Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,875 episodes available.
February 12, 2026ኢትዮጵያ በ1920 ዎቹ በጀርመን ዲፕሎማት ዕይታኢትዮጵያ በ1920 ዎቹ በጀርመን ዲፕሎማት ዕይታ በሚል 51 ታሪካዊ ፍቶግራፎች አዲስ አበባ በሚገኘው ፈንዲቃ የባሕል ማዕከል ውስጥ በዚህ ሳምንት ለዕይታ ቀርበዋል።ምስሎች በዚያን ዘመን የነበረውን የኢትዮጵያን ሕይወት ፣ የከአዲስ አበባን ቀደምት ገጽታ፣የመንግሥታት ደብዳቤዎች፣ የሃይማኖት ክብረ በዓላት ጨምሮ ታሪክን ከትዝታ አሰናስለው ይዘዋል።...more15minPlay
February 12, 2026በምዕራብ ሸዋ ዞን ሶስት ወረዳዎች ያልተለመደ የዱር አውሬ ጥቃት የሰው ህይወት እያጠፋ ነውበኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ሶስት ወረዳዎች ስሙ በውል ያልታወቀ የዱር እንስሳ ጥቃት የሰዎች ሕይወት እንዳለፈ ነዋሪዎች ተናገሩ። የዱር እንስሳው በዞኑ አደዓ በርጋ፣ ሜታ ሮቢ እና ሜታ ወልቂጤ ወረዳዎች ለሚገኙ ነዋሪዎች ሥጋት ሆኗል።...more4minPlay
February 12, 2026የሳውዲ አረቢያ ከፍተኛ ባለስልጣን የኢትዮጵያ ጉብኝት አንድምታውጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ብቅ ካሉት የሳዑዲ አረቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፈይሰል ቢን ፈርሃን ቢን አብዱላሕ ጋር ተ “ቀጣናዊ እና አለምአቀፋዊ ጉዳዮች” ላይ መወያየታቸውን አስታውቀዋል። በሱዳን ጦርነት ምክንያት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የአዲስ አበባ ጉብኝት ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶታል።...more5minPlay
February 12, 2026በውጭ ለሚኖር ዘመድ ዶላር ማስተላለፍ የሚቻልበት ሥርዓት ተፈቀደኢትዮጵያውያን ከ3,000 የአሜሪካ ዶላር ያልበለጠ የውጭ ምንዛሬ ከሀገር ውጭ ለሚኖሩ ዘመዶቻቸው "እገዛ እንዲውል" ከሀገር ቤት ወደ ውጭ ማስተላለፍ እንዲችሉ ተፈቀደ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሬ መመሪያ ላይ 19 ማሻሻያዎችን አድርጓል። ርምጃው የምንዛሪ አስተዳደሩን "ቀለል" ማድረጉን የገንዘብ አስተዳደር ባለሙያ ተናግረዋል...more4minPlay
February 12, 2026በኦሮሚያ ክልል ከአመያ ወረዳ የተፈናቀሉ ከ1,200 በላይ ሰዎች ወደ ቀያቸው ተመለሱከአመያ ወረዳ ተፈናቅለው በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ተጠልለው ከቆዩ ተፈናቃዮች ከ1,200 በላይ ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን የአካባቢው ባለሥልጣን ገለጹ። ሁለት ወደ ቀያቸው የተመለሱ ነዋሪዎች የደሕንነት ዋስትና እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸዋል። ለተመላሾቹ ደሕንነት አካባቢዎቹን የሚቆጣጠረው የጸጥታ ዕዝ ኃላፊነት እንደወሰደ አንድ ባለሥልጣን ተናግረዋል...more4minPlay
February 11, 2026“ማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እያመጣን ትርፋማ መሆን እንችላለን” የላቭግራስ ኢትዮጵያ መሥራች ዮናስ አድማሱየብሪታኒያ ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት (BII) ለላቭግራስ ኢትዮጵያ የአምስት ሚሊዮን ዶላር ፋይናንስ እንደሚያቀርብ አስታውቋል። ኩባንያው በሱሉልታ በሚገኘው ፋብሪካ ከጤፍ ፓስታ እና ኩኪሶችን ጨምሮ የተለያዩ ምግቦች እያመረተ ለዓለም ገበያ የሚያቀርብ ነው። መሥራቹ ዮናስ አድማሱ በቢኤንፒ ፓሪባ፣ ጄፔ ሞርጋን እና ክሬዲት ስዊዝ ባንኮች ሠርተዋል።...more0minPlay
February 11, 2026የሱዳን የርስ በርስ ግጭት፤ አፍጦ የመጣው ጣልቃ ገብነት እና ጂኦፖለቲካውበሱዳን እየተካሄደ ባለው የርስ በርስ ግጭት የውጭ መንግስታት ጣልቃ ገብነት በጭምጭምታ ይነገር እንደነበር የሚያስረዱት ተንታኞች ግጭቱ በአፍሪካ ቀንድ የውክልና ጦርነት ሊያስከትሉ ከሚችሉ ክስተቶች ማሳያዎች አንዱ ሊሆን ይችላል ሲሉ ያስጠነቅቃሉ ።...more5minPlay
February 11, 2026ሁለት ሳምንት ሞላን ፤ የሰብአዊ ድጋፍ አልቀረበልንም ፤ ተፈናቃዮችየፌደራል የጸጥታ ኃይሎች ከአላማጣ ፣ኮረም እና ሌሎች አካባቢዎች ለቆ መውጣቱን ተከትሎ ለመፈናቀል የተገደዱ ነዋሪዎች ለብርቱ ሰብአዊ ችግር መዳረጋቸውን አመለከቱ። ተፈናቃዮቹ እንዳሉት ወደ አቅራቢያ ከተሞች ከሸሹ ሁለት ሳምንት ቢሞላቸውም ምንም አይነት የሰብአዊ ድጋፍ እንዳልቀረበላቸው ተናግረዋል።...more4minPlay
February 11, 2026የአብን የፖርላማ ተመራጮች ቀጣዩን ምርጫ አስመልክቶ የወሰዱት አቋምበሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተመራጭ የሆኑት ዶክተር አበባው ደሳለው በመጪው ጠቅላላ ምርጫ ኢሕአፓን ወክለው እንደሚወዳደሩ ትናንት ይፋ አድርገዋል። የፓርላማ አባሉ፤ "ባለፉት አራት ዓመታት ከአብን አመራሮች ጋር በፍፁም ተገናኝቼ አላውቅም" ሲሉ ሌላ ፓርቲን ለመቀላቀል ምክንያት ያሉትን ጠቅሰዋል።...more4minPlay
February 10, 2026የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የቀረው ጊዜ እና ቀጣይ የሚጠበቁ ሥራዎችየኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለአንድ ዓመት የተራዘመለት የሥራ ጊዜው ሊያበቃ አንድ ሳምንት ብቻ ቀርቶታል።ኮሚሽኑ ሥራውን እንዲያጠናቅቅ በሚል የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ዓመት የካቲት 11፤ 2017 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰብ ነበር ጊዜው ለአንድ ዓመት ያራዘመው።ያም ሆኖ ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል ስራ አልጀመረም።...more5minPlay
FAQs about DW | Amharic - News:How many episodes does DW | Amharic - News have?The podcast currently has 2,875 episodes available.