Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,875 episodes available.
March 12, 2026ነጻ ሚዲያ የሚኖረው ሚና - ትኩረት እንዲሰጠው ተጠየቀባሉት ወራቶች በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የተወሰዱት ተከታታይ እርምጃዎች በኢትዮጵያ የሚዲያ ነፃነት እና ጋዜጠኝነት ሞያ ላይ ከፍተኛ ጫና የታየበት ነበር ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበር ይፋ ባደረገዉ የዳሰሳ ዘገባ አስታወቀ። በሽብርተኝነት ወንጀል የተከሰሱት ጋዜጠኞች ጉዳይ ሌላዉ ርዕስም ነዉ።...more0minPlay
March 12, 2026የጀርመን የፌዴራሊዝም ሥርዓት አተገባበር እና ልዩ መገለጫውቡንደስታግ የሀገሪቱ የታችኛው ምክር ቤት ሕግ አውጪ አካል ነው። ምክር ቤቱ የሀገሪቱን ቻንስለር ይመርጣል፣ የፌደራል መንግሥትንም ይቆጣጠራል። ቡንደስራት የሀገሪቱ ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ከሚመሩ 16 ከፍተኛ ዳኞች መካከል ስምንቱን ይመርጣል። አባላቱም ከ16 የፌዴራል ክልሎች የተውጣጡ ናቸው።...more0minPlay
March 12, 2026የጦርነት ስጋት ያዣበበባት የትግራይ ክልል እና የህወሓት አስገዳጁ የገንዘብ ማሰባሰብያህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በትግራይ ነዋሪ የሆነዉ ደሞዝተኛ ሕዝብ የአንድ ወር ደምወዙን እንዲያዋጣ ፤ ደምወዝተና ያልሆነዉ ደግሞ ሌሎች ቁሳቁሶችን እንዲሰጥ መጠየቁን በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ሦስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጠየቁ። በትግራይ ዳግም ግጭት ይቀሰቀሳል የሚለዉ ስጋት አይሏል። የክልሉ ነዋሪዎች አካባቢዉን ጥለዉ እየወጡ ነዉ።...more0minPlay
March 12, 2026በጀርመን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሴቶች ማህበርበጀርመን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሴቶች ማህበር በፍራንክፈርት ከተማ ባዘጋጀው መድረክ ላይ 130 ኛዉ የአድዋ ድል በዓል ብሎም ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን ታስቦ ዉሏል። በዝግጅቱ ላይ የፍራንክፈርት ከንቲባ በፍራንክፈርት የሴቶች ጉዳይ ዋና ተጠሪ ጨምሮ በጀርመን የኢትዮጵያ አንባሳደር እና ሌሎች ተጋባዥ የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።...more0minPlay
March 11, 2026አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን በገጠሙት ጦርነት የነዳጅ ዋጋ “አስፈሪ በሆነ መልኩ” ሲንር ኢትዮጵያ “የቁጠባ እርምጃዎች” ልትከተል ነውአሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን በገጠሙት ጦርነት የነዳጅ ዋጋ ሲንር የኢትዮጵያ መንግሥት ለቤንዚን እና ለነጭ ናፍጣ በሊትር የሚያደርገው ድጎማ በ44 ብር ገደማ እንደጨመረ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ ተናግረዋል። ከነዳጅ በተጨማሪ የማዳበሪያ ዋጋ በዓለም ገበያ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በማሳየቱ የኢትዮጵያ ገበሬዎችን ሊፈታተን ይችላል።...more0minPlay
March 11, 2026በታዋቂ ሴቶች ላይ የበረታው ዲጅታል ጥቃት በኢትዮጵያአዲስ ፓወር ሃውስ የተባለ ሀገር በቀል ተቋም በቅርቡ ባወጣው ጥናት፤ በኢትዮጵያ ታዋቂ ሴቶችን ኢላማ ያደረገ ዲጅታል ጥቃት ጨምሯል።ጥናቱ በቲክቶክ፣በፌስቡክ፣በቴሌግራም፣በዩቱብ እና በሊንክዴን ላይ በተለጠፉ1307 ይዘቶች ላይ ትንተና ያደረገ ሲሆን፤ በዚህም በታዋቂ ሴቶች ላይ ጥቃቱ የበረታ መሆኑን የተቋሙ ዳይሬክተር ሀና ለማ ገልፃለች።...more14minPlay
March 11, 2026የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው እና የኑሮው ጫናውየገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ፤ በመንግስት ከፍተኛ ድጎማ ወደ አገር ውስጥ ከሚገቡ ምርቶች አንደኛው የሆነው ነዳጅ የኑሮ ጫናን እንዳያስከትል በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተደጎመ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ “መንግስት በከፍተኛ ዋጋ የሚያመጠው ነዳጅ በአግባቡ አገልግሎት ላይ እንዳይውል መሰናከል የሚሆኑት ላይ እርምጃ መወሰዱ ይቀጥላል” ብለዋል፡፡...more0minPlay
March 11, 2026በጋሞ ዞን ጎርፍ እና በናዳ አደጋ የ64 ሰዎች ህይወት አለፈበደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በመሬት ናዳ እና በጎርፍ አደጋ የ64 ሰዎች ህይወት አለፈ ፡፡ አደጋው ትናንት ሌሊት በጣለው ዝናብ የተከሰተው በዞኑ ካምባ ዙሪያ ፣ ጋጮ ባባ እና ቦንኬ በተባሉ ወረዳዎች ውስጥ ነው ፡፡ የዞኑ መስተዳድር የመሬት መንሸራተት በሚያሰጋቸው ገደላማና ተዳፋት ቦታዎች ነዋሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል ፡፡...more0minPlay
March 11, 2026በኢትዮጵያ ህዝባዊ እምቢተኝነትን አሰመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫይህ ትዕይንተ-ሕዝብ በአገሪቱ የሚዲያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ፣በዩትዩብ ከአንድ ሚሊዮን በሳተላይት ቴሌቪዥን ደግሞ ከ10 ሚሊዮን ያላነሰ ህዝብ በቀጥታ ሥርጭት እንዲከታተለው ታቅዶ የሚካሄድ መሆኑን የአዘጋጁ ግብረ ኃይል አስታውቋል።የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሁኔታ የሚከታተሉት አቶ አያና ፊይሳ ደግፎ ሰልፍ ሊወጣላቸው የሚችል ሰው ስለመኖሩ ጥያቄ አላቸው ።...more0minPlay
March 11, 2026ዳግም የቪዛ ክልከላ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ላይየኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን የፊታችን ዐርብ ፖላንድ ውስጥ በሚጀምረው የዓለም አትሌቲክስ ውድድር ለመሳተፍ የሚያስችለውን ቪዛ እስካሁን አላገኘም ። ፖላንድ ለመግባት የሚያስፈልገውን የሸንገን ቪዛ ለማመልከት 45 ቀናት እንደሚያስፈልግ የጠቆሙ አሰልጣኝ ይህንኑ ከሦስት ወራት በፊት ብናገርም ሰሚ አጥቻለሁ ብለዋል ።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,875 episodes available.