Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
June 12, 2024በአቬሽን ቴክኖሎጂ ኢትዮጵያ ምን ደረጃ ላይ ትገኛለች?ከስምንት አስርተ አመታት በፊት አውሮፕላን ለመገጣጠም ጥረት ያደረገችው ኢትዮጵያ፤ በአፍሪቃ ስሙ የሚጠቀሰስ አየር መንገድ በመመስረትም ቀዳሚ ሀገር ነች።ለመሆኑ ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት በአቬሽን ቴክኖሎጂ ምን ደረጃ ላይ ትገኛለች? በዘርፉ ያሉ ችግሮች እና መፍትሄዎችስ?12 minPlay
June 05, 2024በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰሩ ቪዲዮዎችን እንዴት መለየት ይቻላል?በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ በመታገዝ ተንቀሳቃሽ ምስሎችም /ቪዲዮዎች/ መስራት በአሁኑ ወቅት እየተለመደ መጥቷል። እነዚህ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ሰዎች ያልሰሩትን እና ያላሉትን ነገር እንዳሉ እና እንደሰሩ ተደርጎ የሚቀርብ በመሆኑ የጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃዎችንም ያስፋፋሉ። ታዲያ እነዚህን ቪዲዮዎችን እንዴት መለየት ይቻላል?12 minPlay
May 29, 2024ኢትዮጵያ ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ምን ያህል ምቹ ናት?የቤት አውቶሞቢል የኤለክትሪክ ካልሆነ ወደ ሀገር እንዳይገባ የኢትዮጵያ መንግሥት ውሳኔ ካሳለፈ ወራት ተቆጥረዋል። ያም ሆኖ የመኪናዎቹ ውድ መሆን፣ የኤለክትሪክ አቅርቦት ፣ የባትሪ መሙያ ጣቢያዎች ፣ የመለዋወጫ እና የጥገና ማዕከላት እጥረት ተግዳሮቶች መሆናቸው ይነገራል።13 minPlay
May 22, 2024በኢትዮጵያ በሴቶች ላይ ያነጣጠረ የኦንላይን ዘለፋ እና ማሸማቀቅ ከፍተኛ መሆኑን ጥናት አመለከተበማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች በሀሰት እና በተዛባ መረጃ ላይ የተመሰረቱ በመሆናቸው፤በማህበራዊ ህይወታቸው፣ በቤተሰባቸው ፣በስራ አካባቢያቸው እና በሙያቸው ላይ ጉዳት ማድረሱን ጥናቱ አመልክቷል ። አንዳንድ ሴቶች በበይነመረብ በተደረጉ ዘመቻዎች ምክንያት አካላዊ ጥቃት ወይም እንግልት እንደደረሰባቸው ለአጥኝዎቹ ገልፀዋል።13 minPlay
May 08, 2024የዘረመል ማሻሻያ የአይን ህክምና እና ያሳደረው ተስፋየሰው ልጅ በተፈጥሮ ከተጎናጸፋቸው የስሜት ህዋሳት ስስ የሆነው እና በዚያው ልክ ለተለያዩ አደጋዎች በእጅጉ ተጋላጭ የሆነው አይን እንደማንኛውም የሰውነት ክፍል ሊታከም ይችላል። አሁን አሁን ያለንበት የቴክኖሎጂ ዘመን ልክ እንደሌሎች የህክምና ዘርፎች ሁሉ ለአይነስውርነት መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉ የምርምር ውጤቶች ይፋ እየሆኑ ነው ።11 minPlay