ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የዜና መጽሔት፤ ነሐሴ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ማክሰኞ
    የዜና መፅሔት ጥንቅራችን፣ ትግራይ ክልል የሥልጣን ሽም የጫረዉነዉ በተባለ ግጭት መኾኔ ከተማ ዉስጥ ሰዎች መቁሰላቸዉ ተሰምቷል።አማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን በስርቆት ምክንያት የኤሌክትሪክ ኃይል ሲቋረጥ፣ ጋምቤላ ክልል ደግሞ የነዳጅ እጥረት ነዋሪዎችን እያማረረ ነዉ።ሩሲያና ዩክሬን የገጠሙትን ጦርነት ለማስቆም የሚደረገዉ ዲፕሎማሲ ጥረትን የሚቃኝ ዘገባም አለዉ።ዜና መፅሔቱ የዕዉቁ ኢትዮጵያዊ አርቲስት የደበበ እሸቱን ሥርዓተ-ቀብር በሚቃኘዉ ዘገባ ያሳርጋል።
    21 min
  • የነሐሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    ጋዜጠኞችን «ከሕግ ውጪ መሰወር በአስቸኳይ ይቁም» ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማሕበር መጠየቁ
    መቐለን ጨምሮ በትግራይ ከተሞች የተስፋፋዉ ወንጀል አሳሳቢ ሆንዋል ተባለ
    በማኅበረሰቡ እልባት የሚሻው የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ግጭት
    በአማራ ክልል ከ 3.6 ሚሊዮን በላይ የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ ተቻለ መባሉ
    18 min
  • DW Amharic የነሐሴ 09 ቀን 2017 የዜና መጽሔት
    የአሜሪካ መንግሥት ስለ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ያወጣው ዘገባ፣ በጠለምት ወረዳ በመኖ እጥረት ከ3ሺህ በላይ እንስሳት መሞታቸውን ወረዳው አስታወቀ፣ የናይሮቢ እና አዲስ አበባ ቀጥታ የአውቶብስ ትራንስፖርት ውጥን
    17 min
  • የነሐሴ 8 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መፅሔት
    የዜና መፅሔት ጥንቅራችን የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ የግብፅ ፕሬዝደንት ለሰጡት አስተያየት የአብንን ተቃዉሞ የሚቃኘዉን ዘገባ አስቀድሞ ከሕዳሴ ግድብ የተመረተዉን የአሳ መጠን የሚያስተዋዉቀዉን ያስከትላል።ዜና መፅሔቱ የትግራይ ተፈናቃዮች የገጠማቸዉ ሥነ-ልቡናዊ ቀዉስና ከፊል ቢሾፍቱ ከኃይለኛ ዝንብና አዉሎ ነፋስ በኋላ መብራት ማጣቷን የሚያወሱ ዘገቦችም አሉት
    17 min
  • የነሐሴ 7 ቀን 2017 የዜና መፅሔት
    የኢትዮጵያ ብሔራዊ መልሶ ማቋቋም ኮሚሽን ከ65 ሺህ በላይ የቀድሞ ተዋጊዎች ከህዳር አንስቶ ከኅብረተሰቡ ጋር መቀላቀላቸውን አስታውቋል። በመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ሰዎች በግጭት ወቅት ለተቃጠሉ ቤቶቻቸው ግብር እንድንከፍል ተጠይቀናል ሲሉ ብሶታቸውን ተናገሩ። የህዳሴ ግድብ መጠናቀቁ ከተገለጸ በኋላ ግብጽ የምታነሳው ተቃውሞ ፣አሸከርካሪዎች በተለያዩ አቅጣጫዎች ሲጓዙ ከደኅንነት ችግር አንስቶ እስከ ሕገ ወጥ የኮቴ ክፍያ ድረስ የሚገጥማቸው ፈተናዎች እንዲሁም የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካን ዋና ከተማ ዋሽንግተን ዲሲ ፖሊስ ተግባራዊ ያደረጉት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ
    ዜና መጽሔት የሚመለከታቸው ጉዳዮች ናቸው
    22 min
  • የነሐሴ 6 ቀን 2017ዓ/ም የዜና መጽሄት
    DW Amharic-የዛሬው የዜና መፅሔት፣ኦሮሚያ ክልል የመንገደኞች እገታ መቀጠሉን፣ አማራ ክልል በተለይ ደቡብ ወሎ ዞን የሰፈሩ ተፈናቃዮች ለረሐብ መጋለጣቸዉን፣ ትግራይ ክልል የሚደረገዉ ሕገ ወጥ የወርቅ ማዕድን ቁፋሮ ያደረሰዉ ጉዳት፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽንና የሲቪክ ድርጅቶች ረቂቅ ሕግ፣ የዩክሬን ጦርት፣የአሜሪካና የሩሲያ መሪዎች የዉይይት ቀጠሮና የአዉሮፖችን ጭንቀት የሚቃኝ ዝግጅት ተጠናቅሮበታል።
    21 min
  • የነሐሴ 5 ቀን 2017 የዜና ፅሔት
    በትግራይ ክልል ኃይሎችና ራሱን ከትግራይ ኃይሎች ነጥሎ በአፋር ይንቀሳቀሳል በተባለው ቡድን መካከል ተነሳ የተባለው ግጭት ፣ ካለፈው ሐሙስ አንስቶ የህዝብ የመጓጓዣ አገልግሎት መስጫዎች መንቀሳቀስ ማቆማቸው በጎጃም አካባቢዎች ያስከተላቸው ችግሮች ፣ብልጽግና ፓርቲ ባለፈው ሳምንት ያወጣው መግለጫና የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየት እንዲሁም ፣ ነዳጅ በውድ ዋጋ ለመግዛት ተገደናል የሚሉ ሾፌሮችና የመኪና ባለቤቶች ሮሮ በዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን የሚያስቃኘን ጉዳዮች ናቸው።
    18 min
  • የነሐሴ 2 ቀን 2017 የዜና መፅሔት
    የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ መንግሥትን በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ እንዲቀይሩ ጥሪ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከትግራይ ክልል 60 ሺህ ወጣቶች መሰደዳቸው፤ በያዝነው ነሐሴ ወር ከመደበኛ በላይ የዝናብ ስርጭት የጎርፍ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል መገለጹን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል የዜና መጽሔት፤
    16 min
  • የነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የዜና መፅሔት ጥንቅራችን ኢትዮጵያ ዉስጥ በኤሌክትሪክ ኃይል ላይ የሚደረገዉ ጭማሪ ተገቢ ነዉ መባሉን ከሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ጋር የሚቃኘዉን ዘገባ ያስቀድማል።ሲዳማና ኦሮሚያ ክልልሎች ድንበር ላይ የተደረገዉ ግጭት ሰበብ የግዛት ይገባኛል እንዳልሆነ መነገሩ፣ኦሮሚያ ክልል የአዋሽ ወንዝ ሙላት ሰዉ ማፈናቀሉ፣ ሰሜን ወሎ ደግሞ ለዝናብ ሲፀለይ፣ ዝናብ ተፈናቃዮችን መጉዳቱን የሚቃኙ ዘገቦች በተከታታይ ተስምተዉ ያሳርጋል።
    17 min
  • የሐምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በአሮሚያ እና ሲዳማ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በተነሳ ግጭት ሁለት ሰዎች ተገደሉ
    ወጣቶች ሞት እንዳለ እያወቁ ለምን በአደገኛ የጉዞ መስመር ይሰደዳሉ?
    የሕገ-ወጥ ስደት አስከፊ ገጽታ - ከሞት መለስ ያሉ የስቃይ ምዕራፎች
    ኢትዮጵያዊያንን ለአደገኛ የፍልሰት ጉዞ የሚዳርጓቸው ገፊ ምክንያቶች ምንድናቸው ?
    21 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…