Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ... more
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,995 episodes available.
May 17, 2024የግንቦት 9፣2016 ዜና መፅሔት-በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሥለ ኢትዮጵያ ፖለቲካዊና የሰብአዊ መብት ይዞታ የሰጡትን አስተያየት ኢትዮጵያ አጥብቃ ተቃወመችዉ።የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ባወጣዉ መግለጫ የአምባሳደሩን አስተያየት «ሐሰት« ና «ተቀባይነት» የሌለዉ በማለት አጣጥሎታል።-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዎላይታ ዞን ደሞዝ ያልተከፈላቸዉ የመንግስት ሠራተኞች ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ያደረጉት ሰልፍ በፖሊስ ኃይል ተበተነ።-በቀጣዮቹ ሁለት ወራት 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወታቸው ለመመለስ እቅድ መያዙ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የተሃድሶ ኮምሽን አስታወቀ...more21minPlay
May 16, 2024የሐሙስ ግንቦት 8 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የዜና መጽሄትየዜና መጽሔ ዘገባዎቹ፦ለኢትዮጵያው ግጭት መፍትሄ የአሜሪካ ጥሪ፦ የአምባሳደሩ ንግግር፤ ለባሕላዊ ዳኝነት ትኩረት የሰጠው የፍትሕ ተቋማት ሽግግር ፤ የሲቪል ድርጅቶች ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አጀንዳዎችን አስገቡ፤ የኢትዮጵያ ኢንደስትሪ ዞኖች እጣፈንታ እና የፖሊሲ ለውጥ እንዲሁም እስራኤል በራፋሕ ላይ የከፈተችው ጦርነት ይሰኛሉ ።...more27minPlay
May 15, 2024የግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. የዜና መጽሔትየአሜሪካን የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛን፣ የኦሮምያን የፖለቲካና ፀጥታ ችግር ለመፍታት ሁሉን አቀፍ ድርድር እንዲደረግ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ጠይቀዋቸዋል። በአማራ ክልል የሰላም እጦት ሰበብ በተለያዩ አካባቢዎች ትምሕርት ቤቶች በመዘጋታቸው ሴት ተማሪዎች እንዲያገቡ እየተገደዱ መሆኑን ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ተናግረዋል።በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሶዶ ዙሪያ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኞች ደሞዝ እንዲከፋላቸው በአደባባይ ሰልፍ ጠይቀዋል። እነዚህና የካናዳ መንግሥት እርዳታ ለቀድሞ ተዋጊዎች እንዲሁም በጎ ፈቃደኛዋ ሲስተት ካሕሳ ሓጎስ መሸለማቸውን የሚያስቃኙ ዘገባዎች ተካተዋል።...more21minPlay
May 14, 2024የማክሰኞ፤ ግንቦት 6 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የዜና መጽሄትየፖለቲከኛ በቴ ዑርጌሳን ግድያ የምርመራ ሂደት ምን ተግዳሮት ገጥሞት ይሆን?--ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ተማጋጋቢዎቹ ጎረቤት ሀገራት--በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ በተከሰተ ግጭት የሰው ህይወት ማለፉ እንዲሁም --የአዉሮጳ ህብረት 2024 ምርጫ ዛሬ ከያዝናቸዉ ለማስደ,ጥ ከያዝናቸዉ ዘገባዎቻችን መካከል ጥቂቶቹ ናቸዉ...more17minPlay
May 13, 2024DW Amharic - ዜና መጽሔት፤ የግንቦት 5 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ሰኞDW Amharic - ከባድ ዝናብ ድንኳናቸውን ያፈራረሰባቸው በደቡብ ወሎ የሚገኙ ተፈናቃዮች ፤ በድሬደዋ የጎርፍ ጉዳትን ለመቀነስ ያለመው ፕሮጀክት፤ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ቦረና ዞን የተማሪዎች ጥያቄና ስጋት፤እንዲሁም ጅቡቲ ለዓለም አቀፍ ባለሀብቶች ያቀረበችውን የልማት ጥሪ የተሰኙ ዘገባዎች ተጠናቅረዉበታል።...more18minPlay
May 08, 2024DW Amharic የሚያዝያ 30 ቀን 2016 ዜና መጽሔትጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በነቀምቴ ከተማ ከአራቱም የወለጋ ዞኖች ለተውጣጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች “ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ምላሽ አግኝቷል፤ ለዚህ አንታገልም” ሲሉ ተናገሩ። በግጭት ምክንያት በአማራ ክልል ደም ባለመሰብሰቡ ሆስፒታሎች ሕሙማን ለማከም ችግር ገጥሟቸዋል። በትግራይ ክልል የሚገኘው እና በጦርነት ወቅት የተጎዳው የአል ነጃሺ መስጂድ መልሶ ለመገንባት ያቀደ መርሐ ግብር ይፋ ተደረገ። ኢትዮጵያ በፕሬስ ነጻነት ባለፈው ዓመት ከነበረችበት በአስራ አንድ ደረጃዎች ወደ ኋላ አሽቆለቆች። እስራኤል በራፋ የጀመረችው ወታደራዊ ዘመቻ እንዳሳዘናቸው የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል ተናገሩ።...more21minPlay
May 07, 2024የማክሰኞ ሚያዝያ 29 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ዜና መፅሔትየሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት)ኃይላት ከሱዳን ጦር ጋር ወግነው እየተዋጉ ነው በማለት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ያቀረበውን ክስ የትግራይ ክልል ዜያዊ አስተዳደር አስተባበለ። በአማራ ክልል የሰሜን ጎጃም ዞን መምህራን ደመወዝ ከተከፈላቸው ከ2 ወራት በላይ መሆኑን ዐስታወቁ።የቅድመ ክስ እሥርን ለመቆጣጠር እና ለማስቀረት እንዲሁም የፍትሐዊ እና ሰብአዊ መብት መርኾችን ያካተተ የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ለመገንባት፤ የፍትሕ አካላት እና ሌሎች ባለድርሻዎች ግዴታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ።በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን ዛሬ ጠዋት የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል...more19minPlay
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,995 episodes available.