Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,881 episodes available.
February 12, 2026በኦሮሚያ ክልል ከአመያ ወረዳ የተፈናቀሉ ከ1,200 በላይ ሰዎች ወደ ቀያቸው ተመለሱከአመያ ወረዳ ተፈናቅለው በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ተጠልለው ከቆዩ ተፈናቃዮች ከ1,200 በላይ ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን የአካባቢው ባለሥልጣን ገለጹ። ሁለት ወደ ቀያቸው የተመለሱ ነዋሪዎች የደሕንነት ዋስትና እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸዋል። ለተመላሾቹ ደሕንነት አካባቢዎቹን የሚቆጣጠረው የጸጥታ ዕዝ ኃላፊነት እንደወሰደ አንድ ባለሥልጣን ተናግረዋል...more4minPlay
February 11, 2026“ማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እያመጣን ትርፋማ መሆን እንችላለን” የላቭግራስ ኢትዮጵያ መሥራች ዮናስ አድማሱየብሪታኒያ ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት (BII) ለላቭግራስ ኢትዮጵያ የአምስት ሚሊዮን ዶላር ፋይናንስ እንደሚያቀርብ አስታውቋል። ኩባንያው በሱሉልታ በሚገኘው ፋብሪካ ከጤፍ ፓስታ እና ኩኪሶችን ጨምሮ የተለያዩ ምግቦች እያመረተ ለዓለም ገበያ የሚያቀርብ ነው። መሥራቹ ዮናስ አድማሱ በቢኤንፒ ፓሪባ፣ ጄፔ ሞርጋን እና ክሬዲት ስዊዝ ባንኮች ሠርተዋል።...more0minPlay
February 11, 2026የሱዳን የርስ በርስ ግጭት፤ አፍጦ የመጣው ጣልቃ ገብነት እና ጂኦፖለቲካውበሱዳን እየተካሄደ ባለው የርስ በርስ ግጭት የውጭ መንግስታት ጣልቃ ገብነት በጭምጭምታ ይነገር እንደነበር የሚያስረዱት ተንታኞች ግጭቱ በአፍሪካ ቀንድ የውክልና ጦርነት ሊያስከትሉ ከሚችሉ ክስተቶች ማሳያዎች አንዱ ሊሆን ይችላል ሲሉ ያስጠነቅቃሉ ።...more5minPlay
February 11, 2026ሁለት ሳምንት ሞላን ፤ የሰብአዊ ድጋፍ አልቀረበልንም ፤ ተፈናቃዮችየፌደራል የጸጥታ ኃይሎች ከአላማጣ ፣ኮረም እና ሌሎች አካባቢዎች ለቆ መውጣቱን ተከትሎ ለመፈናቀል የተገደዱ ነዋሪዎች ለብርቱ ሰብአዊ ችግር መዳረጋቸውን አመለከቱ። ተፈናቃዮቹ እንዳሉት ወደ አቅራቢያ ከተሞች ከሸሹ ሁለት ሳምንት ቢሞላቸውም ምንም አይነት የሰብአዊ ድጋፍ እንዳልቀረበላቸው ተናግረዋል።...more4minPlay
February 11, 2026የአብን የፖርላማ ተመራጮች ቀጣዩን ምርጫ አስመልክቶ የወሰዱት አቋምበሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተመራጭ የሆኑት ዶክተር አበባው ደሳለው በመጪው ጠቅላላ ምርጫ ኢሕአፓን ወክለው እንደሚወዳደሩ ትናንት ይፋ አድርገዋል። የፓርላማ አባሉ፤ "ባለፉት አራት ዓመታት ከአብን አመራሮች ጋር በፍፁም ተገናኝቼ አላውቅም" ሲሉ ሌላ ፓርቲን ለመቀላቀል ምክንያት ያሉትን ጠቅሰዋል።...more4minPlay
February 10, 2026የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የቀረው ጊዜ እና ቀጣይ የሚጠበቁ ሥራዎችየኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለአንድ ዓመት የተራዘመለት የሥራ ጊዜው ሊያበቃ አንድ ሳምንት ብቻ ቀርቶታል።ኮሚሽኑ ሥራውን እንዲያጠናቅቅ በሚል የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ዓመት የካቲት 11፤ 2017 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰብ ነበር ጊዜው ለአንድ ዓመት ያራዘመው።ያም ሆኖ ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል ስራ አልጀመረም።...more5minPlay
February 10, 2026የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ የዘርፉ ገቢያ የመግባታቸው ስጋቱና ተስፋየውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ ውስጥ ገብተው እንዲሰሩ የሚፈቅደውን ሕግ የኢትዮጵያ ፓርላማ ካፀደቀበት ታህሳስ ወር 2017 ዓ.ም. በኋላ፤ ባለፉት 14 ወራት በርካታ አቅማቸው የደረጀ የውጭ ባንኮች ከ130 ሚሊየን ህዝብ በላይ ባለው በኢትዮጵያው ገቢያ ይሻማሉ የሚለው ግምት በብዙዎች ዘንድ ከፍ ብሎ ነበር፡፡...more0minPlay
February 10, 2026የህወሓት ወቀሳና የዳግም ጦርነት ስሥጋትህወሓት፤ በትናንቱ መግለጫው “የትግራይ ህዝብ እና የክልሉ አመራሮች ያለውን ልዩነት ለመፍታት ውይይት ወሳኝ ነው የሚል አቋም ባሳዩበት ባሁን ወቅት የፌዴራል መንግስት ይህን ወደ ጎን ብሎ ለሌላ ዙር ጦርነት እየተዘጋጀ ነው” ሲል ወቅሷል...more0minPlay
February 10, 2026በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ለምርጫ እየተዘጋጁ ነዉ ተባለባለፉት 2 ዓመታት በአማራ ክልል ተፈጠረው የፀጥታ ችግርበገጠርም ሆነ በከተማ ተንቀሳቅሶ የምርጫ ቅስቀሳና የምርጫሂደቱን ለመለወጥ የሚያስችል ሁኔታን እንዳይኖር ምክንያት ሊሆንአይችልም ወይ ስንል የጠየቅናቸው የአማራ ክልል የሚገኙየፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ተስፋሁ አለምነህአሁን ያለው ሁኔታ ምርጫ ከማካሄድ የሚያግድ አይደለም ይላሉ፡...more4minPlay
February 10, 2026አዲሱ የአውሮፓ ህብረትና የህንድ የንግድ ስምምነትየአውሮፓ ህብረትና አባል መንግስታቱ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ያሳለፉትን የታሪፍ ውሳኔ ቢያንስ እንዲያሻሻሽሉ እየጎተጎቱ ነው።በሌላ በኩል የአውርፓ ህብረት ከሌሎች አገሮች ጋር ሲካሂዱ የቆዩ የንግድ ድርድሮችን በመቋጨት አዳዲስ ስምምነቶንም በማድረግ አማራጭ የንግድ መስመሮች እና ገበያዎችን እያፈላለገ ነው።...more9minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,881 episodes available.