Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,875 episodes available.
February 19, 2026በተገጣጠመው የዐቢይ ጾምና የረመዳን ጾም መጀመሪያ ላይ በአማራ ክልል የናረው የሸቀጦች ዋጋ ንረት‹‹የእኛ አካባቢ ነጋዴዎች አጋጣሚዎችን በአላትን አፅዋማትን በመጠቀም ያው የተለየ ትርፍ ለማግኘት ነው ጥረት የሚያደርጉት ከሌሎች አገሮች ተሞክሮ ብታይ እንደዚህ አይነት ሁነቶች በአል ሲኖር የንግድ ተቋማት የተለየ ቅናሽ ያደርጋሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን በተቃራኒው ነው ፤ ይህን አጋጣሚ ተጠቅሞ የተትረፈረፈ ትርፍ ማግኘት ነው፡፡››...more0minPlay
February 19, 2026የየካቲት 12 ሰማዕታት ፍትሕ እንዲያገኙ የሚደረግ ዓለም አቀፍ ዘመቻ''ለዚህ ሁሉ ወንጀል፣ ኢትዮጵያ ያገኘችው ተገቢ የሆነ ካሳ የለም። ዋናው ነገር ፍትሕ እንዲገኝ፣ ያ ሁሉ ጭፍጨፋ፣ያ ሁሉ ወንጀል ተከናውኖ ዝም ብሎ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ማለት ተገቢ አለመሆኑን በማስረዳት በልዩ ልዩ መንገድ ጥረት ተደርጓል።''...more0minPlay
February 19, 2026የኮሪደር ልማት - ፈንድቃ ወደነበረበት ሊመለስ መሆኑ ተሰማመዲና አዲስ አበባ ካሳንችስ እንብርት ላይ የነበረዉ እና በተለይ ከተለያዩ ዓለም ሃገራት ለሚመጡ ዜጎች የኢትዮጵያን ሙዚቃ ሥነጥበብ በማስተዋወቁ የሚታወቀዉ የባህል ማዕከል ፈንድቃ፤ አዲስ አበባ የጀመረችዉን የኮሪደር ልማት ተከትሎ ከፈረሰ እና ከከነበረበት ከካሳንችስ ከተነሳ በኋላ፤ ወደነበረበት ወደቀደመዉ ቦታ ሊመለስ መሆኑ ተሰምቷል።...more12minPlay
February 19, 2026ከሶማሊያና ሳውዲ አረቢያ ወታደራዊ ስምምነት ጀርባ ምን አለ?ሶማሊያ እና ሳዑዲ አረቢያ እስራኤል ለሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅናን ከሰጠች ሳምንታት በኋላ የወታደራዊ ትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል። «ሶማልያ ከተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ጋር ያላትን የሻከረ ግንኙነት ተከትሎ፤ ከሳዑዲ አረቢያ ጋር ባላት አዲስ ግንኙነት ተጠቃሚ ለመሆን ስትሞክር ሳዉዲ አረብያ ደግሞ ተጽእኖዋን ለማስፋፋት እየሞከረች ነው።»...more6minPlay
February 19, 2026የጠቅላይ ሚኒስቴር ዐብይ አህመድ(ዶ/ር) የምዕራብ ኦሮሚያ ጉብኝትበቀሌም ወለጋ፣በምዕራብና ምስራቅ ወለጋ ጉብኝት ያደረጉት ጠቅላይ ሚነስቴር ዶ/ር አብይ ባለፉት 3 አስርት ዓመታት ወለጋ የተሟላ ሰላም ሳይገኝ በመቆየቱ በልማት ወደኀላ መቅረቱን አመልክተዋል፡፡ በአካባቢው ፀጥታ በሰላም ወጥቶ መግባት ጉዳይ ችግር ሆኖ መቆየቱን በመግለጽ ልዩነቶችን በንግግርና ድርድር በመፍታት ወደ ልማት መግባት ያሰፈልጋል ብለዋል፡፡...more4minPlay
February 19, 2026“የጦርነት ድባብ”፤ የኦነግ ማሳሰቢያበግጭቶች ብዙዎች መፈናቀላቸውን የጠቀሰው ኦነግ በግጭቱ ሰላማዊ ዜጎች ተጠቅተዋል ብሏል።፡ በጨፌው የመንግስት ተጠሪ አቶ ከፍያለው ተፈራ በአዳማ ችግሮችን «ከሚመለከታቸው ጋር ለመወያየት በተደረገ ጥረት የተፈቱ ችግሮች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡ «ቀሪ ችግሮችን ለመፍታት የሕግ የበላይነትን በማስከበር ጠንከር ያለ እርምጃ ተወስዷል” ብለዋል።...more0minPlay
February 18, 2026በኢትዮጵያ ጦርነት ዳግም ሲያንዣብብ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች እና ኢኮኖሚ ካሁኑ ዳፋው ተጭኗቸዋልበኢትዮጵያ ሌላ ጦርነት ሲያዣብብ በትግራይ ክልል የነዳጅ ምርቶች፣ ጤፍ እና ዘይትን ጨምሮ የምግብ ግብዓቶች በአንድ ሳምንት የዋጋ ጭማሪ ታይቶባቸዋል። በክልሉ ከኤቲኤም ገንዘብ ማግኘት አይቻልም። ባንኮች ደንበኞቻቸው ወጪ የሚያደርጉትን የገንዘብ መጠን ገድበዋል። ለንግድ እና አገልግሎቶች ክፍያ የሚፈጸመው በሞባይል የገንዘብ ማዘዋወሪያዎች ሆኗል።...more0minPlay
February 18, 2026አሳሳቢው የልጆች የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አጠቃቀምጥናቶች እንደሚያሳዩት ልጆች የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ይዘትን ለረጅም ጊዜ መመልከት፤ ባህሪን እና የአእምሮ ጤናን በዘላቂነት ሊጎዳ ይችላል።ጉዳቱ በተለይም እድገቱ ባልተጠናቀቀ የልጆች አእምሮ ላይ በመሆኑ ደግሞ የሚመጣው መዘዝ ከፍተኛ መሆኑን ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ።ይህ ያሳሰባቸው ሀገራት ልጆጆን ከዲጅታል መድረኮቹ የሚያግዱ ህጎችን እያወጡ ነው።...more0minPlay
February 18, 2026የቱርክዬ ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝትየቱርክዬ ፕሬዚዳንት፦ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸው «ለአካባቢው ሰላምና መረጋጋት አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት» ገለጡ ። ትናንት ኢትዮጵያን የጎበኙት የቱርኪዬ ፕሬዚዳንት ረሲብ ጣይብ ኤርዶሃን ኢትዮጵያ በምትገኝበት ክፍለ ዓለም አገራቸው፦ «አዲስ ግጭቶች እና አዲስ ህመም» ያሉትን መጨመር እንደማትፈልግ ገለጡ።...more0minPlay
February 18, 2026ደቡብ ወሎ ዞን ከ276 ሺህ በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት አልተመለሱምበደቡብ ወሎ ዞን በጦርነት ምክንያት ተዘግተው የነበሩ 464 ትምህርት ቤቶች በሀገር ሽማግሌዎች ጥረት ዳግም ቢከፈቱም፣ ከ276 ሺህ በላይ ተማሪዎች ግን አሁንም በፀጥታ ስጋትና በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ወደ ትምህርት ገበታቸው አለመመለሳቸው ተገለጸ።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,875 episodes available.