Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,875 episodes available.
February 14, 2026የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተባበሩት መንግሥታትን ሲያብጠለጥሉ የቻይና አቻቸው ተከላከሉበሙኒክ የጸጥታ ጉባኤ የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ የተባበሩት መንግሥታት በዓለም ዙሪያ የሚካሔዱ ግጭቶችን የመፍታት አቅም የለውም ሲሉ በኃይል ተችተዋል። የቻይና አቻቸው ዋንግ ይ ግን “የተባበሩት መንግሥታት ባይኖር ኖሮ ዓለም ጠንካሮች በደካሞች ላይ ወደሚበረቱበት የጫካ ሕግ ይመለስ ነበር” ሲሉ ተከላክለዋል...more0minPlay
February 14, 2026በአህጉሪቱ እየተባባሱ የቀጠሉት የጸጥታ ችግሮች ጉዳይ አሳሳቢ ነው፤ የአፍሪቃ መሪዎች ጉባኤበ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የመክፈቻ ስነስርዓት ላይ የተናገሩ መሪዎች ገልፀዋል። እ.አ.አ በ2030 ግጭቶችን ለማስቆም የወጣው እቅድ ትግበራ ወደ ኋላ መቅረቱን የሕብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር አሊ መሐሙድ ዮሰፍ ተናግረዋል ። እነዚሁ የጸጥታ ችግሮች ለሁለት ቀናት የሚካሄደው ጉባኤ ዋነኛ አጀንዳ እንደሚኾኑ ይጠበቃል።...more4minPlay
February 14, 2026በአፍሪካ ጠብ መንጃዎችን ዝም ማሰኘት አሁንም ፈታኝ እንደሆነ ማሕሙድ አሊ ይሱፍ ተናገሩበኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት በሚካሔደው አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ የውኃ ጉዳይ ዋንኛ አጀንዳ ቢሆንም በአኅጉሩ የሚካሔዱ ግጭቶች፣ መፈንቅለ-መንግሥቶች ትኩረት ተሰጥቷቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ባሰሙት ንግግር ኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት አለባት የሚል አቋማቸውን ለጉባኤው ተሳታፊዎች ገልጸዋል።...more0minPlay
February 13, 2026በደብረታቦር ከተማ የተከሰተው የጸጥታ አለመረጋጋት እና የነዋሪው አስተያየትረቡዕ የካቲት 4 /2018 ዓ.ምበመንግስት የፀጥታ ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ከነበረ ሰዓታት ከፈጀ ዉጊዪያ በኋላ በደብረ ታቦር ከተማ አንፃራዊ ሰላም መስፈኑና ባንኮች አገልግሎት መጀመራቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የመንግስት ሰራተኞች ግን ገና ወደ ስራ ገበታቸው አልተመለሱም።...more0minPlay
February 13, 2026የጎዳና ላይ ውይይት በዩጋንዳ: ጥቃት መፈፀም ወንጀል ከሆነ ለምን እንደ ቀላል ነገር ይታለፋል?የዶይቸ ቬለ የወጣቶች ዝግጅት በቅርቡ ዩጋንዳ ውስጥ አንድ የጎዳና ላይ ውይይት አካሂዶ ነበር። ውይይቱም በሴቶች ላይ የሚፈፀም ፆታዊ ጥቃት ላይ አተኩሯል። በውይይቱ ተጎጂዎች፤ ጥቃት ፈፃሚ፤ ጋዜጠኛ እና የፖሊስ ባልደረባ ተሳትፈዋል።...more11minPlay
February 13, 2026የኢትዮጵያውያን ሕብረትና የሽግግር ቅድመ ሁኔታ ላይ የተደረገ ምክክርየኢትዮጵያ ጉዳይ ይመለከተናል የሚሉ ኅይሎች፣ በአንድነት በመሰባሰብ፣ አገሪቷ ገጥሟታል ካለው የመበታተን አደጋ ለማዳን የመፍትሄ አካል እንዲሆኑ የኢትዮጵያ ትብብር ንቅናቄ ጥሪ አቀረበ።ንቅናቄው በቅርቡ ባካሄደው ጉባኤ፣ የኅብረት አስፈላጊነት እና የሽግግር ጊዜ ቅድመ ሁኔታ በሚሉ ጉዳዮች ላይ መክሯል።...more4minPlay
February 13, 2026የአውሮጳ መሪዎች ከኤኮኖሚ ጥገኝነት ለመላቀቅ የያዙት መንገድየአውሮጳ ህብረት መሪዎች ትናንት ባክሄዱት መደበኛ ያልሆነ ስብሰባ በተለይ የነጻ ገበያንን ማጠናከር፣ የህብረቱን ኢኮኖሚያዊ ጥገኝነት መቀነስና ተወዳዳሪነትን ማጎልበት በሚቻልባቸው ፖሊሲዎችና የማሻሻያ ፕርግራሞች ላይ ተወያይቷል።...more5minPlay
February 13, 2026ሕዝባዊ ወያነ አርነት ትግራይ ለአፍሪቃ ህብረት የላከው ደብዳቤ እና አንድምታውህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ህወሓት የአፍሪካ ህብረት በሰሜን ኢትዮጵያው ትግራይ ክልል እየከፋ ለመጣው ውጥረት ትኩረት ሰጥቶ እልባት እንዲያበጅ ጠየቀ፡፡ህወሓት ትናንት ሓሙስ የካቲት 05 ቀን 2018 ዓ.ም. ለህብረቱ ሊቀመንበርና አባላቱ በላከው ግልጽ ደብዳቤ የፕሪቶሪያው ስምምነት በአስቸኳይ እንዲተገበር ጠይቋል፡፡...more5minPlay
February 13, 2026ለጸጥታ ቅድሚያ ይሰጣል ተብሎ የሚጠበቀው የአፍሪቃ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤበአህጉሪቱ መፍትሔ ሳያገኙ የቀጠሉት የጸጥታ ችግሮች የ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ቀዳሚ አጀንዳዎች እንደሚኾኑ ዲፕሎማቶችና ተንታኞች ተናግረዋል።ጉባኤው ለነዚሁ የጸጥታ ችግሮች እልባት ማስገኘት የተሳናቸውን የህብረቱን የሠላምና ጸጥታ እንደዚሁም የአስተዳደር መዋቅሮች ለማሻሻል በሚቀርበው ምክረ ሐሳብ ላይሞ እንደሚነጋገር ተገልጿል ።...more5minPlay
February 13, 2026የአፍሪካ ኅብረት ፖለቲካዊ ውይይት ለመጥራት እና ለማመቻቸት እርምጃ እንዲወስድ ህወሓት ጠየቀየግጭት መነሾ የሆኑ “ፖለቲካዊ፣ የጸጥታ እና የአስተዳደር” ልዩነቶችን ለመፍታት ግጭት የማቆም ሥምምነቱን ፈራሚዎች ፖለቲካዊ ውይይት እንዲያደርጉ ለመጥራት እና ለማመቻቸት የአፍሪካ ኅብረት እርምጃ እንዲወስድ ህወሓት ጠይቋል። ህወሓት ጥሪውን ያቀረበው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኅብረት 39ኛ መደበኛ ጉባኤን ለማዘጋት ስትሰናዳ ነው።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,875 episodes available.