ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የሐምሌ 15 ቀን፣ 2017 ዓ.ም ዜና መጽሔት
    የዜና መጽሔታችን በዛሬ ጥንቅሩ በደቡባዊ ትግራይ የስልጣን ሹም ሽሩ ያስከተለው ውዝግብ ፣በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በጋምቤላ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈጠረው ግጭት የበርካታ ሰዎች ህይወት መንጠቁ ፣ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ የተሰጡ ሰሞንኛ አስተያየቶች እና የግድቡ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ምላሽ ፣ የብሄራዊ ባንክ ያለ ማስያዣ ብድር የሚሠጥበትን አሠራር ለመከለስ ማቀዱ እንዲሁም በርካታ ሃገራት በጋዛ ሰርጥ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ያስተላለፉትን ጠንካራ ጥሪ የተመለከቱ ዘገባዎች ተጠናቅረውበታል።
    21 min
  • የሐምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በዛሬው የዜና መፅሔታችን
    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለቀጣዮ ምርጫ የጀመረው ቅድመ ዝግጅት
    የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ በመጪው ምርጫ ለመሳተፍ ያስቀደማቸው ቅድመ ሁኔታዎች
    የኤርትራው ፕረዚደንት ኢሳያስ አፍወረቂ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤
    በጎደቤ ብሔራዊ ፓርክ እየደረሰ ስላለው ውድመት የተጠናቀሩ ዘገባዎች ይቀርባሉ።
    17 min
  • የሐምሌ 11 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በዜና መጽሔት ዝግጅታችን
    -ዝቅተኛ የሠራተኞች የደሞዝ ወለል ተግባራዊ እንዲሆን መጠየቁ
    -የበረታው “የሽፍቶች” ጥቃት በምዕራብ ሸዋ ዞን ጨሊያ ወረዳ እንዲሁም
    በባሕር ዳር ከተማ የሰዓት እላፊ ገደብ በከፊል መነሳቱ፤ የተሰኙ ርዕሶች ይተነተናሉ።
    15 min
  • የሐምሌ 9 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ዛሬ በመቐለ ከትግራይ ክልል መሪዎች እና ሌሎች አካላት ጋር ተወያይተዋል። ይህና -ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የትራምፕ አስተያየትና ኢትዮጵያ ፣
    በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎርፍ 81 ሺህ ሰዎችን ማፈናቀሉ፤ በደቡብ ወሎ ዞን ከ600 ሺህ በላይ ወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት ተመዝግበዋል መባሉ
    በኦሮምያ ክልል በዱር እንሰሳት በተለይም የደጋ አጋዘን ላይ የሚካሄደው አደን የዱር እንሰሳቱን ቁጥር እንዳያመናምን ማሳሰቡ ፣
    22 min
  • የሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    -የተጠናቀቀው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ "በዲፕሎማሲው መስክ ውጤታማ የሥራ ስኬት ያስመዘገበችበት" እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጹ
    - በትግራይ የግብርና ምርት ለማሳደግ ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም ማዳበርያ ጨምሮ የግብርና ስራ ግብአቶች ወደ ገበሬ ለማድረስ የነዳጅ እጥረት ፈተና ሆንዋል መባሉ።
    -የቀይ ባሕር አፋር በኢትዮጵያ ያካሄደው ሕዝባዊ ጉባኤ እና
    ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፔትሪየት የተባለዉን የአየር መከላከያ ስርዓት ለዩክሬን እንደምትልክ መናገራቸዉ ዜና መጽሔት የሚያስተነትናቸቸው ናቸዉ።
    18 min
  • የሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የዜና መፅሔት ጥንቅራችን የትግራይ ክልል የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን «አሥጊ» ያለችዉ ዉዝግብ የሚቃለልበትን ብልሐት የሚያፈላልግ የሽምግሌዎች ቡድን ጠቅላይ ሚንስትር ዓሕመድን እንዲያነጋግር ማቀዷን የሚያወሳዉን ዘገባ ያስቀድማል። የኢትዮጵያና የሩሲያ የመገበያያ ገንዘቦች ብርና ሩብል የቀጥታ ልዉዉጥ ወይም ምንዛሪ መጀመራቸዉን የሚቃኘዉ ዘገባ ተከትሎ፣ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ተጨማሪ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ጋምቤላ ክልል መግባታቸዉን የሚያዳስሰዉ ዘገባ ያስልሳል።
    13 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…