Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,875 episodes available.
February 23, 2026ማሕደረ ዜና፣ የዩክሬን ጦርነት አራተኛ ዓመት፣ መቆሚያ አለዉ ይሆን?150 ሺሕ የሚገመቱ የሩሲያ መደበኛ ወታደሮች፣50 ሺሕ ከሚሆኑ አማፂያን ጋር ተቀናጅተዉ ዩክሬንን ከሰሜን ከቤሎሩስ አቅጣጫ፣ከደቡብ ከክሬሚያ፣ ከደቡብ -ምሥራቅ ከዶንባስ፣ ከምሥራቅ ከራስዋ ከሩሲያ በአ,ራት አቅጣጫ አቃረጧት።2800 የተገመተዉ ታንክ፣ መድፍ፣ የአጭር ርቀት ሚሳዬልና መትረየስ ይፈንቀፈቅ ያዘ።...more14minPlay
February 23, 2026የየካቲት 16 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባበክረምት ኦሎምፒክ ጨዋታዎች የጀርመን ቡድን በርካታ የ4ኛ ደረጃዎችን ማስመዝገቡ የሚያስቆጭ ነው ተባለ ። በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ የአርሰናልና የማንቸስተር ሲቲ ፉክክር ተጠናክሯል ። እንደተለመደው ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ የዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ አሸናፊነታቸውን አስመስክረዋል ። ሙሉ ዘገባውን በድምፅና በጽሑፍ በማገናኛው ይከታተሉ ።...more0minPlay
February 23, 2026በኢትዮጵያ ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት ሠፋ ወይስ ጠበበ?ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት፤ የሚዲያ አስተዳደር እና ቁጥጥር በኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ 3ኛውን የፖሊሲ ዉይይት በሀዋሳ ከተማ ተካሄደ ፡፡ የሀዋሳ ዪኒቨርሲቲ ባዘጋጀው በዚሁ መድረኩ ላይ በዘርፉ የሚታዩ ተግዳሮቶችና የመፍትሄ አማራጮች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በኢትዮጵያ ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት ሠፋ ወይስ ጠበበ?...more0minPlay
February 23, 2026ለተሻለ ሁኔታ ወደ አረብ ሃገር የሚሰደዱ የአማራ ክልል ወጣቶችበአማራ ክልል ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ወሎ እና የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ ከ1,020 በላይ መምህራን በ2018 በጀት ዓመት ሥራቸውን ለቀው ወደ አረብ ሀገራትና ወደተለያዩ ከተሞች እየተሻለ ስራ ፍለጋ እንደሄዱ ተገለጠ። መምህራኑ ለሥራ መልቀቃቸው ዋነኛው ምክንያት የኑሮ ውድነትና የሚከፈላቸው ደመወዝ አለመመጣጠን እንደሆነ ተነግሮል።...more0minPlay
February 23, 2026ለዩክሬይን ይሰጣል የተባለዉ ብድር እና የአዉሮጳ ኅብረት የሚንስትሮች ስብሰባሩሲያ በዩክሬን ላይ እያካሄደችዉ ያለው ጦርነት ነገ ማክሰኞ አራተኛ ዓመቱን ይደፍናል። ሀንጋሪ እና ስሎቫክያ፤ ኅብረቱ ለዩክሬን ይሰጣል ያለዉን የ 90 ቢሊዮን ይሮ ብድር ዛሬ የአዉሮጳ ኅብረት አባል ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተቀመጡበት ስብሰባ ላይ አግደዋል። የሃንጋሪዉ ፕሪዚዳንት ቪክቶር ኦርባን ብድሩንም ሆነ ማዕቀቡን አግደዋል።...more0minPlay
February 23, 2026የአፍሪካ ቀንድ ለውጭ ኃይላት ፍላጎት ማስፈፀሚያነት ያለው ተጋላጭነትየኢትዮጵያና የሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች "በጋራ ቀጣናዊ የሰላም እና ደኀንነት ጉዳዮች ዙሪያ" መወያየታቸው ተገለፀ። በዉይይቱ ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን ግንኙነት "ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር በሚቻልበት" ዙሪያ መክረዋል። የአፍሪካ ቀንድ "የውጭ ኃይሎች መፋለሚያ ሜዳ መሆን የለበትም" ሲሉ የቱርክዬ ፕሬዝዳንት ሰሞኑን ተናግረዋል።...more5minPlay
February 23, 2026የኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እና ፓርቲዎች ተቃወሙየኢትዮጵያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አምስት የምርጫ ክልሎችን በተመለከተ ያሳለፈውን ውሳኔ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ፣ ሳልሳይ ወያነ እና ባይቶና ፓርቲዎች ተቃወሙ።...more0minPlay
February 22, 2026የአፍሪቃ ሕብረት ግጭቶችን ለማስቆም ለምን ተሳነው?ከተመሠረተ 63 ዓመታትን ያስቆጠረው የአፍሪቃ አህጉራዊ ተቋም የአፍሪቃ ሕብረት በአባል ሃገራት ውስጥ ለሚካሄዱ ግጭቶችን ማስቆም ባለመቻሉ እየተተቸ ነው። ተቋሙ ራዕይ በነበራቸው የቀድሞ መሪዎች የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ተብሎ ሲቋቋም አፍሪቃ እንደ አንድ ተባብራ ሰላም አንድነቷን ለመጠበቅ እንደነበር ይታሰባል።...more0minPlay
February 21, 2026አሜሪካ እጇን ያስገባችበት የኮንጎ የሰላም ስምምነት ይጸና ይኾን?በምሥራቃዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለዓመታት የዘለቀው ደም መፋሰስ እንዲቆም አዲስ የተስፋ ጭላንጭል አሳይቷል። ባለፈው ረቡዕ የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ/ም ተግባራዊ እንዲሆን የታቀደው የተኩስ አቁም ስምምነት፤ «ለመጨረሻ ጊዜ የተገኘ የሰላም ዕድል ይሆን?» የሚለው ጥያቄ የአለም አቀፍ ዲፕሎማቶችን ትኩረት ስቧል።...more0minPlay
February 21, 2026ደቡብ አፍሪካ ፊቷን ከአሜሪካ ወደ ቻይና አዙራ ይኾን ?በሁለቱ የዓለማችን ልዕለ ኃያላን የንግድ እና ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫ መሃል የገባችው ደቡብ አፍሪካ ፊቷን ወደ ምሥራቅ ታዞር ይኾን? የሚለው ጥያቄ አሁን የበርካቶችን ትኩረት የሳበ መስሏል።ላለፉት 20 ዓመታት ደቡብ አፍሪካ በዋሽንግተን እና በቤጂንግ መካከል ያለውን ግንኙነት በሚገርም ብልሃት ሚዛኑን ጠብቃ ማቆየቷ ነው የሚነገርላት።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,875 episodes available.