Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,875 episodes available.
February 26, 2026ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ፤ የ76ኛዉ የፊልም ፊስቲቫል "በርሊናለ" የክብር ተሸላሚየእኔ ቀዳሚ ፍላጎት የማስታወሻ መብቴን መያዝ ነው። ለምሳሌ ታሪኬ ለረጅም ጊዜ የተነገረዉ በተሳሳተ መንገድ ነው።የሁለተኛውን የዓለም ጦርነት በተመለከተ የተዘጋጀ ማንኛውንም ዘጋቢ ፊልም ያየን እንደሆነ ኢትዮጵያ በታሪኩ ዉስጥ የምትጠቀሰዉ ለሦስት ሰከንድ ያህል ብቻ ነዉ። ይሁንና የፋሽት ኢጣልያን ወረራ ካነሳን ኢትዮጵያ በዋናነት የምትጠቀስ ነች።...more15minPlay
February 26, 2026ከሶማሊያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ለመክፈት በተዘጋጀችው በኬንያ የነገሰው የደህንነት ስጋትኬንያ ከሶማሊያ ጋር የሚያዋስኗትን ሁለት የድንበር ኬላዎችን የፊታችን ሚያዝያ እንደምትከፍት አሳውቃለች። የድንበሮቹ መከፈት የደኅንነትና የመሠረተ-ልማት ተግዳሮቶችን ሊያስከትሉ ይችላሉ ተብሎ ይገመታል። ደካማ መንገዶችና ለወንበዴዎች የመጋለጥ ስጋት በአጠቃላይ በሶማሊያ እንዲሁም በሰሜን ኬንያ ጉዞን አስቸጋሪ ያደርገዋል የሚል ስጋት አለ።...more4minPlay
February 26, 2026ክራይሲስ ግሩፕ ለኢትዮጵያና ኤርትራ ውዝግብ ያቀረበው ምክረ-ሀሳብኢንተርናሺናል ክራይሲስ ግሩፕ የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ፤ ከኢርትራ መንግስት ጋር በመሆን ወይም በየግላቸው ወደ ጦርነት ሊገቡ የሚችሉበት ሁኔታ መኖሩን ጠቅሶ፤ አለማቀፉ ማህብረሰብ ውጥረቱን በማርገብ ሊመጣ የሚችልን ጦርነት ለማስቀረት የሚያስችሉ እርምጃዎችን ፈጥኖ እንዴውስድ ጥሪ ማስተላለፉ ይታወሳል።...more0minPlay
February 26, 2026ብሔራዊ ምርጫ በ5 የምርጫ ክልሎች ላይ ያሳለፈው ውሳኔ "ለጊዜው ታግዶ እንዲቆይ" ታዘዘዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ ፓርቲ ለውዝግብ ምክንያት የሆነው የአምስት ክልሎች የምርጫ ጣቢያዎች ጉዳይ ላይ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከፈትኩት ባለው ክስ ጉዳዩ "ለጊዜው ታግዶ እንዲቆይ" ማስወሰኑን ፓርቲው ለዶቼ ቬለ አረጋገጠ።...more4minPlay
February 26, 2026የምግብ ድጋፍ ተነፈግን ያሉ ተፈናቃዮች ለከፋ ስቃይ ተዳርገናል አሉከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተፈናቅለው በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ የሚገኙ ተፈናቃዮች፣ የሚቀርብላቸው የምግብ እርዳታ በመቋረጡ ምክንያት ለረሃብና ለሞት መዳረጋቸውን ተናግረዋል። ከግንቦት 2017 ዓ.ም ጀምሮ ይሰጥ የነበረው የምግብ ድጋፍ ሙሉ በሙሉ በመቆሙ ምክንያት በችግር ውስጥ ነንም ብለዋል ።...more4minPlay
February 26, 2026የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ በፌድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በጊዜያዊነት ታገደየፌድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ ለጊዜው ታግዶ እንዲቆይ ትዕዛዝ መስጠቱን የዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ ፓርቲ ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ አስታወቁ። የፌድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔውን ያስተላለፈው አቶ ጌታቸው የሚመሩት ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ላይ ባቀረበው ክስ መሠረት ነው።...more0minPlay
February 25, 2026ለኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ የአጋርነት መዋጮ መሰብሰብ ተጀምሯልለኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ የባንክና ቴሌኮም አገልግሎቶችን ጨምሮ በተለያዩ ስልቶች የአጋርነት መዋጮ መሰብሰብ ተጀምሯል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኝ ተቋም ባልደረባ ባለፈው ወር ከደመወዛቸው 0.5% መቆረጡን ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል። ባለሙያዎች ተቋሙ እንደሚያስፈልግ ቢስማሙም መዋጮው ጫና እንደሚኖረው ተናግረዋል።...more0minPlay
February 25, 2026ያለኢንተርኔት መልዕክት ለመለዋወጥ የሚያስችሉ መተግበሪያዎችእነዚህ መተግበሪያዎች ኢንተርኔት ፈፅሞ በሌለባቸው ወይም ደካማ የኢንተርኔት መሰረተ ልማት ባላቸው አካባቢዎችም ያለ ያለኢንተርኔት መልዕክት ለመለዋወጥ የሚያግዙ ናቸው። መተግበሪያዎቹ በተፈጥሮ አደጋዎች የኃይል መቆራረጥ ሲኖር፣ ኢንተርት ሆን ተብሎ በሚዘጋበት ወይም ተደራሽነት በሌለበት ቦታ የሰዎች መስተጋብር ጠንካራ ሆኖ እንዲቆይ ያደርጋሉ።...more0minPlay
February 25, 2026የትራምፕ ዘለግ ያለ ንግግር በሐቅ አጣሪዎች ሲዳሰስየዩናትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በትናንትናው ምሽት ለአሜሪካ ነዋሪዎች እጅግ ዘለግ ያለ ንግግር አሰምተዋል። በንግግራቸው ከኢኮኖሚ፤ የአገር ውስጥ ደኅንነት አንስቶ እስከ ፍልሰተኞች፤ እንዲሁም የሰላም እና ጦርነት ጉዳዮችን ትንታኔ ሰጥተዋል። ሐቅ አጣሪዎች ምን አሉ? ሙሉ ዘገባውን በማገናኛው ያግኙ ።...more0minPlay
February 25, 2026በአማራ ክልል የጤና ተቋማት የጤና ባለሙያዎች የትርፍ ሰዓት ክፍያ ጉዳይበአማራ ክልል ልዩ ልዩ የጤና ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ የጤና ባለሙያዎች ከመስከረም ወር ጀምሮ የሚገባቸውን የትርፍ ሰዓት ክፍያ በአግባቡ አያገኙ አለመሆኑን በመጥቀስ ቅሬታ አቀረቡ። የጤና ባለሙያዎች ማህበር ጉዳዩን እስከ ክልሉ ምክር ቤት ማድረሱንና ተጨማሪ በጀት ከፌዴራል መንግስት እንዲመደብ ጥያቄ መቅረቡን ዐሳውቋል። ሙሉ ዘገባውን በማገናኛው ያግኙ...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,875 episodes available.