Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,875 episodes available.
February 21, 2026ነዋሪዎችን ያሰጋው በሰሜን ኢትዮጵያ ያጠላው የጦርነት ዳመናበትግራይ ክልል ሌላ ዙር ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል በርካታ የክልሉ ነዋሪዎች ስጋት ላይ መውደቃቸውን እየገለጹ ነው፡፡አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ አንዳንድ የክልሉ ነዋሪዎች ጦርነት ይከሰታል በሚል ስጋት ወደ አገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች እየወጡ መሆናቸውን ገልፀዋል።...more0minPlay
February 21, 2026በትግራይ አንዣበበ ያለውን የጦርነት ድባብ በሰላም እንዲፈታ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ጠየቀትግራይ ክልል ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዱ የሆነው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና በትግራይ ክልል ያንዣበበ" ያለው "አስፈሪ" የጦርነት ድባብ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲገታ ለዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና ተቋማት መሪዎች ግልጽ ደብድቤ ጽፏል።...more0minPlay
February 21, 2026በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ባቲ ወረዳ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በንጹሃን ላይ ያነጣጠረ እገታ፣ ግድያና ዝርፊያ እያደረሱ ነው ተባለበአማራ ክልል ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ባቲ ወረዳ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በንጹሃን ላይ ያነጣጠረ እገታ፣ ግድያና ዝርፊያ እያደረሱ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ።እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ፣ በተለይም በሞቱማ፣ ጀልደይቲ፣ ጉሬ እና መልካሉጎ ቀበሌዎች ታጣቂዎቹ እንደሚገድሉና እያገቱ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንደሚቀበሉ ተናግረዋል።...more0minPlay
February 20, 2026ከጦርነት ሥጋት ያልተላቀቀው ኢትዮጵያን፣ ሱዳንን እና ኤርትራን የሚያዋስነው አካባቢበኢትዮጵያ፣ በኤርትራና በትግራይ ክልል ዳግም "ተባብሷል" ያለው "ውጥረት" በቀጣናው ሌላ አውዳሚ ጦርነት ሊያስከትል ይችላል የሚል ሥጋት መፍጠሩን ዓለምአቀፍ ክራይስስ ግሩፕ የተባለው ድርጅት አሳሰበ። ድርጅቱ ተደማጭነት ያላቸው የአፍሪካ መንግሥታት በአፍሪካ ቀንድ ፍላጎት ካላቸው የውጭ ኃይሎች ጋር ፣ ሰላማዊ የዲፕሎማሲ ጥረት ማድረግ አለባቸው።...more0minPlay
February 20, 2026በኅብረቱ አዛውንቶች የተዘነጉ ወጣቶች ምሬት1.4 ቢሊዮን ግድም ነዋሪዎች ባሏት አፍሪቃ ሲሦው ወጣት ነው ። የአፍሪቃ ወጣቶች የአፍሪቃ ኅብረት የአብዛኞቻችንን ፍላጎት አላሟላም ሲሉ በተደጋጋሚ ይናገራሉ። ኅብረቱ ወጣቶቹ ላይ የተከሰተውን ቀውስ መፍታት ተስኖታል ሲሉ ይተቹታል ባለሞያዎች ። ሙሉ ዘገባውን በማገናኛው መከታተል ይችላል ።...more0minPlay
February 20, 2026እናት ፓርቲ "ለኢትዮጵያ" ወደተባለው የፓርቲዎች ቅንጅት መመለሱእናት ፓርቲ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት በአጭሩ "ለኢትዮጵያ" ወደተባለው የአራት ፓርቲዎች ቅንጅት መመለሱን ገለጠ።ከአምስቱ የቅንጅቱ መስራች ፓርቲዎች ሌላኛው በፈቃዱ ወጥቷል፤የፖለቲካ ድርጅቱ ፓርቲዎችን ላሰባሰበው ቅንጅት ምስረታ ያቀረበው ጉባኤ ያልተሟላና ከአባላት ቀረበ በተባለ ተቃውሞ ምክንያት ነበር ምርጫ ቦርድ ከቅንጅቱ ተሰርዞ የቆየው።...more0minPlay
February 20, 2026እየሰፋ የመጣው የምንዛሪ ቢሮዎች እና የባንኮች ልዩነትየኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች የብር የውጭ ምንዛሪ ከትይዩ ገቢያውና ከውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ጋር ልዩነቱ እየሰፋ መምጣቱ እየተስተዋለ ነው፡፡ ባለሙያዎች እንደሚሉት መንግስት ከውጭ ምንዛሪ አኳያ ተፈላጊውን የምንዛሪ መረጋጋት ለማስፈን በፖሊሲ አማራጮች እየወሰዳቸው ያሉ እርምጃዎች ከወደመጠናቀቅ እየተጠጋ ይገኛል፡፡...more0minPlay
February 20, 2026የተማሪዎች ምገባ በአማራ ክልልበአማራ ክልል በ1,330 ትምህርት ቤቶች የሚደረገዉ የተማሪዎች ምገባ፣ ከ 318 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተጠቃሚ በማድረግ የትምህርት ጥራትንና የተማሪዎችን ጤና እያሻሻለ መሆኑ ተነገረ። በኮምቦልቻ ከተማና በሰሜን ወሎ ዞኖች የተገኘው ተሞክሮ እንደሚያሳየው፣ ምገባው ከተጀመረ ወዲህ ተማሪዎች ትምህርት የማቋረጥና የማርፈድ ችግራቸው ቀንሷል።...more0minPlay
February 20, 2026ነዳጅን ከመደበኛ ዋጋ የመሸጥ ፈተናበኢትዮጵያ ነዳጅን መንግስት ከተመነው መደበኛ ዋጋ ውጭ የሚሸጡ ማደያዎች በእለት ተእለት ስራዎቻቸው ላይ ፈተና መደቀናቸውን አሽከርካሪዎች እና የተሽከርካሪ ባለንብረቶች ይገልጻሉ፡፡ እንደ አስተያየት ሰጪዎቹ በዚህ ከተመን በላይ ክፍያ በሚጠየቅባቸው በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል በሚገኙ ማደያዎች ጋር በሚፈጠር ንትርክ አንዳንዴ ስራቸው ይስተጓጎላልም፡፡...more0minPlay
February 19, 2026ምክክር ኮሚሽን የትግራይን አጀንዳዎች ለመሰብሰብ ያቀረበው ምክረ ሐሳብሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የትግራይ ክልልን አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ አዲስ አበባ ውስጥ ለማድረግ አማራጭ ሐሳብ አቅርቧል። ኮሚሽኑ በክልሉ ያለው "የተሳታፊ ልየታ ተግባር ባለመከናወኑ" እዚህ ውሳኔ ላይ መድረሱን ገልጧል።የፖለቲካ ፓርቲና የሲቪክ ድርጅቶች ውሳኔውን በዐወንታ አልተመለከቱትም። ሆኖም ሥራው ጭራሽ ከሚቀር በሚል እቅዱን የደገፉ አሉ።...more4minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,875 episodes available.