Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,875 episodes available.
March 09, 2026የየካቲት 30 ቀን 2018 ዓ/ም የስፖርት ዝግጅትድሉ አትሌት ጽጌ ገብረሰላማ ክብሯን ያስጠበቀችበት ድል ሲሆን ከ22 ዓመታት በኋላ በሊዝበን ተከታታይ ድል የተቀዳጀች የመጀመሪያዋ ሴት አትሌት አድርጓታል። የ2023 የዓለም የክሮስ ካንትሪ የብር ሜዳሊያ አሸናፊዋ ጽጌ፣ በውድድሩ ሁለተኛ አጋማሽ ጀምሮ ፍጥነቷ ባይቀንስ ኖሮ የቦታውን ክብረ ወሰን የማሻሻል እድሏ የሰፋነበር ።...more0minPlay
March 09, 2026የአፍሪካ ሕብረት የሴቶችን ውክልና የበለጠ እንዲያሳድግ ተጠየቀየአፍሪካ ሕብረት በተለያዩ የአመራርና የኃላፊነት እርከኖች ላይ የሚገኙ ሴቶችን ቁጥር ከወንዶች እኩል ለማድረግ ያስቀመጠውን ግብ አለማሳካቱ እና እንዲሰራበት ሴቶች ጠየቁ። የሕብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር በበኩላቸው የሴቶችን ቁጥር ከወንዶች እኩል ለማድረግ የተቀመጠው ግብ የአጀንዳ 2063 አካል መኾኑንና በትኩረት እንደሚሰራበት ተናግረዋል።...more0minPlay
March 09, 2026መንግሥት የነዋሪዎችን ደህንነት እንዲጠበቅ ሲል ጎጎት ፓርቲ ጠየቀየማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በምሥራቅ ጉራጌ ዞን ምሥራቅ መስቃን ወረዳ የሲቪል ነዋሪዎችን ደህንነት እንዲጠበቅ ሲል ለጉራጌ አንድነትና ፍትህ ፓርቲ ባወጣዉ መግለጫ ጠየቀ፡፡ ፓርቲው በዚሁ መግለጫው በምሥራቅ መስቃን ወረዳ በንጹሃን ዜጎች ላይ በተደጋጋሚ በታጣቂዎች ይፈጸማል ያለው ጥቃት እንዳሳሰበው ገልጿል፡፡...more0minPlay
March 09, 2026“የሴቶች ብርቱ የጦርነት ተጋላጭነት እልባት ይሻል” ኦፌኮኦፌኮ በመላው ኢትዮጵያ በዋናነት ሴቶችን ተጠቂ የሚያደርግ ያለው ግጭት-ጦርነት እንዲቆም አስቸኳይ ያለውን ጥሪ አቀረበ፡፡ ፓርቲው ይህን ያለዉ በመላው ዓለም ታውሶ የዋለውን የዓለም ሴቶች ቀን በማስመልከት ባወጣው መግለጫ ነው። “ሴቶች የሰላምና የዲሞክራሲ ምሰሶዎች ናቸው” ሲል እለቱን በማክበር በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ጦርነት እንዲቆም ጠይቋል።...more0minPlay
March 09, 2026እንወያይ፤ የነጻ ፕሬስ እና የጋዜጠኞች ፈቃድ መሰረዝ ተጽኖ በኢትዮጵያኢትዮጵያ ሰባተኛዉን አገራዊ ምርጫ ለማካሄድ ሽር ጉድ እያለች ባለችበት በአሁኑ ወቅትም ይሁን አስቀድሞ ጥቂት የማይባሉ የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች እና ጋዜጠኞች እንዲሁም በአመዛኙ "ነጻ" የሚባሉ ብዙኃን መገናኛ ዐውታሮች ፈቃዳቸው እየተሰረዘ፣ ጋዜጠኞቻቸውም የሥራ ፈቃዳቸዉን እየተነጠቁ ነዉ።...more0minPlay
March 08, 2026ዓለም አቀፍ የሴቶችን ቀን ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነውበየዓመቱ በጎርጎሪያኑ መጋቢት 8 ቀን የሚከበረው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን፤ የሴቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ እና ፖለቲካዊ ስኬቶችን የሚያከብር ዓለም አቀፍ በዓል ነው። በዓሉ «ለማግኘት መስጠት» / give to gain/በሚል መሪ ቃል በዓለም ለ115ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ እየተከበረ ነው።...more0minPlay
March 07, 2026ትኩረት በአፍሪቃ፤አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ጦርነት በአፍሪቃ ምን ተፅዕኖ ያሳድራል?የኢራን ጦርነት ዓለም አቀፍ ንግድን እያስተጓጎለ ነው። የንግድ መርከቦች ከሱዌዝ ቦይ ይልቅ አፍሪካ ወደሚገኘው ኬፕ ኦፍ ጉድ ሆፕ ለመሄድ ይገደዳሉ። ይህም ወጪን ይጨምራል፤በነዳጅ እና በሌሎች ሸቀጦች የዋጋ ጭማሪ ያስከትላል። ጦርነቱ በውጭ አገር ተቀጥረው ለሚሠሩ አፍሪቃውያንም የኢኮኖሚ መዘዝ አለው።...more0minPlay
March 07, 2026ትኩረት በአፍሪቃ፤ኬንያ በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ለምን ስጋት ገባት?ከ400,000 በላይ ኬንያውያን እንደ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ኳታር ባሉ የባህረ ሰላጤው ሀገራት ይሰራሉ። ብዙዎቹ በቤት ውስጥ ሥራ፣ በግንባታ፣ በእንግዳ ተቀባይነት እና በአቪዬሽን ዘርፍ ተቀጥረው ይሰራሉ።የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት እነዚህን ኬንያውያን ስጋት ውስጥ ከቷል።...more0minPlay
March 07, 2026እያሽቆለቆለ ባለው የዓለም ቡና ገቢያ የበለጠ ማን ይጎዳል?ባለፉት ወራት በዓለም ገበያ የአንድ ፓውንድ ቡና ከ4 ዶላር ወደ 2.80 ዶላር ዝቅ ሲል ለኢትዮጵያ “እጅግ በጣም ፈታኝ ሁኔታ” መፈጠሩን የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ተናግረዋል። ዋጋው የቀነሰው ብራዚል ለዓለም ገበያ የምታቀርበው እና ቪየትናም የምታመርተው ቡና ይጨምራል ተብሎ ስለተተነበየ ነው።...more0minPlay
March 06, 2026ነገ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. ስለሚጀመረው የመራጮች ምዝገባ የተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች አስተያየትየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የካቲት 7 ለመጀመር ያቀደውን የመራጮች ምዝገባ በ21 ቀናት አራዝሞ ነገ የካቲት 28 ቀን ይጀምራል። ምዝገባው ለጊዜው የተራዘመው ሥራውን "በታሰበው መልኩ ማከናወን ባለመቻሉ" መሆኑን የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተ ወርቅ ኃይሉ ገልፀው ነበር። ስለምዝገባውና ዝግጅታቸው የአምስት ከተሞች ነዋሪዎችን አስተያየት ጠይቀናል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,875 episodes available.