Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ... more
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,842 episodes available.
February 16, 2024የመርዓዊው ግድያ ፈጻሚዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ መጠየቁበጎጃም መርዓዊ ከተማ የተፈጸመውን ግድያ ያዘዙትና የፈጸሙት ለፍርድ እንዲቀርቡ ግፊት እንዲደረግ ዓለም አቀፉ የዐማራ ህብረት ጥሪ አቀረበ። ተቀማጭነቱ በአሜሪካ የሆነው ህብረት፤ የመራዊው ግድያን ያዘዙትና የፈጸሙት ለዓለም አቀፍ ፍርድ መቅረብ አለባቸዉ፤ በዐማራ ክልል የተራዘመው የእስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መነሳት አለበት ሲል ጠይቀዋል።...more4minPlay
February 16, 2024ለረሃብ የተጋለጡ ህጻናት በትግራይበትግራይ ለረሃብ በተጋለጡ አካባቢዎች በተለይም ህፃናት ለከፋ ሁኔታ እየተጋለጡ ይገኛሉ። በክልሉ አበርገለ የጭላ ወረዳ በሦስት ወራት ብቻ 120 ህፃናት ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ተጋልጠው ወደ ሆስፒታል ገብተዋል። በተከተሰው ድርቅና ረሃብ ምክንያት በምግብ እጥረት የተጠቁ ህፃናት ቁጥር በሶስት እጥፍ ጨምሯል።...more4minPlay
February 16, 202437ኛዉ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ድባብየአፍሪካ ህብረት 37ኛው የመሪዎች ጉባኤ የሚካሄደው በአስተናጋጇ ኢትዮጵያ ሳይቀር በሌሎች በርካታ አባል አገሮች፤ የሰላም ችግር ባለበት፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦችም በድርቅ ምክንያት ለረሀብ አደጋ በተጋለጡበት ድባብ ነው። አስተያየት ሰጭዎች ህብረቱ በዘንድሮው ጉባኤ አዲሱ ነገር በደካማ አቋም ላይ መሆኑን ይገልፃሉ።...more5minPlay
February 15, 2024በአማራ ክልል በተከሰተው ድርቅ ከ1,8 ሚሊየን ሕዝብ በላይ ለችግር መዳረጉበአማራ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተው ድርቅ ከ1.8 ሚሊዮን በላይ ህዝብ መቸገሩ ተገለጸ። ከመካከላቸው ከ380 ሺህ በላይ ሕጻናትና እናቶች ለከፍተኛ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት መጋለጣቸውን ክልሉ አስታውቋል።...more4minPlay
February 13, 2024ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ኅብረት የሳሞአ ሥምምነት እንድትወጣ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠየቀየኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት የበላይ ጠባቂ አባቶች ህዳር 2016 ዓ. ም የተወሰኑ የአፍሪካ፣ የካሪቢያንና የፓሲፊክ ሀገራት የንግድና የኢኮኖሚ አሳሪ የአጋርነት ስምምነትን ከአውሮፓ ኅብረት ጋራ ``የሳሞአ ስምምነት`` መፈራረማቸውንና ኢትዮጵያ አንዷ ፈራሚ መሆኗን ጠቅሰው ኢትዮጵያ ራሷን ከስምምነቱ እንድታገል ጠይቀዋል።...more3minPlay
February 12, 2024የዓድዋ መታሰቢያ የአገር ግንባታ ፋይዳው - የሕዝብ አስተያየትአዲስ አበባ ውስጥ ግንባታው ተጠናቆ የተመረቀው ዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ለትውልድ አንድነት እና ለአገር ግንባታ የራሱ ሚና እንደሚኖረው ተነገረ፡፡ አስተያየታቸውን የሰጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የሙዚየሙን ፋይዳ አጉልተው ያነሱት በርካቶች ናቸው፡፡ በተቃራኒው ግን ግንባታዉ ከሰላም እጦትና ከኢኮኖሚ አለመረጋጋት መቅደም የለበትም ያሉም ይገኛሉ፡፡...more4minPlay
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,842 episodes available.