Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
August 21, 2024ዛሬ ገበያ፤ ለሸማቾች ወቅታዊ የገበያ መረጃ የሚያቀርበው ዲጅታል መድረክዛሬ ገበያ፤ ለአዲስ አበባ ከተማ ሸማቾች ዕለታዊ የሸቀጣሸቀጦች ዋጋን ለመከታተል የሚያግዝ ዲጅታል መድረክ ነው። ዝሩባቤል ዮሀንስ እና ናኦል ከፍያለው በተባሉ ወጣቶች የተመሰረተው ይህ ዕለታዊ የገበያ ዋጋ መከታተያ ሸማቾች የዕየለቱን የገበያ ዋጋ በማወቅ የገንዘብ አቅማቸውን ያገናዘበ ግዥ እንዲከናውኑ ለመወሰን ያግዛል።11 minPlay
August 14, 2024በበይነመረብ የሚደረግ የማንቃት ስራ መሬት ላይ ለውጥ ያመጣልን?የበይነመረብ ተሟጋችነት፤ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን፣ በይነመረብን እና ተንቀሳቃሽ ስልኮችን የመሳሰሉ ቴክኖሎጅዎችን በመጠቀም ለውጥን ለማነሳሳት ጥቅም ላይ ይውላል።የበይነመረብ ተሟጋችነት በጊዜ እና በቦታ ሳይገደብ በመላው ዓለም በቀላሉ ተደራሽ በመሆኑ ደግሞ ተፈላጊነቱ ጨምሯል። ለመሆኑ ጥቅም እና ጉዳቱ ምንድነው?መሬት ላይስ ለውጥ ያመጣልን?13 minPlay
August 07, 2024እየተባባሰ የመጣው በልጆች ላይ የሚደርስ የሳይበር ጉልበተኞች ጥቃትበቅርቡ በ 44 አገሮች ላይ የተደረገ አንድ ጥናት የ«ሳይበር ቡሊንግ» መጨመሩን ያሳያል። በጥናቱ መሰረት የሳይበር ጉልበተኞች ጥቃት ከ6 ተማሪዎች አንዱን ይጎዳል። መረጃዎች እንደሚያሳዩት ችግሩ በዓለም አቀፍ ደረጃም አሳሳቢ ነው።ለመሆኑ ችግሩ በኢትዮጵያ ምን ያህል ነው? ችግሩ ሲያጋጥምስ ምን መደረግ አለበት? እንዴትስ መከላከል ይቻላል?13 minPlay
July 31, 2024ከሰሞኑ ዓለም አቀፍ የኮምፒዩተር ሥርዓት ብልሽት ጀርባ ያሉ እውነታዎችበቅርቡ በማይክሮሶፍት ዊንዶ ኮምፒዩተሮች ላይ በተከሰተ ችግር በመላው ዓለም በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ መስተጓጎል አስከትሎ ነበር።ችግሩን ፈጥሯል የተባለው ክራውድስትራይክ የተባለው የቴክኖሎጅ ኩባንያ ለችግሩ ይቅርታ ጠይቆ ለማስተካከል እየሰራ መሆኑን ገልጿል። ለመሆኑ ችግሩ እንዴት ተከሰተ? ያስከተለው ጉዳት እና መፍትሄውስ?11 minPlay
July 24, 2024ስፓሩሊና ፤ ብዙ ሚሊዮን ብር የሚታፈስበት የውሃ ውስጥ ምርትከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከፍተኛ ትኩረት እና ሰፊ ጥናቶች እየተደረገበት የሚገኘው «ስፓሩሊና» ውሃ ውስጥ የሚገኝ ወደ ሰማያዊ የሚያደላ አረንጓዴ ቀለም ያለው የአልጌ አይነት ነው። ባለሙያዎች እንደሚሉት ስፓሩሊና በአንድ ህዋስ ውስጥ ፕሮቲን፣ ቫይታሚን፣ ስብ፣ ማዕድናት እና ካርቦሃይድሬትን በመያዝ ብቸኛው ማይክሮ አልጌ ነው።11 minPlay
July 16, 2024በጅማ ከሰማይ ስለወረደው ባዕድ ነገር ምንነትባለፈው ዓርብ ሰኔ 05 ቀን፣ 2016 ዓ.ም. ሌሊት በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን የቡ ከተማ ከሰማይ ከፍተኛ ድምፅ ተሰምቶ ወድቋል የተባለው ባዕድ ነገር በጅማ ዩኒቨርሲቲ በተቀናጀ መልኩ እየተጠና መሆኑ ተነገረ ። ስለባዕድ ነገሩ ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተጀመረው የቤተሙከራ ጥናት መጠበቅ አስፈላጊ መሆኑንም ባለሞያዎቹ መክረዋል ።4 minPlay