 ገንዘቦች መካከል አንዱ ነው ተባለ፤ እንዲሁም “የአፍሪካ ቲንከታንክ” ጉባኤ የሚሉት ናቸው ።
    17 min
  • የመስከረም 28 ቀን 2018 የዜና መፅሔት
    ኤርትራና ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ህወሓት) ፣ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጦርነት ለመክፈት በጋራ እየሰሩ ነው ሲል የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሰሰ። መስሪያ ቤቱ ሁለቱ ወገኖች የአማራ ፋኖን እያገዙም ነው በማለት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶንዮ ጉተሬሽ በላከው ይፋ ደብዳቤ አስታውቋል። የደብዳቤው ይዘትና ስለክሱ የተሰጡ አስተያየቶች በዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ተሰናድተዋል።
    22 min
  • ዜጎች ከመንግስት የዘንድሮ ዓመታዊ ዕቅድ ምን ይጠብቃሉ?
    የኢትዮጵያው ፕሬዝዳንት የመንግስትን አመታዊ እቅድ በሚቀጥለው ሰኞ ያቀርባሉ። የህዝብ ተወካዮች እና የሚንስትሮች ምክር ቤቶችም የሚከፈቱት በዚያው ቀን ነው። ለመሆኑ ሰዎች ከመንግስት ዓመታዊ ዕቅድ ምን ይጠብቃሉ?መንግሥት በዓመቱ የትኞቹን ተግባራት ቢከውን ይበጃል?
    4 min
  • የመስከረም 22 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
    የዜና መጽሔታችን በዛሬ ጥንቅሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የከተማ ሥራችንን "ሊያጣጥሉ የሚሞክሩ" ያንሏቸውን "ሀገራት እና ቡድኖች" መንቀፋቸው፤ ከትግራይ ሐይሎች በመነጠል በዓፋር ክልል እየተደራጁ ያሉ ታጣቂዎች ትግራይ ላይ ለመፈፀም ያቀዱት ጥቃት በክልሉ ነዋሪዎች ጥረት ከሽፏል መባሉና የቡድኑ አዛዥ ምላሽ ፤ በኢትዮጵያ የንግድ ባንኮች የብድር ገደብ አለመነሳትና አንድምታው፤ በኢትዮጵያ በታላቁ የስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኙ ዘጠኝ ሀይቆች ሥነ ህይወታዊ ህልውና ፤ በኦሮሚያ ክልል የቱሪዝም ስራውን ውጤታማ ለማድረግ የገበያ ትስስር ማጠናከር እንደሚገባ መጠየቁን የተመለከቱ ዘገባዎች ተጠናቅረዋል።
    23 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…