Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,875 episodes available.
March 06, 2026ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም አትሌቲክስ የ"አንድ ቀን ውድድር" ልታዘጋጅ ነውኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም አትሌቲክስ የ"አንድ ቀን ውድድር" ልታዘጋጅ ነው ። ከ 43 ቀናት በኃላ ሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ የሚካሄደው ይህ ውድድር፣ ኢትዮጵያን በአትሌቲክስ ውድድሮች ካላት የቆየ ዝና ባሻገር በትልልቅ ውድድር አዘጋጅነትም ወደ ዓለም አቀፉ መድረክ ብቅ የምትልበት አጋጣሚ እንደሆነ ተነግሯል።...more0minPlay
March 06, 2026የአፍሪካ ቀንድን ያሰጋው ድርቅከጥቅምት እስከ ታህሳስ እንደሚጥል የሚጠበቀው ዝናብ በመቋረጡ በአፍሪካ ቀንድ 26 ሚሊየን ህዝብ ለከባድ ርሃብ መጋለጡን ፤ 58 ሚሊየን ህዝብ ደግሞ የመጠጥ ውሃ እጥረት እንደሚሰቃይ ኦክስፋም ትናንት ባወጣው ዘገባ፤ አስታውቋል። የችግሩ ሰለባ ከሆኑት ሀገራት ውስጥ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ እና ኬንያ ይገኑበታል።...more0minPlay
March 06, 2026“የኦነሰ ተዋጊዎች ወሲባዊ ባርነትን ጨምሮ በርካታ ጥሰቶችን ፈጽመዋል” አምነስቲዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት(ኦነግ-ኦነሰ)ን ሴቶችን በጅምላ በመድፈርና የማሰቃየት ወንጀሎችን ጨምሮ በበርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ከሰሰ፡፡ተቋሙ “የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት በኦነሰ ተዋጊዎች የተፈጸሙ ጾታዊ ጥቃት፣ ከፍርድ ውጭ ግድያና የማሰቃየት ወንጀል ሊመረምሩ ይገባልም”ብሏል፡፡...more0minPlay
March 06, 2026ለ100ኛ ጊዜ ደም ለጋሹ ልባም በጎ ፈቃደኛ ቃዲ አደምበእናቶች እና የጨቅላ ሕጻናት ጤና ፣ በግጭቶች እና አደጋዎች የሚከሰቱ የአካል ጉዳት እና የደም መፍሰስ እንዲሁም በተለያዩ በሽታዎች ምክንያት የደም ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ይነገራል። ይህም በኢትዮጵያ በህክምናው ዘርፍ የሚፈለገው የደም ፍላጎት እና አቅርቦት አለመመጣጠኑን ተከትሎ አንደኛው የጤና ዘርፍ ተግዳሮት መሆኑ ይጠቀሳል።...more0minPlay
March 05, 2026ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ፤ የ "በርሊናለ" የክብር ተሸላሚ -ክፍል ሁለት ቃለ-ምልልስከአስርተ ዓመታት የታሪክ ማህደር ማሰባሰብ በኃላ “ጥቁር አንበሳ - የፎማ ተኩላ” በሚል ርዕስ ለእይታ ያቀረቡት ፊልም፤ ኢትዮጵያዉያን ከፍሺስት ኢጣልያ ጋር ያደረጉትን ተጋድሎ የሚያሳይ ነዉ። የኃይሌ ገሪማ ይህ ዘጋቢ ፊልም ጀርመን መዲና በርሊን በዓመታዊዉ የዓለምአቀፉ የፊልም ፊስቲቫል መድረክ “በርሊናለ” ላይ ለእይታ አቅርበዋል።...more0minPlay
March 05, 2026ለአንድ ወር ያለምንም የምግብ ድጋፍ ተፈናቅለዉ የሚገኙ 100 ሺህ ኖሪዎችአላማጣ ኮረም ወፍላ ዛታና ራያ አላማጣ ጦርነትን ሽሽት ተፈናቅለዉ በቆቦና ሰቆጣ ከተማ የሚገኙ ወገኖች ምንም ዓይነት የምግብ ድጋፍ ለአንድ ወር ባለማገኘታቸዉ ለርሀብ ተዳርገናል አሉ። ከስድስት ወረዳ የተፈናቀልነዉ ቁጥራችን 100 ሺህ ይደርሳል የሚሉት ተፈናቃዮቹ በመንግሥት ደረጃ መረጃ ከመሰብሰብ ያለፈ ድጋፍ የለም ይላሉ።...more0minPlay
March 05, 2026ስለአርሲው ግድያ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ማሳሰቢያየኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (“ኦነግ ሸኔ”) ያለው ታጣቂ ቡድን በሽርካ፣ በጉና፣ በመርቲ፣ በአሰኮ እና በኦንቆሌ ዋቤ ወረዳዎች በሰዎች ላይ በፈጸማቸው ጥቃቶች በሰዎች ሕይወት፣ አካልና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡...more0minPlay
March 05, 2026በኢትዮጵያ እንቅስቃሴን የፈተነው የነዳጅ አቅርቦትአስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ አሽከርካሪዎች እንደሚሉትም፤ “ስቃይ ውስጥ ነን፤ ነዳጅ ይመጣል ተብለን ሁለት ቀን ቆመን ጠብቀን ሲመጣም ይይዙታል” በማት የሚገኙበትን ፈታኝ ያሉት ሁኔታ ገልጸዋል፡፡...more0minPlay
March 05, 2026አሳሳቢነቱ ጨምሯል የተባለው የኢትዮጵያ የሲቪክ ምኅዳር ኹኔታየአውሮፓ ሕብረት አባላቱንና ሌሎችን ጨምሮ 41 ሀገሮችን ወክሎ ባወጣው መግለጫ፣ በኢትዮጵያ ከቀጣዩ ምርጫ በፊት የሲቪክና የመገናኛ ብዙኃን ምሕዳሩ በብርቱ ሊጤን እንደሚገባ አሳስቧል። ይህ ጥሪ የቀረበው በስዊዘርላንድ ጃኔቫ በመከናወን ላይ ባለው 61ኛው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ነው።...more5minPlay
March 05, 2026የጎርፍ አደጋ ሥጋት በምሥራቅ ኢትዮጵያበበልጉ ወራት በምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ የሆነ የዝናብ መጠን እንደሚጠበቅ ያስታወቀው በኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲቲዩት የሶማሌ እና አጎራባች ክልሎች የሚትሮሎጂ አገልግሎት መስጫ ማዕከል የተለያዩ የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች መሠራት እንዳለባቸው አስገንዝቧል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,875 episodes available.