ዜና መጽሔት

ዜና መጽሔት

Download on the App Store

ዜና መጽሔት episodes

  • አዲስ መፅሐፍ በሀረርጌ ኦሮሞ ታሪክ ፣ ባህል እና እሴት ላይ
    በሀረርጌ ኦሮሞ ታሪክ ፣ ባህል እና እሴት ላይ በማተኮር የተዘጋጀው መፅሐፍ በሀረር ለምረቃ በቅቷል። በኦሮሚያ ጥናት እና ምርምር ኢንስቲቲዩት በምስራቅ ሀረርጌ አካባቢ በሚኖሩ የሀረርጌ ኦሮሞዎች ታሪክ ላይ የተዘጋጀው መፅሀፍ ማህበረሰቡ ታሪኩን እንዲያውቅ ከማድረግ ባለፈ ትክክለኛውን ታሪክ ለመሰነድ ያስችላል ተብሏል ።
    4 min
  • የሕዳር 12 ቀን 2017 የዜና መጽሔት
    በትግራይ 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ማሕበረሰቡ ለመቀላቀል ትጥቃቸው ፈትተው ወደ ስልጠና ማዕከላት የሚገቡበት መረሃ ግብር ዛሬ ተጀመረ።ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ውድቅ እንዲደረግ ተጠየቀ።በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች በንጹሃን ላይ ይፈጸማል ያለው ጥቃት እንዲቆም የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ጠየቀ። ሀዋሳ በህጋዊ ማደያዎች ነዳጅ ማግኘት ሲበዛ አዳጋች ነው፡፡ በከተማው የነዳጅ አቅርቦት የለም ፡፡
    18 min
  • የኅዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    የዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ከሚያስቃኘን ጉዳዮች መካከል
    -የደራ ወረዳው አሰቃቂ ግድያና አላባራ ያለው ውስብስብ ቀውስ
    -የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታትና ወደ ማዕከል የማስገባት ሥራ ሊጀመር ነው
    -የርህራሔ ጠብታ ያለታየበት ጭካኔ
    -የአውሮጳ ኅብረት የኅዳር ወር ስብሰባ ትኩረት ይገኙበታል
    22 min
  • የዜና መጽሔት፤ ኅዳር 09 ቀን 2017 ዓ.ም
    አብዛኛዎቹ የመርካቶ ሱቆች በተቃውሞ ምክንያት ዛሬ ተዘግተው ውለዋል
    የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አጠቃላይ ጉባኤ ከመጥራቱና አዳዲስ መሪዎችን ከመምረጡ አስቀድሞ ስድስት ፓርቲዎች የጉባኤውን ውጤት እንደማይቀበሉ ተናግረዋል።
    በትግራይ በአንድ ሳምንት ውስጥ 17 ሺህ ሰዎች በወባ መያዛቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል።
    7ኛው ዙር የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዘመቻ
    እነዚህ በዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ዘገባዎች ትኩረት ናቸው።
    19 min
  • ለ13 አንጋፋ ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙሃን ባላሙያዎች እውቅና ተሰጠ
    ታላላቆችን እናክብር በሚል በ1960ዎቹና በ1970ዎቹ አገራቸውን ያገለገሉ ቀደምት ጋዜጠኞች እና አንጋፋ የመገናኛ ብዙሃን ባላሙያዎችን በዛሬው ዕለት ሽልማት እና ምስጋና ተችሯቸዋል።በዚህ መርሀ- ግብር እንደሚመሰገኑ ከተመረጡ በኃላ ህይወታቸውያለፈውን የሚድያ ሰው ሙልጌታ ወልደሚካኤልን ጨምሮ ለ13 የቀድሞ ጋዜጠኞች ዕውቅ ተሰጥቷል።
    3 min
  • በኦሮሚያ፤ተፋላሚዎች ወጣቶችን በግዳጅ ለውትድርና ይመለምላሉ ተባለ
    በኦሮሚያ ክልል የሚካሄደውን ግጭት ተከትሎ ተፋላሚዎች ወጣቶችን በግዴታም በውዴታም በስፋት ለውትድርና እየመለመሉ መሆኑን የክልሉ አንዳንድ ነዋሪዎች ገልፀዋል።፡ከተለያዩ አከባቢዎች አስተያየታቸውን ለዶቼ ቬለ የሰጡ ነዋሪዎች እንዳሉት እየከፋ መጥቷል ያሉት ይህ መሰሉ ተግባር ለነዋሪው አስጨናቂ ጉዳይ ሆኗል።
    4 min
  • የኅዳር 6 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዜና መጽሔት
    የዜና መጽሔት ርዕሰ ጉዳዮች
    እርዳታ ካገኘን 2 ዓመት ሆነን” በ2013 ከትግራይ የተፈናቀሉ ወገኖች
    የኦሮሚያ ጸጥታ ይዞታ፤ የንጹሃን ጥቃት እና የሰላም ጩኸት
    የምስጋና ዝግጅት ለቀድሞዋ የኢትዮጵያ ርዕሠ ብሔር ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ
    የጋዛው ጦርነት ተጽእኖ ያደረገበት የፓሪሱ የፈረንሳይና የእስራኤል ብሔራዊ ቡድኖች ግጥሚያ
    20 min
  • የኅዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት
    በዛሬው የዜና መጽሔት ከተካተቱት ዘገባዎች መካከል
    -የተካረረዉ የኢትዮጵያ እና የሶማልያ የዶፕሎማሲ ዉዝግብ ፤
    -በአሙሩ ወረዳ ከሰባት ወራቶች በፊት የታሰሩ ከመቶ በላይ ሰዎች እስከዛሬ ለፍርድ አለመቅረባቸዉና
    - በነጩ ቤተ መንግሥት ዉስጥ የተገናኙት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተሰኙት ርዕሶች ስር የተጠናቀሩት ዝግጅቶች ይገኙበታል።
    17 min

About ዜና መጽሔት

From the publisher's feed

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ…