ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የማክሰኞ መስከረም 20 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
    የዜና መጽሔታችን በዛሬ ጥንቅሩ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይመስሪያቤት የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አመቺነት ኹኔታ "ፈታኝ ነው" ማለቱ ፤ በኢትዮጵያ እየተባባሰ ለሄደው የጥላቻ ንግግር መፍትሔ መጠየቁ ፣ የሱዳን የናይል ወንዝ የጎርፍ ሥጋት እና የኢትዮጵያ መንግሥት ምላሽ ፣እና በአሜሪካ የሚደገፈው የጋዛ የሰላም እቅድ እና አንድምታው በቅደም ተከተል ይተነተናሉ።
    19 min
  • የመስከረም 16 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በዜና መጽሔት ጥንቅራችን፤የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ያደረጉትን ውይይት የተመለከተ፣ የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ እንዲሁም በጃፓን ቶኪዮ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በተመዘገበው ዝቅተኛ ውጤት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምላሽን የተመለከቱ ሶስት ዘገባዎች ይቀርባሉ።
    14 min
  • የሐሙስ መስከረም 15 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
    -ግብጽና ኢትዮጵያ ለበሶማሊያ ምድር እድል አልሰጥም ሲሉ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሰሞኑን ተናግረዋል።
    -በፍትህ ተቋማት ውስጥ የሚስተዋሉ ብልሹ አሠራሮችን ማስተካከል እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ በክልሉ በተካሄደው የዳኝነትና የፍትህ ዘርፍ ተቋማት ጥምረት ጉባዔ ላይ አሳስበዋል። እነዚህና
    ትግራይ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚሰሩ ስምንት ሲቪል ማሕበራት ስጋትና ጥሪን
    እንዲሁም የተመድ ጠቅላላ ጉባኤና ፕሬዝደንት ትራምፕ ንግግር የሚያስቃኙ ቅንብሮችም በዛሬው የዜና መጽሔት ተካተዋል።
    19 min
  • የመስከረም 14 ቀን 2018 የዜና መፅሔት
    ጦርነትና ለወራት የተቋረጠ ሰብአዊ ድጋፍ የተፈናቃዮች አቤቱታ፤ በትግራይ ክልል የቀጠለው የተፈናቃዮች ችግር ፤ በጠለምት ወረዳ በዝናብ እጥረት ለችግር የተጋለጡ ወገኖች፤ የኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት ለምን ዝቅተኛ ሆነ? እንዲሁም በቶሮንቶ ካናዳ የተካሄደውን የቢቂላ ዕውቅናና ሽልማት የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል የዜና መጽሔት
    21 min
  • የማክሰኞ መስከረም 13 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔት
    ዜናዉን የሚለጥቀዉ የዜና መፅሔት ጥንቅራችን ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የሚደረጉ ግጭቶች ሐገሪቱ ከቱሪዝም ማግኘት የሚገባትን እንዳታገኝ ማወኩን የሚቃኘዉን ዘገባ ያስቀድማል።የህወሓት ሊቀመንበር በድጋሚ በፌደራል መንግሥቱ ላይ ያሰሙት ወቀሳ፣ ሰሜን ወሎ የሠፈሩ ተፈናቃዮች የገጠማቸዉ ችግርና የመቅደላ ዩኒቨርስቲ የመካነ ሠላም ካምፓስ ዘንድሮ ማስተማር ሊጀምር ነዉ መባሉን የሚዳስሱ ዘገቦች አሉት።
    19 min
  • የመስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በዜና መጽሔት ጥንቅራችን፤
    -ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚታየዩ የተለያዩ የፀጥታ ችግሮች መፍትሄ እያገኙ ይሆን?
    -በሆሮ ጉዱሩ በአቤዶንጎሮ ወረዳ የታጣቂዎቸ ጥቃት
    -የትግራይ ትውልድ ፓርቲ -' ውድብ ወለዶ ትግራይ' የተሰኘዉ አዲሱ የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲ
    በአዲስ አበባ ጉዳት ያደረሰው ጎርፍና መንስኤዉ የተሰኙት ርዕሶች ይተነተናሉ።
    17 min
  • የመስከረም 9 ቀን 2018 የዜና መፅሔት
    የዓለም ዜና ቀዳሚው ዝግጅታችን ነው። ዜናውን የሚከተለው የዜና መጽሔት ስለኢትዮጵያ የወደብ ጥያቄ የዓለም አቀፍ ሕግ ምን ይላል? በሚል ርዕስ የተጠናቀረውን ዘገባ ያስቀድማል ከባድ ዝናብ በዋግኽምራ በሰብል ላይ ባለደረሰው ጉዳት ላይ የሚያተኩረው ዘገባም አለን።
    9 min
  • የመስከረም 7 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የዜና መጽሔት አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ መቀጠሏ፤ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች በደቡባዊ ትግራይ ዞንና በሌሎች አካባቢዎች የመብት ጥሰት ተፈጽሟል ማለታቸው፤ በእሥር ላይ የሚገኙት አቶ ክርስቲያን ታደለ ሕመም እንደጠናባቸው መገለጹ፤ ነዋሪዎች እንዲፈናቀሉ ያስገደደው አዲስ አበባ ላይ የተከሰው የመሬት መንሸራተት እንዲሁም የአረብ ሃገራት መንግሥታት አስቸኳይ ጉባኤ ውሳኔና አንድምታውን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል።
    22 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…