Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,875 episodes available.
February 06, 2026የነዳጅ ዕጥረት በትግራይ“ማደያ ውስጥ ነዳጅ የሚባል ነገር የለም” የሚሉት አስተያየት ሰጪው ነዋሪ እንደ አፋር ካሉ አጎራባች ክልሎች ተቀድተው በግለሰቦች በጄሪካን ከሚያስገቡት ሰዎች ብቻ እጅግ በውድ ዋጋ እየተገዛ ነው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጠውም ብለዋል፡፡...more0minPlay
February 06, 2026„ውጤታቸው ከ90 በላይ የሆኑ ለዚህ ፕሮግራም ቢያመለክቱ የመመረጥ እድላቸው ሰፊ ነው“ የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ ቢኒያም ሎሊሶ“በ15 ዓመቴ የ9ኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ነፃ የትምህርት ቱቶሪያል የሚሰጥ ፕሮጀክት ጀምሬ ነበር። “ ይላል ቢኒያም ሎሊሶ። ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚገኘው የል ዩኒቨርሲቲ የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ ነው። በኢትዮጵያ የክረምት ወቅት ወደ ኢትዮጵያ እየተመላለሰ አዲስኮደር (AddisCoder) በተባለው ተቋም በበጎ ፍቃደኝነት ስልጠናም ይሰጣል።...more0minPlay
February 06, 2026በአፋር ክልል በስድስት ወራት ውስጥ ከ16 ሺህ በላይ ህገወጥ ስደተኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ መደረጉንበአፋር ክልል ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ በህገወጥ መንገድ ድንበር ሊያቋርጡ የነበሩ ከ16 ሺህ በላይ ዜጎች በቁጥጥር ስር ውለው ወደመጡበት እንዲመለሱ መደረጉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ከስደተኞቹ በተጨማሪ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ የተሳተፉ ደላሎችና ተሽከርካሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።...more0minPlay
February 06, 2026በሽብር ወንጀል የተከሰሱ ሰዎች የመከላከያ ዝርዝር እንዲያቀርቡ መታዘዙንተከሳሾቹ የመከላከያ ዝርዝር እንዲያቀርቡ ከ ሚያዝያ 26 እስከ 30 ቀን 2018 ቀጠሮ ተሰጥቷል ያሉት ከተከሳሽ ጠበቆች አንደኛው ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ሰለሞን ገዛኸኝ፤ 51 ዱም ሰዎች የተከሰሱበት የወንጀል አንቀጽ የቅጣት ደረጃ "ዕድሜ ልክ እሥራት እና ሞት የሚያስቀጣ" ድንጋጌ ነው ብለዋል።...more0minPlay
February 05, 2026የመጭውን ጠቅላላ ምርጫ የፀጥታ ኹኔታ የተመለከው ውይይትብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚካሄድባቸውን አካባቢዎችን "የፀጥታ ኹኔታ" በተመለከተ "ከባለድርሻ አካላት ጋር" ሰሞኑን ውይይት አድርጓል።ውስን የመገናኛ ብዙኃን ለመክፈቻው ብቻ ተጠርተው ውይይቱ ላይ ባልተጋበዙበት በዚህ ውይይት ላይ ምን ምን ጉዳዮች ተነሱ?...more0minPlay
February 05, 2026ቀጣዩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ እና የፀጥታው ተግዳሮትኢትዮጵያ በቀጣይ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ሰባተኛ ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ በዝግጅት መሆኗን በምርጫ አስፈጻሚው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል አሳውቃ እየተንቀሳቀሰች ነው፡፡ በዚህ ላይ አስተያየታቸውን የሚሰጡ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫውን ለማድረግ አስቻይ የፀጥታ ሁኔታ የለም በማለት ቅሬታ እያቀረቡ ነው፡፡...more0minPlay
February 05, 2026ብሔራዊ ቋንቋና ገለልተኛ የሕዝብ ቆጠራን ጨምሮ 17 አጀንዳዎች ለምክክር ኮሚሽን ቀረቡበቅርቡ ከመንግሥት ጋር "የሰላም ስምምነት" መፈረሙን የገለፀው "የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት" የተባለዉ ታጣቂ ኃይል አካል የሆነ ቡድን "አማርኛ ብሔራዊ ቋንቋ እንዲሆን፣ ገለልተኛ የሕዝብ ቆጠራ እንዲከናወን የሚሉትን ጨምሮ 17 አጀንዳዎችን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማስረከቡን ገለፀ።...more0minPlay
February 05, 2026የጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ በ9ኛ እና በ11ኛ ክፍል የታሪክ መጽሐፍት ውስጥ የተወሰኑ ምዕራፎችን አገደበደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ በ9ኛ እና በ11ኛ ክፍል የታሪክ መጽሐፍት ውስጥ የሚገኙ የተወሰኑ ምዕራፎች ለተማሪዎች እንዳይሰጡ አገደ ፡፡ መምሪያው እገዳውን የጣለው በመማሪያ መጽሀፍት ውስጥ “ የውሸት ታሪኮች” ተጽፈዋል በሚል ነው ፡፡...more0minPlay
February 05, 2026በገዳ ስርዓት ላይ በርካታ ጥናቶችን ያደረጉት ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ ሲታወሱየኦሮሞ የገዳ ስርዓትን ለግማሽ ምዕተ-ዓመት በማጥናት ለዓለም ያስተዋወቁት ትውልደ ኤርትራዊው ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ ህልፈተ ህይወታቸው መሰማቱ በበርካቶች ዘንድ ሀዘን ፈጥሯል፡፡ተመራማሪው የገዳ ስርዓት በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ፣ ትምህርት እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) እንዲመዘገብ አይነተኛ ሚና መጫወታቸውም ይነገራል።...more0minPlay
February 04, 2026የግል አበዳሪዎች ኢትዮጵያን ሊከሱ እንደሚችሉ ቢገልጹም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የአከፋፈል ሽግሽግ ይጠብቃሉጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያን ዕዳ ለማሸጋሸግ በሚደረገው ጥረት “በሁለት ዓመት ይከፈል የነበረው ዕዳ እንደየአበዳሪው ሁኔታ እስከ 15 ዓመት እንዲራዘም ሥምምነት” መፈጸሙን ተናግረዋል። የግል አበዳሪዎች ግን ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር ያደረጉት ሥምምነት ውድቅ ከሆነ በኋላ በእንግሊዝ ፍርድ ቤት ክስ ሊመሠርቱ እንደሚችሉ ገልጸዋል።...more11minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,875 episodes available.