ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የመስከረም 6 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    ኢትዮጵያ ዉስጥ ሰላም ሥለሚሰፍንበት ሁኔታ የሚነጋገር ጉባኤ አዲስ አበባ ዉስጥ መጀመሩን
    አማራ ክልል የሚደረገዉ ግጭት የመማር-ማስተማሩን ሒደት አሁንም እያወከዉ መሆንኑ
    የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሾፍቱ አጠገብ ሊያስገነባ ሥላቀደዉ ግዙፍ አዉሮፕላን ማረፊያ የተነጋገረ ስብሰባ
    15 min
  • የመስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በዜና መጽሔት ጥንቅራችን፤
    ህዝባዊ ሓርነት ትግራይ ህወሓት በፌደራል መንግሥት ላይ የሰነዘረዉ ክስ
    ግዕዝ ቋንቋ በአማራ ክልል ስርአተ ትምህርት ዉስጥ መካተቱ ያስነሳዉ ተቃዉሞ
    ኢትዮጵያ እና ኬኒያ ድንበር ላይ የሚታዩ ግጭቶችን ለመፍታት መስማማታቸዉ ርዕሶችን በስፋት እንዳስሳለን።
    እንዲሁም ለትምህርት ጥራት ፈተና መፍትሄው የቱ ጋር ነው? የተሰኙት ርዕሶች ይተነተናሉ።
    16 min
  • የመስከረም 2 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሄት
    በዛሬው የዜና መጽሄት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቀሩት 5 የሥራ ወራት ስራውን አከናዎኖ ይጨርስ ይሆን?«ኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘት አለባት » ሲል በትግራይ የሚንቀሳቀሰዉ ተቃዋሚዉ ፓርቲ - ትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ የመንግሥትን አቋም መደገፉን፤የምክክር ኮሚሽንኑ የሰሜን አሜሪካ ውይይት እና የሕግ ባለሙያ አስተያየት እንዲሁም ነገ ቶክዮ ላይ የሚጀምረዉ 20ኛዉ የዓለም የአትሌቲክስ ሻንፒዮና የሚዳስሱ ርዕሶችን አካቷል።
    16 min
  • የመስከረም 1 ቀን 2018 ልዩ የበዓል ዝግጅት
    ዓለም ዜና ቀጥሎ በሚቀርበዉ ልዩ የአዲስ አመት ዝግጅታችን፤ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች አዲስ ዓመትን አስመልክቶ የደረሱንን ዘገባዎች እናደምጣለን። በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ከአገር ቤት ርቀዉ የአዲሱን ዓመት እንዴት እያከበሩት ነዉ፤ ዘገባ ይኖረናል።
    --እነዚህን ዘገባዎቻችን በሙዚቃ እያዋዘን በፊስቡክ የቀጥታ ስርጭት የሚከታተሉንን የዶቼ ቬለ ቤተሰቦች አስተያየቶችን በቀጥታ ስርጭት እናስደምጣለን
    26 min
  • የጳጉሜ 5 ቀን 2017 ዓ.ም የዜና መፅሄት
    DW Amharic- የዛሬው የዜና መፅሔት ጥንቅራችን፣-የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ምርቃት፣ የወደፊት አጠቃቀምና አስተዳደርን የተመለከተ ፤በአዲሱ ዓመት ዋዜማ የተፈናቃዮች ኑሮንና ሸመታን የሚዳስሱ ከደ,ሴና አሶሳ ሁለት ዘገባዎችን፣ በምዕራብ ወለጋ ዉስጥ የተዛመተዉ የወባ በሽታ ሰዎች መግደልና ማሳመሙን የሚመለከቱ ዘገባዎችን አካቷል።
    21 min
  • የጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ/ም የዜና መጽሔት
    በተለያየ ጎራ የተሰለፉ ኢትዮጵያውን በሙሉ ልብ እንደሚስማሙበት የሚናገሩለት ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ መሠረቱ በተጣለ በ14ኛ ዓመቱ በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቋል። በገንዘባችሁ፤ በሙያና ላባችሁ የየበኩላችሁን አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ ሁሉ እንኳን ደስ ያላችሁ! ዛሬ የግድቡን ምርቃት ምክንያት በማድረግ የዜና መጽሔት ትኩረቱን በዚህ ላይ አድርጓል፤ የሕዝብ አስተያየትንም አካተናል፤ የታላቁ ኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስከያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮንም አነጋግረናል።
    21 min
  • የጳጉሜ 3 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በዛሬው የዜና መጽሔት
    በከባባቢ አየር ለውጥ ላይ የሚመክረው በአዲስ አበባ በመካሔድ ላይ የሚገኘው የአፍሪካውያን ሁለተኛ ጉባኤ
    የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍለጋ፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት “የሚታይ የጦርነት ደመና አለ” ማለታቸው
    እንዲሁም በአማራ ክልል በወጣት ሴቶች የሚከበሩት አሸንድዬ እና ሻደይ በዓላትን የተመለከቱ ዘገባዎች ይቀርባሉ።
    17 min
  • የነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የዜና መጽሔት ዝግጅታችን፤
    ከውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ከዶክተር ሃብታሙ ኢተፋ ጋር የተካሄደ ቃለ ምልልስ
    ለትግራይ የመንግስት ሰራተኞች ውዝፍ ደሞዝ ክፍያ 20 ቢልዮን ብር ያስፈልጋል መባሉ
    በባቲ ከተማ የተጣሉት የሰዓት እላፊ ገደቦች እንዲሁም
    በምስራቅ ሸዋ ዱግዳ ወረዳ የታጣቂዎች ጥቃት፤ የተሰኙ ርዕሶችን ይቃኛል
    17 min
  • የዜና መጽሔት፤ ነሐሴ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ሐሙስ
    በመጽሔተ ዜና ከምናስተነትናቸው ዘገባዎች፦«የመውሊድ በዓል ሃይማኖታዊና ባሕላዊ እሴት» የሚለው ርዕስ ቀዳሚው ነው። «ትግራይ ክልል ከጦርነቱ በኋላ የመሠረተ ልማት ዳግም ግንባታ አለመኖር ዳፋው» የሚለው ይከተለዋል ። ዜና መጽሔቱን የምናሳርገው «አሳሳቢው የኢትዮጵያ ስደተኞች የምስራቅ በር ተሰዳጆች» በሚለው ዘገባ ነው ።
    13 min
  • የነሐሴ 28 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ድባጢ ወረዳ የታጣቂዎች እንቅስቃሴ
    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ እስመለዓለም ምህረቱ ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን አሳወቁ። ለሁለት ዓመት ከመንፈቅ ገደማ ብሔራዊውን ባንክ የመሩት አቶ ማሞ በተለያዩ ኃላፊነቶች ካገለገሉበት የመንግሥት ሥልጣን እንደሚለቁ ያሳወቁት በግል የኤክስ ገጻቸው ባሠራጩት የስንብት ደብዳቤ ነው።
    ኢትዮ ቴሌኮም ለአክሲዮን ድርሻ ለገዙት ደንበኞቹ ባለቤትነታቸው መረጋገጡን ማሳወቅ ጀመረ
    እስራኤልን በዘር ማጥፋት ወንጀል የክሰሰው አለማቀፍ የዘር ማጥፋት ወንጀል ምሁራን ማህበር
    20 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…