Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,875 episodes available.
February 09, 2026ኢትዮጵያ ቅዳሜ ዕለት ለኤርትራ የጻፈችው ደብዳቤ በሰላምና ደኅንነት ባለሙያ ዕይታየኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያቀረቡትን ክስ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር “ሐሰት እና የተቀነባበረ” በማለት አጣጥሏል። ዶክተር ጌዲዮን የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር ዘልቀው እንደገቡ እና ለታጣቂ ቡድኖች ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸው ነበር።...more0minPlay
February 08, 2026የትግራይ ግጭት እና ዘላቂው መፍትሔየፌደራል ኃይሎች ከአወዛጋቢዎቹ ከአላማጣ እና ኮረም እንዲሁም ከሌሎች አጎራባች ከተሞች መውጣታቸው ከተሰማ በኋላ ነዋሪዎች ጦርነት ይቀሰቀሳል በሚል ከከተሞቹ መሸሽ መጀመራቸው ሌላው ስጋቱ እንዲጨምር ያደረገ ክስተት ነበር። በትግራይ የድሮን ጥቃቶች በሁለት አካባቢዎች ተፈጸሙ የመባሉ ዜና በሀገር ውስጥም በውጭም ጉዳዩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎታል።...more0minPlay
February 08, 2026ኤርትራ ሰራዊቷን በአስቸኳይ ከሉአላዊ ግዛቶቿ እንድታስወጣ ኢትዮጵያ አሳሰበችኤርትራ በአስቸኳይ ሰራዊቷን ከሉአላዊ ግዛቶቿ እንድታስወጣ ኢትዮጵያ አሳሰበች። ኤርትራን «ግልጽ ጥሰት በመፈጸም» በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍል ከሚንቀሳቀሱ አማጽያን ጋር አብራለች ስትል ኢትዮጵያ ከሳለች።...more0minPlay
February 07, 2026ሩስያና አሜሪካ፥ አፍሪቃን ለመቆጣጠር ሩጫሩሲያ ቀድማ እግሯን ባደላደለችባቸው የሣኅል አገራት ጎዳና ላይ ዩናይትድ ስቴትስም መገስገስ ትሻለች ። ከማሊ፣ ከኒጀር እና ከቡርኪናፋሶ ላይ ያላትን አቀራረብም ከወታደራዊ ኹንታው ጋር ቢሆንም እንደገና እያስተካከለች ነው ።...more0minPlay
February 07, 2026ጥቃት በናይጄሪያ መንደሮች፥ የጽንፈኞች ጥቃትከሰሞኑ ናይጄሪያ ውስጥ እስልምና አክራሪ ታጣቂዎች በአብዛኛው ሙስሊሞች በሚኖሩባቸው መንደሮች ውስጥ ባደረሱት ጥቃት ከ160 በላይ ስለመገደላቸው ተዘግቧል ። ጥቃት አድራሾቹ በዎሮ እና ኑኩ በተሰኙት አብዛኛዎቹ ሙስሊሞች በሚኖሩባቸው መንደሮች ውስጥ ቤት ለቤት በመዞር ቤቶችን እና ሱቆችን ለኩሰው በእሳት አቃጥለዋል ።...more0minPlay
February 07, 2026የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ወደ 10.2% ከፍ ተደርጎ ስለተከለሰው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት ትንበያ ምን ይላሉ?የኢትዮጵያ መንግሥት የኢኮኖሚ ዕድገት ትንበያውን ወደ 10.2 በመቶ ከፍ አድርጎ እንደከለሰ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተናግረዋል። የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እና መንግሥት ተግባራዊ የሚያደርገውን ማሻሻያ በቅርብ የሚከታተሉ ባለሙያዎች ግን ጥያቄ አላቸው።...more0minPlay
February 07, 2026በኢትዮጵያ ሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ ከባድ ጥሰቶች አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሰዋል ተባለኢትዮጵያ ውስጥ በሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ ከባድ ጥሰቶች፣ ግድያ፣ የአካል ጉዳተኝነት፣ ጾታዊ ጥቃት፣ ጠለፋ እና የሰብአዊ አቅርቦት መከልከል አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መብቶች ኮሚቴ ገለፀ። ኮሚቴው መሰል ከባድ ጥሰቶችን ለማቆምና ለመከላከል ኢትዮጵያ ተግባራዊ መሆን የሚገባውን ዓለም አቀፍ ሕግ እንድታከብር አሳስቧል...more0minPlay
February 07, 2026ትራምፕ ኦባማን በተመለከተ የለጠፉትን የዘረኝነት ቪዲዮ ከማኅበራዊ ገፃቸው አጠፉትራምፕ ኦባማን በተመለከተ የለጠፉትን የዘረኝነት ቪዲዮ ከማኅበራዊ ገፃቸው አጠፉ። ትራምፕ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እና ባለቤታቸው ሚሼል ኦባማን ዝንጀሮ አስመስሎ የሚያሳየውን ቪዲዮ ያጠፉት ከዲሞክራቶችም ሆነ ከሪፐብሊካኑ ተቃውሞ ማስነሳቱን ተከትሎ ነው። ያም ሆኖ ትራምፕ ለዘረኝነት ቪዲዮው ይቅርታ እንደማይጠይቁ ተናግረዋል።...more0minPlay
February 06, 2026ስለሰሜን ኢትዮጵያ ጉዳይ የመንግሥታት አስተያየትባለፈው ሳምንት በሰሜን ኢትዮጵያ የተስተዋሉት ክስተቶች "ለሰላምና መረጋጋት ቀጣይነት ያለው ቁርጠኝነት አስፈላጊ መሆኑን የሚያስታውሱ ናቸው" ሲሉ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ተናገሩ።...more0minPlay
February 06, 2026የአሜሪካና የኢራን ቀጥተኛ ያልሆነ ውይይትዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በኦማን ባለሥልጣናት አማካንነት በሙስካት ያደረጉት ድርድር ተጠናቋል። በውይይቱ የተካፈሉት የአሜሪካና የኢራን ልኡካን ከኦማን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በተናጠል የተነጋገሩ ሲሆን ወደፊት ሊነጋገሩ በሚችሉ አጀንዳዎች ላይ መወያየታቸውንና የነበራቸውን ሰፊ ልዩነት መጥበቡን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገልጿል።...more0minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,875 episodes available.