ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • የማክሰኞ ነሐሴ 27 ቀን፣ 2017 ዓ.ም ዜና-መጽሔት
    በዋግኸምራ ዞን አስተዳደር ከ4,000 በላይ አርሶ አደሮች በተፈጥሮ አደጋ መጎዳታቸው፤ የአረና ትግራይ አዲስ የጊዜያዊ አስተዳደር ጥሪ፤ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ዓመታት እንደ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ትልልቅ መሠረተ ልማቶችን መገንባት ትጀምራለች እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ «የቀይ ባሕር ስህተት ይታረማል» ማለታቸውን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል የዜና መጽሔት
    19 min
  • የነሐሴ 26 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የዜና መጽሔት ጥንቅራችን
    በትግራይ ደቡባዊ ዞን እየበረታ የመጣዉ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ፣ በደቡብ እና ሰሜን ወሎ የደሞዝ ጭማሪ ዜና ያስከተለዉ የኑሮ ዉድነት ፣ የምክክር ኮሚሽኑ በዋሽግተን ዲሲ ያካሄደው የምክክር መድረክ ፣ ተገድቦ የቆየው የብድር አቅርቦት እና የቀጣዩ ዓመት ዕቅድ እንዲሁም የሻንጋይ የትብብር ድርጅት የመሪዎች ጉባዔ እና ፋይዳዉ የተሰኙትን ርዕሶች በስፋት ያስቃኘናል።
    21 min
  • DW Amharic የነሐሴ 22 ቀን 2017 ዜና መጽሔት
    በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን በደረሰ የመሬት ናዳ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ ድንቅነሽ ወይም ሉሲ እና ሰላም ቅሪተ አካላት ቼክ ሪፐብሊክ ፕራግ ውስጥ ለእይታ በቅተዋል። ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢ ተፈናቅለው በደቡብ ወሎተሁለደሬ ወረዳ ጃሪ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚገኙተፈናቃዮች መኖሪያ ቤታችን ፈርሶ ከዝናብ እና ብርዱ ጋር መኖር ብንለምድም ወባና እና የተቅማጥ በሽታ ጤና ነሳን ይላሉ፡፡ በኖርዌይ የትውልደ ኢትዮጵያዊት ማህበራዊ ሰራተኛ ግድያ፤ በኢትዮጵያ ጦርነት እንዲቆምና የሽግግር ጊዜ እንዲመቻች የቀረበ ጥሪ
    22 min
  • የነሐሴ 21 ቀን 2017 ዜና መፅሔት
    በዛሬው ሥርጭት የኢትዮጵያ የሽግግር ፍትህ ትግበራ ከምን እንደደረሰ የሚያጠይቀውን ጨምሮ አራት ዜና መጽሔቶች ተዘጋጅተዋል። ሣምንታዊ የከኢኮኖሚው ዓለም እና የሣይንስ እና ቴክኖሎጂ መሰናዶዎች ሰዓታቸውን ጠብቀው ይቀርባሉ
    16 min
  • የነሐሴ 19 ቀን 2017 ዓ.ም የዜና መፅሔት
    ዜና መጽሔት ጥንቅራችን፤
    አሳሳቢዎቹ እገታ እና አስገድዶ የመሰወር ድርጊቶች በኢትዮጵያ
    በኦሮምያ ክልል አርሶ አደሮችን የሚያግተው ማነው?
    “የደመወዝ ማሻሻያ ይደረጋል” መባሉና በአማራ ክልል የፈጠረው የዋጋ ጭማሪ
    “ የኢትዮጵያን ይግዙ “ የተባለዉ ፕሮጀክት ተስፋ እና ተግዳሮት የተሰኙ ርዕሶችን በስፋት እንመለከታለን።
    19 min
  • የዜና መጽሔት፤ ነሐሴ 16 ቀን 2017 አርብ
    የዜና መፅሔት ጥንቅራችን፣ የኢትዮጵያ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ተከታታይ የሰላም ጉባኤዎች ለማድረግ ማቀዱን የሚቃኘዉን ዘገባ ያስቀድማል።የኤሌክትሪክ ኃይል መቆጣራረጥ የኮምቦልቻ ከተማ ባለ ፋብሪካዎችን ሥራ ማስፈታቱን የሚቃኘዉ ተክትሎ፣ የዘንድሮዉ የአሽንዳ በዓል በትግራይ ክልል መከበርን የሚወሳዉ ያሰልሳል።
    16 min
  • የነሐሴ 15 ቀን 2017 የዜና መፅሔት
    እስካሁን የት እንዳሉ ያልታወቀው የጋዜጠኞች ጉዳይ፤ በግጭት ወቅት የሚበዛው የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎት እና ፈተናው ፤ ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን በባሕር ዳር ከዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር ያደረገው ውይይት እንዲሁም ውግዘት የገጠመው ትራምፕ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ችሎት ዳኛ ላይ የጣሉትን ማዕቀብ የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል የዜና መጽሔት
    18 min
  • የነሐሴ 14 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የሲቪል ማኅበራት አስተዳደር የሚያረቀቀዉ ፤ ሕግ ላይ የቀረበው ስጋት
    ስለደመወዝ ጭማሪው የህዝብ አስተያየት
    11 ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት መሠረቱ
    የትግራይ ክልል ኃይሎችን ለመሸምገል የተደረገው ጥረት
    19 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…