Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,875 episodes available.
March 01, 2026አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ከተገደሉ በኋላ ኢራን ሦስት አባላት ያሉት የሽግግር ምክር ቤት አዋቀረችአያቶላህ አሊ ኻሜኒ ከተገደሉ በኋላ ኢራን ሦስት አባላት ያሉት የሽግግር ምክር ቤት ሀገሪቱን በጊዜያዊነት እንዲመራ ማዋቀሯን ይፋ አደረገች። ላለፉት 37 ገደማ ዓመታት ሀገሪቱን የመሩት የ86 ዓመቱ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ፣ የኢራን አብዮታዊ ዘብ አዛዥ ጀኔራል ሞሐመድ ፓክፖር እና የሀገሪቱ መከላከያ ምክር ቤት ጸሀፊ አሊ ሻምክኻኒ ተገድለዋል።...more0minPlay
February 28, 2026በኢራን ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦችን ጨምሮ ከ70 በላይ ሰዎች ተገደሉየኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ የአየር መንገድ ኩባንያዎች ወደ ቀጠናው የሚደረጉ በረራዎችን በሙሉ ሰርዘዋል። በኢራን ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦችን ጨምሮ ከ70 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።...more0minPlay
February 28, 2026በሱዳን ጦርነት የጎረቤት ቻድ ሚናበሱዳን የሚካሄደው ጦርነት ወደ ጎረቤት ቻድም እየተቃረበ ነው። ያለፈው ሳምንት መጨረሻ የሱዳን ጦር እና አጋሮቹ በድንበር ላይ ከሚገኙት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል በእንግሊዝኛው ምህፃሩ የRSF ሚሊሻዎች ጋር ተጋጭቷል። የቻድ መንግስትም ከሱዳን ጋር የሚያዋስነውን 1,300 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ድንበር ዘግቷል።...more6minPlay
February 28, 2026ፕሬዝዳንት ኪር ደቡብ ሱዳንን ማረጋጋት ይችሉ ይሆን?የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ሰሞኑን ባለስልጣኖቻቸውን ከስልጣን ማባረር ይዘዋል። ተንታኞች እንደሚሉት የሰሞኑ የፕሬዚዳንቱ እርምጃ በሀገሪቱ እየጨመረ የመጣውን አለመረጋጋት የሚያባባስ ነው። በሙስና፣ በጎሰኝነት እና በብልሹ አስተዳደር የሚተቸው የሳልቫኪር መንግስት ምክትላቸውን ሪክ ማቻርን ካሰሯቸው ወዲህ በሀገሪቱ አለመረጋጋት ተባብሷል።...more6minPlay
February 28, 2026በሰሜን ሸዋ ዞን አሊ-ዶሮ በታጣቂዎች የታገቱ የወረዳ ባለስልጣናትበኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሁለት የዋራ ጃርሶ ወረዳ ባለስልጣናት ከአሽከርካሪያቸው ጋር በታጣቂዎች ከተወሰዱ አስር ቀናት ማለፉ ተነግሯል፡፡ለመረጃው ቅርበት ያላቸው አስተያየት ሰጪዎች ለዶይቼ ቬለ እንደነገሩት ታጣቂዎቹ ሁለቱን የአከባቢው ባለስልጣናት እና ሾፌራቸውን ለመልቀቅ 13 ሚሊየን ብር ጠይቀዋል፡፡...more4minPlay
February 28, 2026አምስት ምርጫ ክልሎችን የተመለከተው ውሳኔ እና የቀጠሉ ውዝግቦችትናንት አርብ በተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች የፌደሬሽን ምክር ቤት እና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ውሳኔን የሚቃወሙ ሰልፎች ተደርገዋል። የተቃውሞ ሰልፉ መነሻ አምስት የምርጫ ከልሎች ከትግራይ ክልላዊ መንግሥት ውጪ ሆነው ለብቻቸው በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምከር ቤት ምርጫ እንዲደረግ መወሰኑ ነው።...more4minPlay
February 28, 2026እስራኤል እና ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን የተቀናጀ ጥቃት መፈጸም መጀመራቸውን አስታወቁእስራኤል እና ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን የተቀናጀ ጥቃት መፈጸም መጀመራቸውን አስታወቁ። ኢራን በበኩሏ ወደ እስራኤል እና በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሠፈሮች እና «ጥቅሞች» ያለቻቸውን ዒላማ ማድረጓን አስታውቃለች።...more0minPlay
February 27, 2026በኦሮሚያ ስለዘንድሮ ምርጫ ወጣቶች ምን ያስባሉ?ዘንድሮ ዓመት በሚካሄደው ሰባተኛ የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ መሰረታዊ ለውጥ ይመጣል የሚል ተስፋ እንደማኖር አስተያየት ሰጪዎች ገለጹ፡፡ አስተያየታቸውን ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አከባቢዎች ለዶይቼ ቬለ የሰጡ ወጣቶች ምርጫውን ከአማራጭ የሃሳብ ፍጭት ይልቅ ሂደቱን የሚጫጫነው የፀጥታ ጉዳዮች እንደሚያሰጋቸው አስረድተዋል፡፡...more0minPlay
February 27, 2026በኤፍራታ ግድም እና ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ የተከሰተ ግጭትበአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞንና ሰሜን ሸዋ አዋሳኝ ወረዳዎች፣ በተለይም በኤፍራታ ግድም እና ጅሌ ጥሙጋ በተከሰተ ግጭት የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉና የአምስት ሰዎች መቁሰል ተገለጸ። ግጭቱ በንብረት ላይም ጉዳት አድርሷል። ይሁን እና የሁለቱ ወረዳ ነዋሪዎች እና አመራሮች ግጭቱን በዘላቂነት ለመፍታት ቁርጠኝነታቸውን እያሳዩ ይገኛሉ።...more0minPlay
February 27, 2026ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት "በንጹሓን ላይ የሚሰነዘር" ያለው ጥቃት "እያደር ከብዷል" አለሰሞኑን በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች ውስጥ ባሉ ከተሞች ንፁሓን ዜጎች በድሮን ጥቃት መገደላቸውን ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የተባለው የአራት ፓርቲዎች ቅንጅት ገለፀ። ቅንጅቱ በዚሁ ክልል "ተፋላሚ ኃይሎች" የአገልግሎት ተቋሟትን ማውደምን ጨምሮ ተደጋጋሚ እገታዎች መፈጸማቸውን ጠቅሶ ድርጊቶቹን አዉግዟል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,875 episodes available.